እንግዲህ ወገኔ ስለስንቱ እናንሳ ስለእያሱ፣ ስለኤልያስ፤ ስለነዳዊት ሁሉንም ታውቃቸዋለህ፤ ልብ ብለህ አድምጥ፤ ምንም መጥፊያህ ላይ ብትደርስም በሞትህ ጉዞ ውስጥ እውነትን እየሰማህ ወደመደምደሚያህ
መድረስ አለብህ። ባንተ ቀሪው የልዑል ሕዝብ የሚማርበትን ታሪክና ገድል ከአንተ ተሞከሮን ይጨብጣል።
ለሕይወቱና ለልጆቹ ማስተማሪያ ግብአት እንዲሆን ወደትንሳኤው ዘመን ይዞትም ይሻገራል። አንተም እንደ እስራኤላውያን አባቶች በጥመታቸው በክህደታቸው በየበረሃው ወድቀው እንደቀሩት ትሆናለህ። መላው የአዳም ዘር! አንተ የዛሬው ትውልድ ምን እንበልህ ምንም ማለት እንችልም በቃ! አከተመ! ተደመደመ! ስለአንተ ማሰብም መስማትም የማይቻልበት ፍፁም የሚዘገንንበትም ወቅት ላይ ደርሰናል። እንግዲህ ዲሞክራሲህን፤ የዲያብሎስ ድርሰትህን የታበይክበት ሥልጣኔህን የከመርከው መሳሪያና ሀብትህን ሁሉም ላይታደጉህ ሲተኑ አንተም ዘር ማንዘርህም ከአባትህ ከዲያብሎስ ጋር እሁኑኑ ስትካተት ታየዋለህ። እውነቱ ይህ ነው።
የእግዚአብሔር ሕዝብ መፋረጃ ነው። ብትወደውም ብትጠላውም አንዳንተው ሰው ነው፤ ልዩነቱ እሱ በፈጠረው አምላኩ ይታመናል አንተ ደግሞ በፍጡሩ ዲያብሎስ ትታመናለህ ትመካለህ። ልብ በል የእግዚአብሔር ሕዝብ፤ በልዑል ፊት የከበረ የሚወደድ ነው። ቁጥር በእግዚአብሔር ዘንድ ትርጉም የለውም። በዘመነ እስራኤል በኤልዛቤልና በአከዓብ ንግሥና ዘመን የእስራኤል ሕዝብ አግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ የተመረጡት ካሕናት ሁሉ እግዚአብሔርን ክደው ቡኤል ዘቡኤልን አንግሰው በሚያመልኩበት ዘመን የታመነው የእግዚአብሔር አገልጋይ ኤልያስ ብቻ ነበር፤ በአደባባይ ወጥቶ በአምላኩ በሠራዊት ሁሉ ጌታ ስም የተፋለማቸው። ታዲያ እግዚአብሔር ቁጥር ገደደው በፍፁም፤ በቃሉ የታመነው አምላካችን ከኤልያስ ጎን ቆመ እንጂ በቁጥር ምድርን ከሸፈኑት እስራኤላውያን ጎን አልቆመም።
እግዚአብሔር እውነት ነው ስሙም ያው እውነት ነው፤ ቅንም ነው እውነተኛ ዳኛም ነው፤ ለማንም ፊት አይቶ የማያዳላ ነው። ፍቅርም ነው ስሙም ያው ፍቅር ነው። እንዲያ በመሆኑ ነው 7500 ዓመታትን የተሸከመን ቸር ነው እየበደልነው ተሽከሞ እኑሮናል ከዘመን ዘመን አሸጋግሮናል።
ወገኖቼ! የእግዚአብሔር ሕዝብ ውኃ ልክ ነው መፋረጃም ነው። መለኪያ ነው። ስለመርዶክዮስ ስሰነዳንኤል ስለነሕዝቅኤል ስለነዳዊት ወዘተ ... በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንደከዋክብት የሚያበራ
ሆኖ ተመዝግቧል። የእግዚአብሔር ሕዝብ ውኃ ልክ ነው።
ለሌላው የአዳም ዘር ሁሉ እኩል የተዘራውን የእግዚአብሔር ቃል የሰማ ቢሆንም በትክከል የተቀበለው እንደቃሉ ሆኖ በተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ፀንቶ፤ ከመላው ዓለም ሕዝብ አንፃር በቁጥር ኢምንት ቢሆንም በልዑል ፊት ግን የተወደደ ሆኖአል። ብዙ እምነት እንደጎርፍ የሚፈስባት ምድራችን ሁሉንም አንግሣ የተዋህዶ እምነትን ብቻ እንደጠላት ስታሳድድ ኖራለች።
ያ የምታሳድደው ሰው ደግሞ እግዚአብሔርና ቃሉን በሕይወታቸው አንግሰው በእለት ተእለት ሕይወታቸው የሚመላለሱ ናቸው። ብርሃናቸው በሰው ሁሉ ፊት እንዲበራና ምሳሌም እንዲሆን ተደርጎ በልዑል የተቀረፀ
በመሆኑ ዛሬም በእግዚአብሔር በስስት የሚታዩ ልጆቹ ናቸው።
ኖኅ ምድርንና በወቅቱ የነበረውን አመፀኛ ሕዝብ በእምነቱ ዕናት እየኮነነ እግዚአብሔርም በዚህ በእውነት ላይ በቆመ ውድ ባሪያው በኩል ለማይታዘዘው ለአመጸው ትውልድ ፍርዱንና ወቀሳውን ሲያስተላልፍ ኖሯል።
ውኃ ልኩ ኖኅ በጽድቅ ሥራው ዓለምን ኮንኗል።
የልዑል ባሪያ ታማኙና ቀናኢው ኤልያስ በዘመኑ ውሀ ልክ ሆኖ አልፏል። ኤልያስ እስራኤላውያን እጅግ ባመፁበት ዘመን ስለእግዚአብሔር ቃል ፀንቶ በመቆም እንደ ፀሐይ ያበራ የእምነት ጀግና ነው። በጽድቅ ሥራው
እንደፀሐይ በሚያበራ ሕይወቱ ልዑልን በሕይወቱ ያነገሰ ጀግና ነው። ኤልያስ በዚያ ክፉ ዘመን ስደቱንም ረሃቡንም ሁሉንም የጠላት ጥቃት የተቀበለ የልዑል ባሪያ ነው።
እስራኤላውያን በዘመናቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ማመጽን የሚያዘወትሩ ነበሩ። በንግሥት ኤልዛቤልና በንጉሥ አካብ ዘመን ሁሉንም ካሕናት ጨምሮ መላው የእስራኤል ሕዝብ አምላኩን ክዶ ነበር። እግዚአብሔር
በስውር ከጠበቃቸው የታመኑ ልጆቹ በስተቀር ሁሉም እስራኤላውያን ቡኤል ዘቡኤልን የሚያመልኩና ንጉሱም ንግስቲቱም በዚሁ ጣኦት ፍቅር የተለከፉ ነበሩ። የልዑል ቃል በመጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ፤ ምዕ 18 ፡ 15 – 40 እንዲህ ይላል!
ሆኖም የእግዚአብሔር ባሪያ ኤልያስ ስለአምላኩ ታላቅ ቀናኢ ነበርና በስሩ ከሚያገለግለው አንዱ የሆነውን አብዲዩን ኤልያስ እንዲህ አለው! በፊቱ የቆምሁት ሕያው እግዚአብሔርን እኔ ዛሬ ለእርሱ እገለጣለሁ /ለአክአብ/ አለ። አብድዩም አክአብን ሊገናኘው ሄደ፤ ነገረውም። አክአብም ኤልያስን ሊገናኘው መጣ። አክአብም ኤልያስን ባየው ጊዜ እስራኤልን የምትገለባብጥ አንተ ነህን? አለው።
ኤልያስም፦ እስራኤልን የምትገለባብጡ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ በዓሊምን የተከተላችሁ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ፤ እንጂ እኔ አይደለሁም። አሁንም ልከህ እስራኤልን ሁሉ በኤልዛቤልም ማእድ የሚበሉትን አራት መቶ ሃምሳ የበአልን ነቢያት አራት መቶም የማምለኪያ አፀድን ነቢያት ወደ እኔ ወደ ቄርሜሎስ ተራራ ሰብሰብ አለ።አክአብም ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ ልኮ ነቢያቱን ሁሉ ወደ ቄርሜሎስ ተራራ ሰበሰበ።
ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፦ እስከመቼ ድረስ በሁለት ሃሳብ ታነክሳላችሁ፤ እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤ በአል ግን አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ አለ። ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም።
ኤልያስም ሕዝቡን አለ፦
ከእግዚአብሔር ነቢያት እኔ ብቻ ቀርቻለሁ፤ የበአል ነቢያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። ሁለት ወይፈኖችን ይስጡን እነርሱ አንድ ወይፈን ይምረጡ እየበለቱም ይቁረጡት በእንጨትም ላይ ያኑሩት በበታቹም እሳት አይጨምሩ፤ እኔም ሁለተኛውን ወይፈን አዘጋጃለሁ በእንጨቱም ላይ አኖረዋለሁ።
በበታቹም እሳት አልጨምርም እናንተም የአምላካችሁን ስም ጥሩ እኔም የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ ሰምቶም በእሳት የሚመልስ አምላክ እርሱ አምላክ ይሁን ሕዝቡም ሁሉ ይህ ነገር መልካም ነው ብለው መለሱ።
ኤልያስም የበአልን ነቢያት፦ እናንተ ብዙዎች ናችሁና አስቀድማችሁ አንድ ወይፈን ምረጡና አዘጋጁ የአምላካችሁንም ስም ጥሩ በበታቹም እሳት አትጨምሩ አላቸው።
ወይፈኑንም ወስደው አዘጋጁ። ከጠዋትም እስከ ቀትር ድረስ በአል ሆይ ስማን እያሉ የበአልን ስም ጠሩ። ድምጽም አልነበረም፤ የሚመልስም አልነበረም። በሠሩትም መሰዊያ ዙሪያ እያነከሱ ያሸበሽቡ ነበር። በቀትርም ጊዜ ኤልያስ፦ አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጮሁ ምናልባት ሃሳብ ይዞታል ወይም ፈቀቅ ብሏል። ወይም ወደ መንገድ ሄዷል። ወይም ተኝቶ እንደሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል። እያለ አላገጠባቸው።
በታላቅም ቃል ይጮኹ፤ እንደ ልማዳቸውም ደማቸው እስኪፈስስ ድረስ ገላቸውን በካራና በቀጭኔ ይቧጭሩ ነበር። ቀትርም ካለፈ በኋላ መስዋእተ ሰርክ እስኪደርስ ድረስ ትንቢት ይናገሩ ነበር። ድምጽም አልነበረም የሚመልስና የሚያደምጥም አልነበረም።ኤልያስም ሕዝቡን አለ፦ ወደ እኔ ቅረቡ አላቸው ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ የነበረውንም የእግዚአብሔር መሰዊያ አበጀ።
ኤልያስም፦ ስምህ እስራኤል ይሆናል የሚል የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ደረሰለት እንደ ያዕቆብ ልጆች ነገድ ቁጥር አሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ወሰደ። ከድንጊያዎቹም ለእግዚአብሔር ስም መሰዊያ ሰራ፤ በመሰዊያውም ዙሪያ ሁለት መስፈሪያ እህል የሚይዝ ጉድጓድ ቆፈረ። እንጨቱንም በተርታ አደረገ ወይፈኑንም በብልት በብልቱ ቆረጠ። በእንጨቱም ላይ አኖረና አራት ጋን ውኃ ሙሉ በሚቃጠለው መስዋእትና በእንጨቱ ላይ አፍስሱ አለ። ደግሞም ድገሙ አለ። እነርሱም ደገሙ። እርሱም ሶስተኛ አድርጉ እለ። ሶስተኛም አደረጉ፤ ውኃውም በመሰዊያው ዙሪያ ፈሰሰ። ደግሞም ጉድጓዱን በውኃ ሞላው።
መስዋእተ ሰርክ በሚቀርብበት ጊዜ ነብዩ ኤልያስ ቀርቦ – አቤቱ የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤል አምላክ ሆይ፤ አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደሆንህ እኔም ባሪያህ እንደሆንሁ ይህንንም ሁሉ በቃልህ እንዳደረግኸው ዛሬ ይገለጥ። አንተ አቤቱ አምላክ እንደሆንህ ልባቸውንም ደግሞ እንደመለስህ ይህ ሕዝብ ያውቅ ዘንድ ስማኝ አቤቱ ስማኝ እለ። የእግዚአብሔርም እሳት ወደቀች፤ የሚቃጠለው መስዋእቱንም እንጨቱንም ድንጋዮቹንም አፈሩንም በላች በጉድጓዱ ውስጥ ያለውንም ውኃ ላሰች።
ሕዝቡ ሁሉ ያንን ባዩ ጊዜ በግምባራቸው ተደፍተው እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው አሉ። ኤልያስም ከበአል ነቢያት አንድ ሰው እንዳያመልጥ ያዙ አላቸው። ያዙአቸውም ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ አሳረዳቸው።
ይላል የልዑል ቃል! የእምነት አርበኛው ኤልያስ ማን እንደነበር በጥቂቱ አየን።
✍ኢትዮጵያ የአለም ብርሃን መልእክት ቁጥር 8 ከገጽ 13 - 15
Blogger Comment
Facebook Comment