ከህዳሴው ግድብ ምርቃት ጀርባ


ብዙዎቻችን ብዙ  ነገሮች ከሥጋ ዓይን ብቻ ነው የምንመለከተው እስኪ በመንፈሳዊ ዓይንም ለመመልከት እንሞክር። ይሄ ግድብ በሥጋ ስለሚሰጠው ጥቅም በየመገናኛ ብዙኃኑ ብዙ ተብሏል ከነፍሳችንንስ አንጻርስ ጥቅሙ ወይስ ጉዳቱ ያመዝናል?

ዋናው የግድቡ ዓላማ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት  ውጪ ሀገር  ያሉ ክፍተኛ ኃይል የሚጠቀሙ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን ለምሳሌ (Cryptocurrencie Mining እና AI )  ላይ የሚሠሩ  ድርጅቶች ወደ ሀገር ሲገቡ እንዲጠቀሙበት እና  አሁን ያለውን ሀገሪቷን ወደ ዲጂታል ሥርዓት የማስገባቱን ሥራ በጣም በማፋጠን ህዝቡን ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል ስርዓት ለመቆጣጠር የታሰበ ነው።

የኛም የግራኝ ዐቢይ አሕመድ መንግሥት አካሄድ ልክ እንደ ቻይና ህዝቡን ወደ አውሬው ስርዓት ለማስገባት እጅግ በጣም እየተሯሯጠ ይገኛል። ይሄም ደግሞ በተወሰነ መልኩ ይሳካል ለምን ቢባል እዚህ ሀገር ውስጥ የአውሬውን ስርዓት  የሚናፍቁ የሀገር  እድገት ነው፣ ብልጽግና ነው፣ ቴክኖሎጂ ነው እያሉ  እራሳቸውን የሚያታልሉ ከኃዲያን ፣ መናፍቃን፣ አሕዛቦች ፣  አስመሳይ ክርስቲያኖች ስላሉ እነሱን ለመጠቅለል ወደ እዚህ ሀገርም መግባቱ አይቀርም.።

እንዴ ፋይዳ መታወቂያ አውጡ፣ በሞባይል ክፍያ ክፈሉ ፣ ኦን ላይን ተመዝገቡ፣ ፋይዳ ከሌላችሁ አገልግሎት አታገኙም ፣ ትምህርት አትማሩም ፣ አትታከሙም ወዘተ  እያሉ  ሰውን በውዴታ ግዴታ ወደ አውሬው ስርዓት ለማስገባት  እየተሯሯጡ ነው። በጥቂት ዓመታት ውስጥም ከላይ ከላው የባሰ አሰራሮች ሁሉ መምጣታቸው ሁሉ አይቀርም።

መፍትሔውስ ምንድነው? ችግሩ በጣም ከባድ እንደሆነ ሁሉ መፍትሔውም ከባድ ነው ግን አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው.... እነሱ ወጥመድ አድርገው የያዙብንን አገልግሎቶች በተቻለ አማራጭ ፈልጎ  ለመላቀቅ መሞከር ነው...   መብራቱንም፣ ውሃውንም ፣ ስልኩንም ፣ ባንኩንም ፣ትምህርቱንም ፣  ኢንተርኔቱን ወዘተ  ሁሉ እነሱ ሰውን ወደ አውሬው ስርዓት ለማስገበት የሚጠቀሙባቸው ወጥመዶቻቸው ናቸው እና ለነዚህ ነገሮች አማራጭ መፈለግ ካልሆነ ጥሎ መሸሽ ብቻ ነው ያለው አማራጭ... አባቶችም በትንቢት  እደሚናገሩት ከውጪ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ስደት ይሆናል፣ ከኢትዮጵያ ከተማዎችም ወደ ገጠር እና  እስከምጽአት ጊዜ ድረስ ቃልኪዳን ወደ ተሰጣችቸው ገዳማት  ሰው ይሰደዳድ ይላሉ።

በኢትዮጵያ ታሪክም እንደሚነገረው ድሮ በጥንት ጊዜ የዓለም ህዝብ አንድ ሆኖ በእግዚአብሔር ላይ አምጾ የባቢሎንን ግንብ የሚገነባ በነበረበት ወቅት እኛ በእግዚአብሔር ላይ አናምጽም ይሄንን ግንብም ለመገንባት ከናንተ ጋር አንድ አንሆንም ብለው ከባቢሎን ተሰደው የመጡ አጋዚያን የተባሉ ነጻ ህዝቦች ሃገር እንደመሠረቷት ይነገራል.... 

አሁንም በሀገራችን ያሉ ገጠሮች እና ገዳሞቻችን፣ የዓለም ሰዎች በባቢሎን ጊዜ የተቋረጠውን ፕሮጀክት በሐሳዊው መሲህ እና በአውሬው ስርዓት መሪነት በሚያስቀጥሉበት ጊዜ ልክ እንደቀደመው ይሄንን ስርዓት አንቀበልም ብለው ከአውሬው ስርዓት ወጥተው፣ እግዚአብሔርን እያመለኩ  በየገጠሩ እና በየገዳማቱ ማሕበረሰቦችን መሥርተው የሚኖሩ፣ ሌሎች ተሰደው የሚመጡ  እየተቀበሉ እስከ ዳግም ምጻት ጊዜ ድረስ ከአውሬው ስርዓት የማምለጫ ቦታ እንደሚሆኑ ቀድሞ የተነገረ እና ሊፈጸም ትንሽ የቀረው ትንቢት ነው።

የአውሮፓ ፓርላማ  ድሮ በባቢሎን ጊዜ  የተቋረጠውን ፕሮጀት አሁን እያስቀጠሉ ነው።


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment