በ16ኛ ክ/ዘ በዓረብኛ በተፃፈ መጽሐፍ የተገኘ ምስጢር


ይህ መፀሀፍ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተፃፈ ነው ተብሎ በየመን አርኪዎሎጂ አጥኒዎች ቁፋሮ ሲያደርጉ በደቡብ የመን የተገኝ መፀሀፍ ነው። በመፀሀፉ ላይ ኢትዮጵያ የሚል በላቲን ፊደል የተፃፈ ስም ይገኝበታል።  በመጀመሪያዎቹ ሁለት ምስሎች ላይ የሚታየው ፁሁፍ አረብኛ ነው። ቃላቱም ክርስቲያናዊ የሆነ የፀሎት ወይም የሥርዓተ ቅዳሴ ትርጉምን የያዘ ነው። በሁለተኛው ምስል ላይ "ጌታ ሆይ'' ቅዱስ ሥጋህንና ደምህን ለመቀበል ብቁ እንዳልሆንኩ አውቃለሁ'' የሚልና የንስሐ ፀሎትን የሚገልፁ ቃላቶች በግልፅ  ይታያሉ።

በአንደኛው ምስል ላይ ደግሞ የጳጳስ ወይም የቅዱስ ሰው ምስል ሲኖር፣ ከጎኑ በላቲን ፊደላት "ETHIOPIE" (ኢትዮጵያ) የሚል ጽሑፍ ይገኛል። ይህ የሚያሳየው መጽሐፉ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ጋር የተያያዘ መሆኑን ነው።

አስቡት በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተፃፈ የብራና መፀሀፍ ከአንድ ሰው መቃብር ስር መገኘቱ የአሁኗ ደቡብ የመንና የኢትዮጵያ ህዝብ የታሪክ ትስስራቸው ምን ያህል የተቆራኘ እንደሆነ በግልፅ ያስረዳል።  በነገራችን ላይ የታሪክ ተመራማሪዎች የአሁኑ ባብል መንደብ የባህር ስፋት በጣም ትንሽ እንደነበር ተደጋጋሚ ጊዜ ሲያስረዱ ነበር።

ገና ብዙ ምስጢር ወደ አደባባይ ይወጣል። ኢትዮጵያም ትንሣኤዋ ይበሰራል!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment