✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
[ራዕይ ዮሐንስ ፪:፲፫]
"የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስበነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።"
ሞኙ ኢትዮጵያዊ በአዲስ አበባ ጉዳይ ሲባላ የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ በሱዳን እና ሶማሊያ ዳግማዊ ግራኝ አሕመድን በመናሳሳት ላይ ነች።
ምንም የሌላቸው ውቂያኖስ አቋርጠው ሌሎች ሃገራትን ለመያዝ ይሞክራሉ፤ ዓለምን የመግዛት ፀጋና ስጦታ ያለን እኛ ኢትዮጵያውያን በዘረኝነት፣ ጐጠኝነት፣ ጠባብነት፣ ብሔርተኝነትና መንደርተኝነት በሽታ እራሳችንን ለማጥፋት ተነሳስተናል።
በሱዳን የተፈጠረውን ውጥንቅጥ ሁኔታ በመጠቀም (እስከ መቶ ሰዎች በዚህ ሰሞን ተገድለዋል) ሲ.አይ.ኤና ቱርክ የመለመሉትን ሱዳናዊውን ወታደር መሐመድ ሃምዳን ዳጎሎን፡ "ሄሜቲ" ስልጣን ላይ ለማውጣት እያዘጋጁት ነው፤ ልክ እንድ ኮሎኔል (እንዴት ያገኘው ማዕረግ ነው?) ዶ/ር (ማን የሰጠው ማዕረግ ነው?) አብዮት አሕመድ። ሙርሲ= አሕመድ = ሄሜቲ።
በአሜሪካ እና ጀርመን እርዳታ ለኢትዮጵያ እንኳን የተረፈ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የገነባቸው ቱርክ የቀድሞዋን የኦቶማንን/ኦስማን ግዛት መልሳ ለማምጣት ደፋ ቀና በማለት ላይ ነች። ይህ የኦስማን ግዛት ግራኝ አሕመድን ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት በማነሳሳት ተዋሕዶ ኢትዮጵያን ለማዳከም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክታለች። ሦስት ሚሊየን አርሜኒያውያን እና አሽሩ ክርስቲያን ወገኖቻችንን የጨፈጨፈችው የአሁኗ ቱርክም የኢትዮጵያውያን ደም አሁንም ጠምጧታል፤ የግራኝ አሕመድን መዋረድ ለመበቀል ወደ ኢትዮጵያ እና አካባቢዋ በየዘመኑ ዘልቃ በመግባት አሉ የተባሉትን የኢትዮጵያ መሪዎች ለመግደል በቅታለች። ከመቶ ሠላሳ ዓመታት በፊት የሃገራቸውን ዳር ድንበር ከወራሪ ጠላት ለመከላከል፤ እንደ ተራ ወታደር በጀግንነት ተፋልመው መተማ ላይ አንገታቸውን ለቱርክ ወኪሎች ለድርቡሽ ሱዳናውያን የሰጡበት ድንቁን አፄ ዮሐንስ ንጉሠ ነገስት ዘኢትዮጵያን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።
ዛሬም ተመሳሳይ ነገር እየታየ ነው፤ በሱዳን፣ በሶማሊያና 'ኦሮሚያ' በተባለው ህገ-ወጥ ክልል የመሐምዳውያኑ ቱርኮች ቅጥረኞች ተነስተው በኢትዮጵያ ሃገራችን ላይ እንደገና ለመዝመት እየተዘጋጁ ነው። ለጊዜውም ቢሆን አሁን ሁኔታው በጣም አመቺ ሆኖላቸዋል፤ ዳግማዊ ግራኝ አሕመድን በዶ/ር አብዮት በኩል ለማምጣት ችለዋል፣ ልክ በግራኝ እና ጣልያን ወረራዎች ጊዜ እንደታየው በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ሊነሳ የሚችል እስላማዊ ሠራዊት በተለይ "ኦሮሚያ" እና "ሶማሊያ" (እግዚአብሔር ይይላችሁ በተለይ እነዚህ ሁለት ክልሎች እንዲመሠረቱ ፈቃዱን የሰጣችሁ) በተባሉት ክልሎች ወቅቱን እና ትዕዛዙን በመጠባበቅ ላይ ነው።
የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ ባለፉት ዓመታት
ከታሪክ ለመማር ፈቃደኞች ብንሆን ነው አሁን ለምንገኝበት አሳፋሪ ሁኔታ አንጋለጥም ነበር። ፍዬሎቹ ጠላቶቻችን እነማን እንደሆኑ አንዴም፣ ሁለቴም፣ ሦስቴም... በተደጋጋሚ ለማየት በቅተናል፤ ግን ከታሪክ ስለማንማር እንደ ቱርኮችና ዓረቦች ከመሳሰሉት ውዳቂዮች መጫወቻ ሆነናል።
በደርግ ጊዜ መንግስቱ ኃይለማርያም አሉ የሚባሉትንና ልምዱ ያላቸውን ጄነራሎችና የጦር መሪዎች በመረሸን አገሪቱን አድክሞ ስለነበር እንደ ሶማሊያ ያሉ እስከ ጂጂጋ ድረስ ሰተት ብለው ገቡ፤ በዚህ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን አጡ። ዛሬም የዶ/ር አብዮት አሕመድ መንግስት ልምዱ ያላቸውን የጦር መሪዎች በጴንጤዎችና ሙስሊሞች እየተካ የኢትዮጵያን ሠራዊት በማድከም ላይ ይገኛል። ቱርኮችና ዓረቦች በሶማሊያና ሱዳን በኩል በቅርቡ ለሚጀምሩት ወረራ ሕዝባችን ከመቼውም ጊዜ በከፋ ተጋልጦ ይገኛል። ሠራዊቱ ውስጥ የገቡት ጴንጤዎች መሳሪያዎቻቸውን እየወረወሩ ወደ ኬኒያ ያመልጣሉ እንጅ ለኢትዮጵያ ብለው አይሞቱም፥ ሙስሊሞቹም ለቱርክ፣ ዓረብና ግብጽ "ወንድሞቻቸው" ሲሉ ጡት ያጠባቻቸውን ኢትዮጵያን በመክዳት ከታሪካዊ ጠላቶቿ ጋር ተሰልፈው እንደሚወጓት 100% እርግጠኛ ሆኜ መናገር እደፍራለሁ። ባለፉት አንድ ሺህ ዓመታት ይህን በተደጋጋሚ አይተናል፤ ከሰማይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም!
ባለፈው ዓመት ቱርክ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሠላሳ አራት ሺህ በጎችን ለበዓል ሰጥታ ነበር፥ አስራ አምስት ሺህ ወደ አማርኛ የተተረጎሙ እርኩስ ቁርዓኖችን በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ አከፋፍላ ነበር። (መጀመሪያ በጉን፣ ቀጥሎ ቁርዓንን፣ ከዚያም ሜንጫውን) ይታየን፤ እኔ በአንካራ ከተማ መንገዶች ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ላከፋፍል ሲፈቀድልኝ! ክርስቲያኖች በሚረገጡባት ቱርክ ፈጽሞ የማይቻልና የሚያስገድል ተግባር ነው። የአገራችን በር ግን ለማንም ውዳቂ ክፍት ነው። በጣም ያስቆጣል! ወገን፤ ሰዓቱ ተቃርቧልና ለመጨረሻው ፍልሚያ እራስህን በሚገባ አዘጋጅ!
"... ናፖሊዮን ራሱን ትልቅ አድርጎ ያይ ይሆናል። እኔ ግን ዛሬም ታላቅ ነኝ። እሱ በቅርብ አመታት የተጎናጸፋቸው ድሎች ይሆናል ታላቅ ያደረጉት። የእኔ ግን ታላቅነት ከጥንት... የሚነሳ ታሪክ፤ ገናና ሀገር ያለኝ መሆኔን ሊያውቅ ይገባል።" [አፄ ቴዎድሮስ]
"... የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት፤ ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት። ሁለተኛ ክብርህ ናት። ሶስተኛም ሚስትህ ናት። አራተኛም ልጅህ ናት። አምስተኛም መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከታቲነት
እንዲህ መሆኑን አውቀህ ተነሳ።" [አፄ ዮሐንስ ፬ኛ]
"... እናንተ አንድ ልብ ከሆናችሁ፤ እናንተ በምቀኝነት እርስ በርሳችሁ ተዋግታችሁ ካላለቃችሁ በቀር አገራችንን ኢትዮጵያን ለሌላ ለባዕድ አትሰጧትም። ክፉም ነገር አገራችንን አያገኛትም። ነፋስ እንዳይገባባችሁ በያላችሁበት ሀገራችሁን በርትታችሁ ጠብቁ። ወንድሜ ወንድሜ የገነተ ተደጋገፉ።..." [ዳግማዊ አፄ ምኒልክ]
Blogger Comment
Facebook Comment