ሔሮንኤል ዘኢትዮጵያ)
ዛሬ ባገራችን እናቅላችሃለን የሚሉት አላዋቂዎች: በባዕድ አስተምህሮት/ አምልኮ የጨለማ ዕይታ ተማርከው : የብርሃንን ተስፋ ታውረው : ዘመናዊ ሆናችሁ ተብለው ተቀብለው : አጣጥመው ዉጠው ... ዉጥንቅጥ ዉስጥ ከተውናል ...
በባሌም ይሁን በቦሌ የጸረ ኢትዮጵያው የዘንዶው ሊቀ ካህናትና አገልጋይ ሆነዋል ...እኛ ኢትዮጵያዊያን : እንደ ሕዝብ : በባዕዳን ክፉና ከንቱ እሳቤ የዘንዶው አገልጋይ ከመሆን ይልቅ ... ወደ ቀደመው ታላቅነታችን ክብራችን ... ኃያልነታችን የሚያደርሰንን ኢትዮጵያዊ ጥበብ ላይ ጊዜያችንን ብናጠፋ : ጥፋታችን ይቀንሳል ... እኛም ከጥፋት እንድናለን::
ለማንኛውም :
እኛ ኢትዮጵያዊያን :
ዘንዶውን "ድል" አድራጊዎች :
ለሰው ልጅም : "ነፃነት" ን የምናውጅ :
መሆኑ ልንረዳ ይገባል ... እንደ መረዳታችን በኢትዮጵያዊነት መመላለስ ይጠበቅብናል::
እንደ ምሳሌ: በኢትዮጵያዊነት መረዳት ዕለት ተለት ስንመላለስ: ዘረኝነት ስንዋጋ : ዘንዶውን በኢትዮጵያ ጦር እየወጋነው የመሆኑን እውነት እንመነው እንወቀው : በደንብም ደጋግመን እንውጋው!
ስማችን:ኢትዮጵያዊያን + ስኬታችን:ኢትዮጵያ
+++++++ውበታችን : ኢትዮጵያዊነት::+++++++
Blogger Comment
Facebook Comment