ኪዳነ ምሕረትና ቅዱስ መስቀሉ፣ አይለያዩምና በአንድ ቀን ዋሉ።

 

✍
 አሐዱ ዓለም ኢትዮጵያዊ 

በተዋሕዶ ምሥጢር፡ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ድንግል ማርያም ናት፤ ድንግል ማርያም፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ቅዱስ መስቀል፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ቅዱስ መስቀል ነው። ፈጽመው አይለያዩምና።

እኛ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ኹለቱን አካላትና ባሕርያት፡ ማለትም፡ እግዚአብሔር ወልድንና ድንግል ማርያምን፥ እንዲሁም፡ በድንግል ማርያም ሰውነት የተገለጸውን እግዚአብሔር ወልድንና መስቀሉን፡ ፈጽመን አንለያያቸውም፤ የምናውቃቸውና የምናምንባቸው፥ የምናመልካቸውና የምንሰግድላቸው፡ በአንድነታቸው እንጂ፡ ተለያይተው በተናጠል አይደለም፤ በሥዕላችን እንኳ አንለያያቸውም፤ የተለያዩበት ሥዕል፡ ከኢትዮጵያዊነት ውጪ፡ ባዕድ ይኾናል።

እግዚአብሔር ወልድ ለኾነው፡ ለኢየሱስ ክርስቶስ እናት፡ ለቅድስት ድንግል ማርያም እና ለቅዱስ መስቀሉ፡ በእውነትና በመንፈስ ቅዱስ አምልኳችን ኾነን፡ የአምልኮ ስግደትን የምናቀርብላቸው፡ በዚህ ምክንያት ነው። ይህን እውነታ፡ ኹሉም ይወቀው! ለእነርሱ የምናቀርበው ስግደት፡ የአምልኮ እንጂ፡ የጸጋ፥ ወይም የአክብሮት አይደለም።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment