አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል። እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና

 

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹፩]

፩ እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።

፪ እስከ መቼ ሐሰትን ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼ ለኃጢአተኞች ፊት ታደላላችሁ?

፫ ለድሆችና ለድሀ አደጎች ፍረዱ፤ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ አድርጉ፤

፬ ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፤ ከኃጢአተኞችም እጅ አስጥሉአቸው።

፭ አያውቁም፥ አያስተውሉም፤ በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፤ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።

፮ እኔ ግን። አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤

፯ ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ አልሁ።

፰ አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍርድ፥ አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹፪]

፩ አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።

፪ እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።

፫ ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።

፬ ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።

፭ አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ፤ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፤

፮ የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥

፯ ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤

፰ አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው።

፱ እንደ ምድያምና እንደ ሲሣራ፥ በቂሶንም ወንዝ እንደ ኢያቢስ አድርግባቸው።

፲ በዓይንዶር ጠፉ፥ እንደ ምድርም ጕድፍ ሆኑ።

፲፩ አለቆቻቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፥ ታላላቆቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው።

፲፪ የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንወርሳለን የሚሉትን።

፲፫ አምላኬ ሆይ፥ እንደ ትቢያ በነፋስ ፊትም እንደ ገለባ አድርጋቸው።

፲፬ እሳት ዱርን እንደሚያቃጥል፥ ነበልባልም ተራሮች እንደሚያነድድ፥

፲፭ እንዲሁ በቍጣህ አሳድዳቸው፥ በመቅሠፍትህም አስደንግጣቸው።

፲፮ ፊታቸውን እፍረት ሙላው፥ አቤቱ፥ ስምህንም ይፈልጋሉ።

፲፯ ይፈሩ ለዘላለሙም ይታወኩ፤ ይጐስቍሉ ይጥፉም።

፲፰ ስምህም እግዚአብሔር እንደ ሆነ፥ በምድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ።

“አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል። እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ። ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ። አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ፤ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፤ የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥ ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤ አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው።”

የእግዚአብሔር ቃል በእውነት ድንቅ ነው!!!

በሃገራችን እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ ይሄ እኮ ነው! እነማን “እንታይ! እንታይ! ሁሉም ኬኛ!” እያሉ እንደሚጮኹ፣ እነማን ሕዝባችንን በምክርና ማታለያ ቃላት እየሸነገሉ ለማደናበርና ለማሳመን እንደሚሞክሩ፣ እነማን እንደሚዋሹና ሀሰተኛ ፍርድንም እንደሚሰጡ፣ እነማን የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማጥፋት እንደሚሹ፣ እነማን ቅድስት ኢትዮጵያን ለመውረስ እንደሚተጉ፣ እነማን “ኢትዮጵያ ትፈርሳለች!” እንደሚሉ፣ እነማን በተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን እግዚአብሔር አምላኳ ላይ በመነሳት ከእስማኤላውያን እና ኤዶማውያን ጋር ቃል ኪዳን እንደሚያደርጉና እንደሚያብሩ በግልጽ እያየነው ነው።

የሃገራችንን ጠላቶች እግዚአብሔር በቍጣው ያሳድዳቸው፣ በመቅሰፍቱም ያስደንግጣቸው!!!

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment