ከዳስ ጣል (አንሳው) እስከ ጀምበርና ጽዮን ሙሽራየ


ቆሞስ አባ ጳውሊ | ከግንባር

በመጀመሪያ ደረጃ ይህን ዕንቁ የሆነ የህዝብ ልጅ ቴዲ አፍሮን ከማመስገን እጀምራለሁ።  ኢትዮጵያ መከራ ውስጥ ባለችበት በአሁኑ ሰዓት ኪነ ጥበብ በጣም ወሳኝ መሆኑን ሁላችንም መገንዘብ ይኖርብናል። እኛ ከበርካታ ጊዜያት ጀምሮ በተለያየ መልኩ ህዝብን ስናነቃ ቆይተናል። እኔ በበኩሌ ከኮቪድ 19 በፊት ጀምሮ ወጣቶችን እንዲነቁ ኢትዮጵያም ከፊቷ ከባድ አደጋ እንደተጋረጠባት ሳስጠነቅቅ ነበር። ይህን ከዚህ በፊት ስናገር እንደሰማችሁት መላው የሰሜን ወሎ ህዝብ በሚገባ ያውቃል። ሌሎችም በርካታ አባቶች በተለያየ ቦታ ወጣቱ እንዲነቃ እና ኢትዮጵያ ከገባችበት መከራ እንድትወጣ ብዙ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ሆኖም ግን ትውልዱ ነቃፊና አስቸጋሪ ስለሆነ እጅግ በጣም ፈታኝ ነበር። እኛም እግዚአብሔር ለጠራን ዓላማ ሳንሰለችና ተስፋ ሳንቆርጥ በተቻለ መጠን ጥረት እያደረግን እንገኛለን። ዛሬ ልጃችን ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ መከራ ውስጥ እንደገባች እኛ አባቶች ስንነግራችሁ የነበረውን  በኪነ ጥበብ ፍንትው አድርጎ ነግሯችኋል። ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን የመከራ  ሁኔታ "ዳሥ ጣል (አንሳው)" በሚለው ላይ በሚገባችሁ መልኩ ነገሯችኋል። ጀምበር በሚለው ላይ ደግሞ ሃምሌዎች የተባሉ የመከራ ምጦች (አምባገነኖች) እንዲያልፉና የኢትዮጵያ የብርሃኑ ዘመን እንዲገለጥ ቁጭት ጋር የመጨረሻው (11ኛው) ሰዓት ላይ እንደሆንም ምኞቱን በሚገባ ገልጾታል። ጽዮን ሙሽራዬ የሚለው ደግሞ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማምጣት ዳር ቁመን መመልከት እንደሌለብን ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ አስገንዝቧችኋል። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ስላለችበት አሁንናዊ ሰቆቃና ሀገራችንን  እንዴት መታደግ  እንዳለብን አመላክቷኋል። ይህ እኛ ለዘመናት ስንነግራችሁ የነበረ እናንተ ግን ያላስተዋላችሁት የኢትዮጵያ መከራ ነው። እንግዲህ እኛን ያልሰማችሁ ምንአልባት በዚህ መልኩ የኢትዮጵያ መከራ ይገለጽላችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።  በመንፈሳዊ ዓይን ስንነግራችሁ ያልሰማችሁት ምናልባት እናንተ በምትወዱትና ሁላችሁንም ባማከለ መልኩ የኢትዮጵያን መከራ ስትሰሙት ትነቁ ይሆናል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ:: በጣም የገረመኝ ነገር ቴዲ ዝናና ፍርሃት ሳይከልለው ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ በሚገባ መረዳቱና ለህዝብ ማሳወቁ ነው። ከዚህ በዘለለ ደግሞ ምንም ስለራሱ ሳይጨነቅ በዚህ በመከራ ሰዓት አገዛዙም ድምጽን እያፈነ ባለበት ሁኔታ ለኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽ መሆኑ ነው። አንዳንድ ወገኖች ዘፈን ኃጢአት ነው ለምን እንዴት ወዘተ••• ሲሉ እየሰማን ነው። እነዚህ ሰዎች ዘፈን ኃጢአት መሆኑ ሁሉም ሰው ሳይረዳው ቀርቶ ይሆናል ብለው እንዳይመስላችሁ። እነዚህ አካላት ያስጨነቃቸው ኢትዮጵያ  ያለችበትን የመከራ ሁኔታ በኪነ ጥበብ ለዓለም ስለገለፀባቸው ነው። ሁሉም የሚቃወሙት ከብልጽግና አምባገነናዊ ስርዓት ጊዜያዊ ጥቅም የሚያገኙት ናቸው። ከዚህ በዘለለ ደግሞ ይህ አምባገነናዊ መንግስት ፕ*ሮ*ቴ*ስ*ታ*ን*ታ*ዊ  መር ስለሆነ እነዚህ አካላት ናቸው የሚቃወሙት።  እነዚህ ሰዎች ግን መዝሙር ብለው (ናኒ ናና ...እየዘለላችሁ•• ) እያሉ በየመድረካቸው ጭፈራን ባስናቀ መልኩ የሚ*ዘሉ ናቸው ድንቄም መዝሙር! ድንቄም ዘፈን ነቃፊ! እነዚህ ሰዎች ሲቃወሙ ማ*ፈ*ር አለባቸው!  

