የአባ ገብረ ኪዳን ሌላኛው የጥፋት ፕሮጀክት!

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ አውታር

የአባ ገብረ ኪዳን ሌላኛው ፕሮጀክት ፣ በ2019 ከKG እስከ ሃይስኩል ከዛ ኮሌጅ ገንብተው፣ ትውልድ እንቀርጻለን  እያሉ ነው። ጥያቄው ምን አይነት ትውልድ ነው መቅረጽ የፈለጉት?

እርሳቸው የሚያስተምሩት ጉባኤ፣ የአብነት ትምህርቱ ፣ የቆሎ ትምህርት ቤቶች ትውልድ አይቀርጹም ማለት ነው? የቀደሙት ነገሥታት እና ሃገር ሁሉ ተጠብቃ የነበረችው በቤተክርስቲያን ጉባኤ ቤቶች አልነበረም?  አሁን ለምንደው  ትውልድን ለመቅረጽ KG እና ሃይስኩል መገንባት ያስፈለገው?

ሲጀመር እርሳቸው ስለ ኬጂ እና ሃይስኩል ግንባታ ምን አገባቸው?  አንድ በትምህርት ሚኒስቴር ያለ ሃላፊ  ወይም በመካነ አዕምሮ/ዩኒቨርስቲ ውስጥ ያለ ፕሮፌሰር፣ ትውልድ ለመቅረጽ የአብነት ትምህር ቤት እናቋቁም ብሎ ይናገራል?

ትውልድ መቅረጽ ከፈለጉ ሙሉ ቀን የሚያስተምር አብነት ትምህርት ቤት አይገነቡም?  ወይስ የሚያስተምሩት ጉባኤ እንደ ጊዜ እንደማሳለፊያ ነው የሚቆጥሩት?

ይሄ ለሳቸው ብቻ ሳይሆን በቤትክርስቲያን ውስጥ ላሉ ዓለማዊ ትምህርት ቤቶች ሁሉ ነው።

አባ ቀጥለው ትውልዱን  ለማዝናናት  ሆቴል እና  ናይት ክለብ እንዳይገነቡ ነው የምፈራው።

"ዘመናዊው ትምህርት" የሚባለው እኮ እዚህ ሃገር ተሞከረ ፣ ተሞከረ ምን አይነት ትውልድ አንደሚያፈራ ወጤም ታየ እኮ። መጀመሪያ ሃይስኩል፣ በመካነ አዕምሮ/ዩኒቨርስቲ የተማሩት ከሃዲ ሱሰኛ ፣ ሃይማኖት የለሽ ሆኑ ፣ ሃይማኖትን ለወጡ ፣ ሀገርን አፈረሱ፣  እርስ በርሳቸው ተጨራረሱ ፣ ከዛም በኃላ ያሉት ሃይማኖት የላቸውም ስለሃገር አይጨንቃቸውም ገንዝብ የሚያሳድዱ፣ ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ይሚያስቡ ፣ ሃገርን ቅርጽ የሚያወቱ የሚሸጡ ናቸው የሆኑት፣ እነሱም መጨረሻቸው በሽተኞች ነው የሆኑት።

አሁንም የተማረው ዘረኛ፣ መናፍቅ ፣ ሱሰኛ  እና  ሴሰኛ ፣ ግብረሰዶማዊ  ነው። ዘመናዊው  ትምህርቱ በራሱ የክህደት መንገድ ነው። 

ታዲያ ለምንድነው  ቤተክርስቲያን ልጆቿን ለዚህ አይነት ክህደት አሳልፋ እንድትሰጥ የሚደረገው?

እንደው ወደ ቅድስና ህይወት ቢገባ እንኳን የተማረውን የዓለማዊ ትምህርት ከንቱነት እና ያባከነውን ጊዜ እየቆጨው ነው የሚሆነው።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment