ከ82 ዓመታት በፊት የተሰረቀው የአክሱም ሐውልት፡ ሐሙስ፡ ጥቅምት18 ቀን1930 ዓ.ም እ.አ.አ ጥቅምት 28 ቀን 1937 ፡ በፋሺስቱ የኢጣሊያ መሪ በቤኒቶ ሙሶሊኒ ተመርቆ ሮም ከተማ ላይ በይፋ ተተከለ። ሐውልቱ የቀድሞው የአፍሪቃ ሚንስቴር ዋና ሕንፃ፡ በኋላም ላይ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) ዋና መሥሪያ ቤት ከሆነው ህንፃ ፊት ለፊት እንዲቆም ተደረገ፤ (ልብ እንበል፤ ድርቅና ረሃብ ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ እንዲታወቁ ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራውን ጠነሰሱ)
- + የሮም ኦሎምፒክስ 10. September 1960ቅዳሜ, ጳጉሜ 5 / 1952 ዓ.ም (እንቁጣጣሽ ዋዜማ)
ቍ.11 ያረፈበትን ሸሚዝ ለብሶ የነበረው ጀግናው ኢትዮጵያዊ አበበ ቢቂላ ልክ የአክሱም ሐውልት ጋር ሲደርስ ጫማውን አውልቆ ጣለ፤ የኦሎምፒክ ማራቶንን አሸነፈ፤ ፋሺስቶችን አዋረዳቸው። ኢትዮጵያን የያዘ አሸናፊ ነው!
- ቍ. 11 ፥ September 11 New York / አዲስ ዮርክ ፥ አዲስ ዓመት ፥ አደ/ዲይ/ስ አበባ ፥ አበበ ቢቂላ ፥ አበባ በቀለ።
- + አክሱም/Axum ፥ ኒው ዮርክ/New YorkማክሰኞSeptember 11 / 2001 – መስከረም 1 / 1994 ዓ.ም ፥ እንቍጣጣሽ
ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ሁሉ በአክሱም የአወቃቀር ንድፍ ነው የሚሠሩት። በኒው ዮርክ ከተማ ተሠርተው የነበሩት መንትያዎቹ የአለም ንግድ ማዕከል ሕንፃዎች በመሀመዳውያኑ የሽብር ጥቃት ፈራረሱ። አክሱም በሳባውያን የግማሽ ጨረቃ አምላክ "አልማቃህ" ላይ + ነጎድጓድ / መብረቅ...በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።
- + የአክሱም ሐውልት በሮማ January 2001 – ጥር 1993 ዓ.ም
ኢጣልያ በዲያብሎሳዊ ቅጥፈትና በፈርኦናዊ ትዕቢት ሐውልቱ ይበላሻል፣ በመንገድ ላይ ሊፈራርስ ስለሚችል አልመልስም አለች።
- + July 18, 2001 – ረቡዕ, ሐምሌ 11 / 1993 ዓ.ም
የአክሱምን ሐውልት ለማስመለስ ኢትዮጵያ ጩኸቷን አሰማች፤ በኋላም ላይ በሮማው የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት(FAO) ዋና መሥሪያ ቤት በሆነው ህንፃ ረሃብን የተመለከተ ስብሰባ ላይ ተግኘትው የነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ኢጣሊያ ሐውልቱን ለኢትዮጵያ በፍጥነት እንድትመልስ ጥሪ አቀረቡ።
- + ሮማ 27 May 2002 – ሰኞ, ግንቦት 19 / 1994 ዓ.ም ፥ የቅዱስ ገብርኤል ዕለት
የአክሱም ሐውልት በመብረቅ ተመታ።
- + July 19, 2002 – ዓርብ, ሐምሌ 12 1994 ዓ.ም
የኢጣልያ መንግስት የአክሱምን ሐውልት ለመመለስ ተስማማ፤ “ኡ!ኡ! ሌላ ጣጣ ሳይመጣብን ኧረ ቶሎ ውሰዱልን!” አለ፡ በድንጋጤ፡ የወቅቱ የኢጣልያ ጠቅላይ ሚንስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ።
- + ማክሰኞ, April 19, 2005 – ሚያዝያ 11 / 1997 ዓ.ም
የአክሱም ሐውልት ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።
በነገራችን ላይ፡ "ጉግል" ገብታችሁ በአማርኛው "የአክሱም ሐውልት(በሁሉም 'ሐ'ዎች)ጻፉ፤ 16ሺህ ፣ "አክሱም" በሚለው ደግሞ 294ሺህ የፍለጋ ውጤቶች ብቻ ይገኛሉ፤ አዎ! ስለ አክሱም እና ስለ አክሱም ሐውልት...ዋው! በላቲኑ ግን "The Obelisk of Axum” 107ሺህ ወይንም በ ”Axum“ 3ሚሊየን የፍለጋ ውጤቶች ይወጣሉ... አስገራሚ ነገር ነው!
Blogger Comment
Facebook Comment