ቤተክርስትያናችን ከጥንት ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ የራሷ ቀኖና፣ዶግማና ትውፊት ያላት ሲሆን ለእግዚአብሔር የምናቀርብበት ምስጋናም ትላንትም ዛሬም ነገም የማይቀየርና ስርዓቱን ሁላችንም የምናውቀው ነው።  ነገር ግን ኢትዮጵያዊያን ሁላችንም እንደ አጠቃላይ የራሳችን የሆነ ትውፊት ያለን ህዝቦች ነን። በሀዘንና በደስታ ሰዓት ማዘናችንንና መደሰታችንን፣ በሀገር መ*ወ*ረ*ር ጊዜ  ድ*ል ማድረጋችንን እንዲሁም ለድ*ል መነሳ*ታችንን የምንገልጽበት የራሳችን የሆነ ስርዓት አለን። ይህ ከሃጥአት ጎራ የማይመደብ ጎጅ ያልሆነ ባህልና ትውፊት ነው፤ ምክንያቱም ሃገርን ለመጠበቅና ለአንድነትም ጠቃሚ የሆነ ማህበራዊ መስተጋብር ስለሆነ። ለምሳሌ ያክል እንደ አብነት ብንጠቅስ ጣሊያን ሀገራችንን በወረረበት ሰዓት አባቶቻችን በቀረርቶ እና በፉከራ ፈሪውን ሲያጀግኑ የደከመውንም ሲያበረቱ ነበር። ሀገራችን ነፃ እንድትወጣም ኪነ ጥበብ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል። ዘፈን ብለን እኛ በሃጥአት የምንፈርጀው ልክ እንደ ሄሮድያዳ በአሻጥር ለነፍስ መጥ*ፋት መንገድ የሚጠርግ አይነት እና ሌላም ለዝሙት የሚገፋፋን ነው።  በድጋሚ ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር ይህን ለህዝብ ደወል የሆነን ድምጽ ለማጣጣል ጥረት የሚያደርጉት አካላቶች እነሱ መዝሙር ብለው ከሚዘምሩት ዳንስ እና ጭፈራ ሽህ ጊዜ ይልቃቸዋል። ይህን ስል ዘፈንን እያበረታታሁ እንደሆነ አድርጋችሁ እንድትረዱት አልፈልግም። እኛ በተደጋጋሚ አሁን ኢትዮጵያ ስላለችበት መከራና ተባብረን አንድ ከሆን ቀጣይ ስለምትመጣው ሙሽራዋ ኢትዮጵያ በብዙ መንገድ መልእክት እያስተላለፍንላችሁ ስላልሰማችሁ ምናልባት በዚህ መልኩ ልትነቁ ትችላላችሁ ብዬ አስባለሁ።

እኛ ዳስ ከጣልን ቆይተናል! ኢትዮጵያ ሃዘን ላይ ናት። ግን ከእናንተ መካከል ሃዘኗን ማን አስተዋለ? እኛ እየጮህን ማን ሰማን? ምንም የሚያስተውል ትውልድ የለም! ከመንቀፍና ከመሳደብ ውጭ መፍትሄ የሚፈልግ አንድም ትውልድ የለም። ይህ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው። ኢትዮጵያዊያን በቃ እንዲህ ሆን ማለት ነው? እሳት አመድን ወለደ ማለት እንዲህ ነው! በታሪክ ከምናውቃቸው ሀገራችንን ጠብቀው ካቆዩልን አባት እናቶቻችን የወረስነው ምንም ጀግንነትም ሆነ አንድነት በፍጹም የለንም። ኧረ ተው እንንቃ! ፋ*ኖ ብቻ ኢትዮጵያን ያድን ዘንድ እጃችሁን አጣጥፋችሁ ተቀምጣችሁ አትጠብቁ! ልናግዛቸው አንድ ሆነን ልን*ነሳ ግድ ይለናል::

አምባገነኑ የአብይ አህመድ አገዛዝ በቅዳሴ፣ በዝማሬ፣ በስነ ጽሑፍ ፣ በቀረርቶና ሽለላ ወዘተርፈ  በጣም የሚደነግጥ ነው። ይህ ደግሞ የአምባገነኖች ዋነኛ ምልክት ነው። ኪነ ጥበብ ህዝብን የማነሳሳት አቅም ስላለው አምባገነኖችን ያስደነግጣቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በርካታ የኪነጥበብ ሰዎችና ጸሐፍት ወህኒ ቤት ታጉረው ይገኛሉ። አምባገነን ስርዓት ሃገርን ሲያፈርስ የሚመለከት የኪነ ጥበብ ሰው ካለ  በጣም ያሳዝናል። ታዋቂነትን ለህዝብ ካላደረገው ለዝና ብቻ ከሆነ ምንም ሊጠቅመው አይችልም። ታዋቂ እንዲሆን ያደረገው ማህበረሰብ በችግር ውስጥ ሆኖ የእርሱን ዝና ተሸክሞት ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? ስለዚህ ሁላችሁም የኪነ ጥበብ ሰዎች ከህዝብ ጎን መቆም ያለባችሁ ሰዓት አሁን ነው።  የፊልም ባለሙያ አርቲስቶች፣ ሰዓሊዎች፣ የግጥም ጸሐፍት፣ ስታንድ አፕ ኮሜዲ አቅራቢዎች፣ ሾው አዘጋጆች ወዘተርፈ ሁላችሁም ኢትዮጵያን በጋራ ልንታደጋት ይገባናል። ሁላችንም በየሙያችን በተለያዩ መልኩና አጋጣሚ ያንቀላፋውን ህዝብ ልናነቃ ይገባናል። በብዛት አዲስ አበባ ተቀምጣችሁ ኢትዮጵያ ምን ላይ እንደሆነች ምናልባት ልትገነዘቡ አትችሉም ይሆናል። አገዛዙ አዲስ አበባን ብቻ በማብለጭለጭና ሀገሪቱ ፍጹም ሰላምና የዕድገት ማማ ላይ እንደሆነች በማሳየት ብዙዎችን እንደሚታለል እናውቃለን። በስውር ግን በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በማንነታቸው ምክንያት ወደ ወህኒ ቤት ተጥለዋል፣ተረሽ*ነዋል፣ ወደ አልታወቀ ቦታ በመወሰድ ተሰውረዋል፣ምንም የማያውቁትን ደግሞ በሽ*ብር ወን*ጀል ስም ተከሰዋል፣ በማንነት ተኮር በተለይ ደግሞ የአማራ ተወላጅ የሆኑትን የኮንዶሚኒየምና የጨረቃ ሌሎችንም ህጋዊ ቤቶቻቸውን ጭምር በመቀማት በምትኩ ተረኛ ብለው ለሚያስቧቸውና የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ ለመቀየር በሚል እሳቤ ከክፍለ ሃገር ድረስ በማስመጣት ሰጥተዋል። ሁላችሁም ደግሞ እንደምታዩት አዲስ አበባ ውስጥ ከትንሽ እስከ ከትልቅ መስሪያ ቤቶች ድረስ የሚሰሩ በብሔር አማራ የሆኑት ከስራ ገበታቸው ተፈናቅለዋል። በየመስሪያ ቤቱ ለምልክት አንዳንድ የምናገኛቸው አማራን ለመበደል ለአገዛዙ ተላላኪ ሆነው የሚያገለግሉ ብቻ ናቸው። አስቡት ይህ የሚፈጸመው አዲስ አበባ ብቻ ነው! ከአዲስ አበባ ስንወጣ አጠቃላይ ሰሜን (ትግራይና አማራ) አሁን ያሉበትን ሁኔታ ሁላችሁም መገንዘብ ያቅታችኋል ብዬ አላስብም!
ይህ ስርዓት አጠቃላይ ዓላማው ሰሜንን በማ*ጥፋት ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው። አገዛዙ ኢትዮጵያንና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን አምሮ ይጣላል፤እያፈረ*ሳቸውም ይገኛል።  የአገዛዙ ደጋፊዎች የቀድሞዋ ኢትዮጵያ ሞታ*ለች  እያሉ የሚሳለቁት ዝም ብለው እንዳይመስሏችሁ። የቀድሞ ኢትዮጵያን የሚጠሉት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን በማሰብ ነው። በተዘዋዋሪ ጸባቸው ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ጋር እንደሆነ ልታውቁ ይገባችኋል።  ወዳጄ ሆይ ዝም ብለህ አንተ በነጠላ ተብለ*ጭነጭ ግን አላስተዋልክም እንጂ መከራ ውስጥ ነህ! ሃገርህም ሃይማኖትህም ሁለቱም ችግር ውስጥ ናቸው አንተ ግን ፃድቅ ፃድቅ  ትጫወ*ታለህ!  እንዲህ አይነት ትውልድ በታሪክ ሰምተን አናውቅም።  ቄስ መነኩሴ ምዕመን ሳንል ሁላችንም ሀገራችንን ማዳን አለብን። በአሁኑ ሰዓት ለህዝብ የቆማችሁ ሁላችሁም እግዚአብሔር ስራችሁን እንደ አቤል እና እንደ አብርሃም የለመለመ መስዋዕት አድርጎ እንደሚቀበልላችሁ አልጠራጠርም። ይቺን ቅድስት ሀገር ለማዳን ጥረት የምታደርጉ ሁሉ በርቱ ጠንክሩ። አሁን ሀገርን የሚያፈርሱ ሁሉ ታሪክ ይሆናሉ። ኢትዮጵያ እንደወደቀች አትቀርም በጀግኖች ልጆችዋ ትነሳለች። ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሰሩ አምባገነኖችና የእነሱ ተላላኪ ሆ*ድ አደሮች ዘለዓለማዊ አይደሉም!  ሁሉም ነገ እንዳልነበሩ ይሆናሉ ፤ኢትዮጵያ ግን ታበራለች!   

የመጨረሺያ መልእክቴ ከአድስ አበባ መጭውን የምርጫውን ጊዜ በማስመልከት እንዲሁም ሰሞኑን በወጣው የቴዲ ማንቂያ በርካታ የአማራና የትግራይ ተወላጆች እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ ስለሆነ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አሳስባለሁ::  መንግስት ሆይ አትድከም ምርጫ ብሎ ጨዎታ የለም!  ዝም ብለህ ድራማህን ስራ! የኢትዮጵያ ህዝብ ግን በቅቶታል! ህዝቡ ነጻነት ተጠምቷል ሰላም ተርቧል! 

ለዚያ ዕንቁ ልጅም እንዲህ በሉት:- አይዞን ሃምሌዎች ይሄዳሉ! የኢትዮጵያ ትንሳኤም ይበሰራል፤ ጽዮንም ትሞሸራለች! 

ድል ለኢትዮጵያ!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment