የአለቃ አያሌውን አንጎል ጅብ አውጥቶ ሲበላው ያዩት መምህር‼️‼️


«ትንቢት ይቀድሞ ለነገር።» 

የአለቃ አያሌው መምህር የነበሩት የአለቃ ማርቆስ ብርሃኑ ሕልም። በልጅነት ዕድሜያቸው ካስተማሯቸው ታላላቅ መምህራን አንዱ የሆኑት የንታ መምህር ማርቆስ ብርሃኑ፤ ስለ አለቃ አያሌው ታምሩ ያዩትን ታላቅ ሕልም ለተማሪያቸው ለመምህር ዘሚካኤል ይሁኔ ነግረዋቸው ነበር። ይህንንሕልምም ከመምህር ዘሚካኤል እንደ ተነገረን አቅርበነዋል። 

«ሕልሙን ያዩት የንታ መምህር ማርቆስ የሕፃኑን አንጎል ጅብ አውጥቶ ሲበላው ያያሉ። በጣም ይደነግጡና እስከሚነጋ ቸኩለው ከቅኔ ቤቱና ከመጽሐፍ ትምህርት ቤት ጉባኤ መካከል የነበሩ ሦስት ወይራዎች ተክለው እዚያ ውስጥ በዓት አድርገው ስለ ተማሪዎች ይጸልዩ ወደ ነበሩት የንታ እውነቴ ወደ ተባሉ ባሕታዊ ሄደው ይነግሯቸዋል። ምክንያቱም እንደ አባት ነበር የሚያዩአቸው።

ባሕታዊውም፤ «ምን ያስደነግጥሃል ማርቆስ?» ይሏቸዋል። «እኔስ ይህንን የምወደውን ሕፃን በሕልሜ አንጎሉን ጅብ አውጥቶ ሲበላው አይቼ ደንግጬ ነው፤» አሏቸው። «አይዞህ አትደንግጥ፤ ይህ ሕፃን ትልቅ ሰው የሚሆን ነው።

ምክንያቱም ጅብ ማለት ሕዝብ ማለት ነው። አንጎል ማለት ደግሞ አእምሮ ነውና ይህ ልጅ ትልቅ ሰው ሆኖ የዚህን ሕፃን አንጎል ብዙ ሕዝብ ይጠቀምበታል። 

ጠብቀው ታላቅ ራእይ ታያለህ፤ ይሁንለት፤» ብለው በበጎ ሲተረጉሙላቸው ዳንኤል ለናቡከደነፆር እንደ ተረጐመለት ሁሉ ደስ አላቸው። ይህ ሲያያዝ ደርሶ ይኸው እሳቸው ዛሬ የሕዝብ አባት፥ የሕዝብ ምግብ ሆነው ኖሩ፤» ሲሉ ይህ ታሪካቸው ተመዝግቦ እንዲታወቅ ፈቃዳቸው መሆኑን በመግለጽ መምህር ዘሚካኤል ተናግረዋል።
+++++++++++++++

🌿 አቡነ ወልደ ጊዮርጊስ(አለቃ አያሌው ታምሩ) መጋቢት ፳፫ ቀን ፲ ፱፻፲ ፭ ዓመተ ምሕረት በዕለተ እሑድ እኩለ ቀን ላይ ከዲማ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በስተምዕራብ አቅጣጫ በሚገኘው ልዩ ስሙ ቤተ ንጉሥ በተባለው ቦታ አንድ ሕፃን ተወለደ። ከወይዘሮ አሞኘሽ አምባዬና ከአቶ ታምሩ የተመኝ አብራክ የተገኘው ይህ ሕፃንም «አያሌው» የተሰኘ ስም ወጣለት።

በረከታቸው ይደርብን!!! 


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment