ሆላንድ | የጥቁሯን “ኢትዮጵያዊት” ማርያም ቅዱስ ሥዕልን በጥቁሮች መፈክር አበላሹት

..አ በ1656 .ም በፖላንድ ላይ ተቃጥቶ የነበረውን የስዊድኖች የጥቃት ወረራ በጥቁሯ ማርያም እርዳታ ሲከሽፍ የፖላንድ ንጉሥ ካዚሚሬስ ጥቁሯን እመቤታችንን የፖላንድ ንግሥት እንድትሆን ወሰነ። ብልሕ ንጉሥ!
..አ በ1944 .ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ክፉኛ የደቀቁት (1/5ኛው ሕዝቧ፤ 6ሚሊየን ፖላንዳውያን አልቀዋልፖላንዳውያኑ የጥቁሯን/ኢትዮጵያዊቷን እመቤታችንን ስዕል ተሸክመው እስከ ኔዘርላንድስ/ሆላንድ ድርሰ ዘልቀው በመግባት ተንቀሳቃሽ ምስል ወድምጹ ላይ የምትታየውን የብሬዳ ከተማን ነፃ ለማውጣት በቅተዋል። ድንቅ ተዓምር!
ጥቁሯ ማርያም (Black Madonna of Czestochowa) ..አ በ1944 .ም የኔዘርላንድሷን(ሆላንድ) ከተማ ብሬዳን ከናዚዎች ነፃ ላወጧት የፖላን ወታደሮች በ1954 .ም የተሠራ መታሰቢያ ላይ ሰሞኑን በመላው ዓለም በመካሄድ ካለው ከፀረ-ዘረኝነት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ያልታወቁ ሰዎች "BLM“ ( Black Lives Matter – BLM የጥቁርም ሕይወት ይገባዋል” በሚል ትልቅ ጽሑፍ ለማበላሸት ደፍረዋል። ትልቅ ቅሌት!
ለመሆኑ የጥቁሯ ማርያም ስዕልን የሚቃወም የጥቁሮች እንቅስቃሴ አለ እንዴይህን ጽንፈኛ ተግባር ሊፈጸም የሚችለውስ በማን ይሆንበኮሙኒስቶችበፌሚኒስቶችበግብረ-ሰዶማውያንበመመዳውያን?። ሁሉም የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸውን አያደርጉትም አይባሉም።
እንቅስቃሴው ቀስ በቀስ በዘረኞች፣ በኮሙኒስቶች፣ በግብረ-ሰዶማውያን እና በአዛብ እይተጠለፈ ነው። የጥቁር ሕዝቦች ለነፃነትና ህይወት የሚያደርጉትን ትግል ሁሌ የሚጠልፉት እነዚህ ቡድኖች ናቸው። ለዚህ ነው ጥቁሮች ተገቢውን የነፃነት ዒላማ ከመምታት መንገድ ላይ የሚቀሩት። በሃገራችንም ተመሳሳይ ክስተት ይታያል፤ የኢትዮጵያ ብሔርተኛውን አጀንዳ ዘውገኞቹ ኦሮሞዎችና አዛብ በሁሉም መስክ ጠልፈው እየወሰዱት ነው።
አሁን አጋጣሚውን በመጠቀም ግራኞች፣ ኮሙኒስቶች፣ ፌሚንስቶች እና ሰዶማውያን ከመመድ አርበኞች ጋር በማበር በዓብያተ ክርስቲያናት ላይ በመላው አውሮፓ እና አሜሪካ ጥቃት በመፈጸም ላይ ናቸው። አጋንንት የተለቀቁበት ዘመን ላይ ነንና ግድ የለም እራሳቸውን እንዲህ ያጋልጡ፣ ይታዩን፤ ጊዚያቸው በጣም አጭር ነው!
ለማንኛውም እንደ ፖላንድ፣ ሩሲያ፣ ሩማኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ስፔይን ወዘተ ላሉ አውሮፓውያን ሃገራት እኛ ኢትዮጵያውያን በድንቁርናችን ነጭ የቆዳ ቀለም እና ሰማያዊ ዓይኖች እያለበስን ያመጣናት ጥቁሯኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ማርያም በታሪካቸው በጣም ብዙ የሆኑ ተዓምራትንና ድሎችን አሳይታቸዋለች።
በተለይ በምስራቅ አውሮፓ በኮሙኒዝም እና ኦቶማን ቱርክ ዘመን አስከፊ ልምዱ ላቸው ምስራቅ አውሮፓውያን በጥቁሯ/ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ማርያም ጉዳይ ምንም ድርድር የለም። በዘመነ ኮሮና በእነዚህ አገራት ከተሞች ጎዳናዎች ላይ በእጣን ታጅበው እንዲወጡ የተደረጉት የእናታችን የጥቁሯ ማርያም ስዕላት ናቸው። 
ዝነኛው የፖላንድ ጥቁሯ ማርያም (Black Madonna of Czestochowaቅዱስ ሥዕል
ሥዕል ጽሑፍ
አስገራሚ የሆነው የቼስቶኮቫ ጥቁር ቅድስት ድንግል ማርያም አይከን/ሥዕል/ጽሑፍ ቅዱስ ሐዋርያው እና ወንጌላዊ ሉቃስ ከሣላቸው/ከጻፋቸው ሰባ ቅዱሳት ሥዕላት/ጽሑፎች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታመናል
ሮማውያን በ 66 .ከተማዋን ድል ባደረጉበት ጊዜ ምስሉ ከኢየሩሳሌም ተወስዶ ነበር እናም ፔላ አቅራቢያ ባለ ዋሻ ውስጥ ተደብቆ ነበር ስዕሉ ለቅድስት ሔለን (..ግንቦት 21/ 326 .ቅድስት አገር ስትጎበኝ ተሰጣት፤ ከዚያም ቅድስት ሔለን ወደ ቁስጥንጥንያ አመጣችው።
ይህ ተዓምረኛ ሥዕል ከስምንተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በመላው አውሮፓ በኦሮቶዶክሳውያን እና ካቶሊኮች ዘንድ ብዙ ተዓምራትን ካሳየ በኋላ ከአስራ አራተኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ያስና ጎራቺስታኮቫ በተባለው የፖላንድ አውራጃ ይገኛል። ድንቅ ተዓምራት የሚታዩበት ይህ ቦታ በብዙ ጎብኞዎች ይዘወተራል። አረመኔው አዶልፍ ሂትለር ያስና ጎራቺስታኮቫን ለጎብኝዎች ዝግ እንዲሆን አድርጎ ነበር።
እኛስ ይህን እያየን እመቤታችንን አላግባብ ፈረንጅ ስናደርጋት ሊያሳስበንና ሊያሳፍረን አይገባምን?
ሮማውያኑ "እየሱሳውያን"፤ የጌታችን እና ቅዱሳኑ መልአክቱ ስዕላትንና ኃውልቶችን በነጮች ምሳሌ እንደሚስሏቸውና እንደሚሠሯቸው "ጥቁሯን" / ኢትዮጵያዊቷንማርያምንም በተንኮል ነጭ አድርገው በመሳል ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውን ስንቶቻችን ነን የምናውቀው?
አሁን ኢትዮጵያውያን ወደ ጥንታውያኑ እና እውነተኞቹ የእመቤታችን ስዕላት መመለስ ይኖርብናል። ቤተ ክሕነትና ማሕበራቱ እንዲሁም ግለሰቦች ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት መስጠት አለባቸው። በዚህ ላይ ቁጥጥር የሚያደርግ አካል መኖር አለበት። ይህ በቸልታ የሚታለፍ ቀላል ነገር እንዳይመስለን። ይህን አስመልክቶ ኢትዮጵያውያን ልሂቃን ብዙ ሥራዎችን መስራት ይጠበቅብናል።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment