የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሆይ ከልብ ስሙኝ ልንገራችሁ! ሀገራችን ኢትዮጵያን እንመራለን የሚሉ በአሁኑ ሰዓት እንደ ህጻን ልጅ መሐረቤን ያያችሁ አላየንም እባካችሁ አይነት ጨዋታ በህዝብ ላይ እየተጫወቱ ይገኛሉ። የሀገራችን ፖለቲካ የሚዘወርበት ቤተ መንግስቱ የተኩ*ላዎች መነሐሪያ ከሆነ ቆይቷል። ከዚህ ማዕከል የሚወጣው ፖለቲካዊ ቁማር መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀርጥፎ እየ*በላው ይገኛል ። አራት ኪሎ አሁን ህዝብን የሚያስተዳድር ህግ ሳይሆን ሃገርን የሚበታትንና ለእል*ቂት የሚዳርግ ሴራ የሚፈልቅበት የጥ*ፋት ምንጭ ሆኗል። አራት ኪሎ የአምባገነኖችና የወንበ*ዴዎች ዋሻ ከሆነ ቆይቷል። እኛ ኢትዮጵያዊያን ህልውናችንን ለማስጠበቅና ከማትወጣበት አዘቅት ውስጥ የገባችውን ሀገራችንን ኢትዮጵያን ለማውጣት መፍትሄ መፈለግ ይኖርብናል። ይህ አገዛዝ ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጋጨት የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። አገዛዙ የራሱ የሚላቸውን ህዝቦች ለመያዝና ስልጣኑ እንዲቆይለት ደጋፊ ለማግኘት ሲል አደገኛ መርዝ የሆነ ትርክት በመፍጠር ጥላቻ፣ዘረኝነት፣መለያየት፣አድመኝነት፣ነፍሰ ገዳ*ይነትና ልዩ ልዩ የሀገር ሰቆቃዎች እንዲበዙ እያደረገ ነው።
አገዛዙ ወደ ስልጣን በመጣ ማግስት ጀምሮ ፖለቲካዊ ትርክት በማንሳትና በመፍጠር ለዘመናት ተከባብሮና ተዋዶ ተዋልዶ የኖረውን የኢትዮጵያ ህዝብ በማለያየት ህዝብ በህዝብ ላይ እንዲነሳ በማድረግ በዋናነት በሰሜን ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጥፋት እያደረሰ ይገኛል። መንግስት ይህን ያደረገበት ዋነኛ ምክንያት ሀገርን መምራት ባለመቻሉ ስልጣኑን እንደሚያጣ በመረዳቱ ቢሆንም ዋነኛ አላማው ግን አሮጊቷን ኢትዮጵያን አፍርሰን አዲስቷን ኢትዮጵያ እንገነባለን በሚል ጥላ*ቻን መሰረት ባደረገ የተሳሳተ ፖለቲካዊ ስሌት ነው። ስርዓቱ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ብሎ ያሰባት ምን አይነት ሀገር እንደሆነች ማሰብ አያዳግታችሁም! ምናልባት እንግዲህ መንግስት አዲሲቷ ኢትዮጵያ ብሎ የሚያስበው የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ሁሉ በማፍሰስ ለእይታ የሚያብለጨልጫትን አዲስ አበባን ብቻ ይመስለኛል። በነገራችን ላይ አዲስ አበባን ለማስዋብ ሲባል በርካታ የከተማ ነዋሪዎች ተፈናቅለው መጠጊያ አጥተው ተሰደዋል። እነዚህ ህዝቦች ከእናት አባታቸው ጀምሮ በትውልድ በዕድገትም አዲስ አበቤ የነበሩ ስለ ነበር ሲፈናቀሉ ሌላ ቦታ ተሰደው የሚጠጉበት ምንም የላቸውም። መንግስት ይህን እንኳን ታሳቢ አላደረገላቸውም። እንዳውም ይባስ ብሎ ክብርን የሚነካ ከሰባዊነት የወረደ የንቀት ቃላትን ከጠሚዶ አቢይ እስከ ወይዘሪት አዳነች አበቤ ሲናገሩ ሰምተናል።
ይህ የሚያሳየው ይህ ስርዓት በህዝብ ላይ የቆመ ለህዝብ ግን ያልቆመ መሆኑን ነው። አድስ አበባን እግረ መንገዴን ላነሳት ፈልጌ እንጅ መንግስት ባይሳካለትም አድሲቷ ኢትዮጵያ ብሎ ያሰባት ሌላ ናት! እርሷም ለዚች ሀገር መሰረት የሆኑ ነባር ህዝቦችንንና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን በማጥፋት ታሪክ የሌላት የማትታወቅ ሀገር ለመመስረት ነው! በመሰረቱ መንግስት እሽ ይችን አድሲቷ ኢትዮጵያ ብላችሁ የምታስቧትን አምጧት ብንላቸው እንኳን ማሳካት የማይችሉ 7 ዓመት ሙሉ ባህር በር እያለ በአጀንዳ ሲቀልድ የከረመ ህዝብንም በድሮን የሚጨ*ፈጭፍ ወደ ፊት ስንዝር ያልተራመደ ወደ ኋላ ለውድቀት ግን በብዙ ምዕራፍ የሚያፈገፍግ ነው:: ይህ መንግስት ከክፋትና ከወሬ ውጭ ምንም ለሀገር የሚጠቅም ስራ የሰራው አንድም ነገር የለም! እንደ ውሸታቸውማ እስካሁን ኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትና የተፈጥሮ ድፍድፍ ጋዝ አውጥተውም ሀገራችንን የሀብት ማማ ላይ አድርሰዋት ነበር! ወሬ ብቻ!
አብይ አህመድ መራሹ ብልጽግና እያካሄደ ያለው ፖለቲካ የምን ታመጣላችሁ አይነት ፖለቲካ ነው! ለዚህ ነው ሀገራችንን በእብሪት ወደ ማትወጣበት አዘቅት የከተቷት። መንግስት ስልጣናቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ እና ሀገሪቱንም ማስተዳደር እንዳልቻሉ በሚገባ ተረድተዋል። ሀገራችን የእድገት ማማ ላይ እና ፍጹም ሰላም ሰፍኖባታል የሚሉት ምጸታዊ ቃል ነው። ይህን ቃል ህዝብ እንደማይሰማቸውና እንደሚስቅባቸው እያወቁ ይናገሩታል። ከአዲስ አበባ ውጭ አንድም የክፍለ ሃገር ቦታ ሰላም የለም። እንግዲህ በብልጽግናዎች አመለካከት ኢትዮጵያ ማለት አዲስ አበባ ሆነች ማለት ነው። ሲቀጥልም አዲስ አበባ በርካታ የፀጥታ አካላትን በማሰማራት ህዝቡን በማሳቀቅ በፍርሃት እንዲኖር በማድረግ ሰላም የሆነች ቢያስመስሉም በምትኩ ግን ጨለማን ተገን በማድረግ በየጊዜው በርካታ ወጣቶችን እያፈሱ ሁለት ምርጫዎችን በማቅረብ እስር ቤት ወይንሥ ወታደራዊ ስልጣና ተወስዳለህ እያሉ እያሰሩና ያለ ፍላጎቱም የውትድርና ስልጠና እንዲወስድ እያደረጉ ይገኛሉ። ስለዚህ እውነታው አዲስ አበባ ሰላም ናት ማለት በራሱ በጣም ያስቃል! ህዝብ እንኳን ፖለቲካ ነክ ይቅርና የኑሮን ውድነት መከራ ለመግለጽ እንኳን አይችልም! ህዝቡ ታፍ*ኗል! ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉትን የክፍለ ሃገራትን ከተሞችና አጠቃላይ ገጠራማውን ክፍል ምን ያክል ሰቆቃ ላይ እንዳለ እውነታውን ለሁላችሁም እተዋለሁ። እንግዲህ ይህ ነው ብልጽግና ህዝብን እየመራሁ ነው የሚለው ማለት ነው!
ኢትዮጵያውያን ሆይ እንደ አሁኑ ክፍፍላችን ሳይሆን እንደ እውነተኛ ኢትዮጵያዊነት ተሰምቷችሁ ከልባቸሁ እንድትሰሙኝ እፈልጋለሁ። መንግስት ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲል የራሱ የሚላቸውን ብሔሮች (በተለይ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆችን) መንግስታችሁን ጠብቁ እያለ በጊዜያዊ ጥቅም እያታለለ ይገኛል። እነዚህ ጊዜያዊ ጥቅሞች ስልጣን፣የሌሎች ቤት ቀምቶ መስጠት፣ትርክት የወለደውን የመበቀል ተስፋንና ሌሎችም ልዩ ልዩ ነገ እንደ ጥዋት ጤዛ የሚጠፉ የሚያልፉ ናቸው። ላስተዋለውና ነገን ለሚያስብ ሰው እነዚህ የማይጠቅሙና ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው። ሁሉም በዚህ ዓለም ቋሚ ነገር የለም። ዛሬ የገዙ ነገ ይገዛሉ ("ግ" ን አጥብቃችሁ አንብቡ)፣ ዛሬ ያሳደዱ ነገ ይሳደዳሉ፣ ዛሬ የበሉ የነጠቁ ነገ ይራባሉ፣ዛሬ የተራቡ ነገ ይጠግባሉ፣ ዛሬ የጨፈሩ የሳቁ ነገ ያለቅሳሉ፣ ዛሬ ያለቀሱ ነገ ይስቃሉ፤ ዓለም ላስተዋላት እንዲህ ናት። ስለዚህ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ግፍ እና በደል ማድረስ ነገ ዋጋ ያስከፍላል። በነገራችን ላይ ትላንት በህወሓት ዘመን መላው ትግራይ እንደተጠቀመ ስርዓቱ ያስመስል እንደነበረ ሁሉ አሁንም የብልጽግና መንግስት መላው ኦሮምያ በስርዓቱ እንደተጠቀመ በማስመሰል ሌሎችንም ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንዲያስቡ በማድረግና መላው የኦሮሚያ ተወላጆችም በስርዓቱ እንደተጠቀሙ በመምሰል ከስርዓቱ ጎን እንዲቆሙ አድርጓል። ይህም መንግስት ህዝቡን ለመያዝና በእነሱ ተከልሎ ስልጣኑን ለማራዘም የሚጠቀምበት ዋነኛው መንገዱ ነው። ስርዓቱ ህዝብን የሚይዘው በጥቂት ተጠቃሚዎች ሲሆን እነዚህም ጥላቻን በህዝብ መካከል በመዝራት ለመንግስት እንዲቆሙ በማድረግ ነው። ይህ ብቻ አይደለም መንግስት በጥቅም በማታለል በደል በሚያደርስባቸው የአማራና የትግራይ ክልሎችም ሆደ አደ*ሮችን ከጎኑ አሰልፏል! እነዚህም ከአገዛዙ ጋር ሆነው በጭካኔ ህዝብን የሚጨ*ፈጭፉና የሚያስ*ጨፈጭፉ ናቸው::
የአማራ ህዝቦች ነፍጥ አንስተው አገዛዙን እየ*ታገሉ ያሉት የእኛ ብሔር ያልሆነ ወደ ስልጣን መጣ ብለው አይደለም። ይህንንም መላው ኢትዮጵያ ህዝብ ያውቃል። ያኔ አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጣ በብሔሩ የኦሮሞ ተወላጅ እንደሆነ እየታወቀ መላው የአማራ ህዝብ በታላቅ ደስታ ነው የተቀበለው። የሽወዳ ጅማሬውን አይተውም አሻጋሪያችን ሙሴ እስከማለትም ሲያሞካሹት ነበር:: የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ የሚገዛ አገዛዝ ከመጣ ከየትኛውም ብሄር ቢሆን ቅር የሚለው አይደለም። አማራ ወደ ትግል የገባበት ምክንያት ሁላችንም እንደምናውቀው በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ተበትነው የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች በርካታ ግፍ ስለደረሰባቸውና አገዛዙም በአማራ ህዝብ ላይ የዘረጋው የጥፋት መረብ እጅግ ከባድ ስለሆነ ነው። አገዛዙ የኢትዮጵያን ህዝብ በተሳሳት መልኩ ጥ*ላቻ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ትግራይን ካደቀቀ በኋላ ቀጥታ ወደ አማራ ክልል ነው የዞረው። አብይ አህመድ በዋናነት ኢትዮጵያን ለመበታተን የተጠቀመበት ዋነኛ መንገድ አንዱን ክልል ለአንዱ ክልል ጠላቱ በማድረግ ነበር። ለበርካታ ሺህ ዘመናት ተዋዶና ተፈቅሮ የኖረን የሰሜን ህዝብ ከመለያየት ጀምሮ በጋብቻና በደም የተሳሰረውን የኦሮሞንና የአማራን ህዝብ በጠላትነት እንዲተያዩ አድርጓል። ለዚህ ነው አሁን በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች የመከላከያ ዩኒፎርም በመልበስ በአማራ ክልል ውስጥ በመግባት ህዝብን እያሰቃዩ እነርሱም ራሳቸውም የፋ*ኖ ጥ*ይት ሰ*ለባ የሆኑ ያሉት። መንግስት በሰራው ሴራ ምክንያት ለአማራ ህዝብ ጥላቻ ያልነበረው የደቡብ ህዝብ እንኳን አእምሮ እየተቀየረ ይገኛል። ይህም ኢትዮጵያን ተባብረን እንዳናድናት ከፍተኛ መሰናክል ሆኖብናል።
መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች እንድታውቁት የምፈልገው ነገር አማራ እየታገለ ያለው የነፃነት ትግል ለጊዜው ራስን የመከላከል ቢሆንም እንኳን ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ትግል ነው። መንግስት በህዝቦች ላይ ያደረሰውን ግፍ ለመደበቅ ሲል ፋኖ የውጭ የኢትዮጵያ ጠላቶች ተላላኪ ነው እያለ ያታልላል። ሆኖም ግን መንግስት ፍጹም ስህተት ሲሆን የፋኖን ዓላማ በውል ከተረዳችሁ በእርግጠኝነት መላው ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንደምትቆሙ አልጠራጠርም። ፋኖ የብሄር ጥላቻ የለውም! እኛ ኢትዮጵያዊያን ከጥንት ጀምሮ አጥንታችንን በመከስከስ ደማችንን በማ*ፍሰስ ሀገራችንን ስንጠብቅ ቆይተናል። ሁላችንም አንድ የሚያደርገን የጋራ ማንነት አለን። በተለይም ደግሞ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ሁላችንም በደም ተሳስረናል። ከብዙ ሽህ ዓመት በፊት የነበሩ እናት አባቶቻችን ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በጋብቻ በመተሳሰር አንድ ህዝብ እንድንሆን አድርገውናል። ብታምኑም ባታምኑም ማንም ንጹህ የራሱ የሆነ የብሄር ማንነት ያለው የለም። መልካችንን እስኪ አስተውሉት! ምናልባት የቋንቋ ልዩነት ይኖረናል እንጂ በደማዊ ማንነት ግን አንድ ነን። ይህን የምላችሁ ከመጽሐፍ ቅዱስ አምድ ወጥቼ በእናንተ ቋንቋና አስተሳሰብ ስለምናገር እንጂ ሰውማ ከጥንትም አንድ ነን ከአዳምና ከሄዋን የተገኘን! የፖለቲካ ሴራ እንጅ ሰው ሰው ነው አንድ ነን:: ቋንቋም ከባቢሎናዊያን ውድቀት ጀምሮ የመጣ እንጅ ማንነት አልነበረም:: የሰው ልጅ ማንነቱ ሰብዓዊ ፍጡር መሆኑ ብቻ ነው:: ይህም ማንነታችን አንድ የሚያደርገን ነው:: ሰው ሆይ አስተውል ሰው ሁን!
ኢትዮጵያዊያን ሆይ እንዳናስተውል ካደረግን አዚም የምንነቃው መቼ ነው? አሁን የመለያየታችን ትርክት የተፈበረከው ኢትዮጵያን ለመ*ውረው በአሰቡ አውሮፓዊያን ቀድሞ ቢሆንም በዋናነት እንድንለያይ ሴራ የተሰራው ግን ከ1950 ዓ.ም ጀምሮ ነው። ይህን የማይጠቅመንን ትርክት በማስ*ወገድ አንድ ሆነን ለአንድነት መነሳት ይኖርብናል። በየዘመኑ የሚመጣው ስርዓት ሁሉ እየተጠቀመብን ለጥፋት ሰለባ እየሆን መኖር የለብንም። መለያየትን እናስ*ወግድ አንድነትን እናጽና ፍቅራችንን እናድስ አንድ ሆነን ኢትዮጵያን እንታደግ። የቀድሞ ስርዓት ናፋቂዎች እያሉ የሚያሳቅቁን ተበታትን እንድንኖር የሚፈልጉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው። እነዚህም አማራ ከዚህ በፊት እንደተጠቀመ በማስመሰል አሁን በምትኩ በስቃይ መኖር አለበት ብለው የሚያስቡ ናቸው። እነዚህ ሀገራችን ፍጹም ሰላም እንድትሆን ስለማይፈልጉ ነው:: አሁን በያዝነው የመለያየት መንገድ ከቀጠልን መከራችን ከባለፈው እጅግ ይከፋልና እንንቃ! ስለዚህ ሁላችንም ካንቀላፋንበት ከአዚም ነቅተን በፍቅርና በአንድነት በመቆም ሀገራችንን እንታደግ። ወደ ቀድሞ ፍቅራችንም እንመለስ። ህዝብ አንድ ከሆነ ሀገር ይድናል እግዚአብሔርም ምህረቱን ያወርዳል። አምባገነኖችን እምቢ እንበል! ኢትዮጵያን አንድ ሆነን እንታደጋት! ለራሳችን ስንል አንድ እንሁን! ካልሆን ግን እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ስለማይተዋት ሰይ*ፍ ይበረታልና ለሁላችንም የሚመጣው ጊዜ አስፈሪ ይሆናል! አንድ ከሆን መስዋዕትነትን መቀነስ እንችላለን:: የእግዚአብሔርን ቁጣ ፍቅር ትመልሰዋለች! አንድ ከሆን የአምባገነኖች እድሜ ሰከንድ አትሞላም!
ኢትዮጵያ ትነሳለች እንደወደቀች አትቀርም! ትንሣኤዋ ቅርብ ነው። ግን እንዳይዘገይብን በፍቅር አንድ ሆነን እንነሳ!
ድል ለኢትዮጵያ!
Blogger Comment
Facebook Comment