ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
"ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ።" ማር 7:6-7
አባቶች አውሬውን ፈርተውታልን? ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ሕብረት አለው? ወይስ ብርሃኑ በጨለማ ተሸንፏል?
"በጉልበቴ ተንበርክኬ ከምኖር በእግሮቼ ቆሜ ብሞት ይሻለኛል" የሚል የጀግኖች መርሆ አለ። አባቶቻችን እነ አቡነ ጴጥሮስ፣ እነ አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ለሰማእትነት የበቁት ለዚህ መርሆ ስለቆሙ ነበር። የዘመኑ አንዳንድ አባቶች ግን በፈርዖናዊ እብሪት ለስጋቸው እየኖሩ ነው።
የተዋሕዶ ልጆች እየታረዱና ሴት ልጆቻቸው ታግተው በጠፉበት፣ ዓብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ ፣ ታቦታት ላይ ድንጋይ እየተወረወሩ ባሉበትና የጃንሜዳ ጥምቀተ ባሕር በተወረሰበት እንዲሁም ሰንደቃችን ከቤተ ክርስቲያን እንዲወርድ በተደረገበት በዚህ ዘመን ከዚህ ሁሉ ወንጀል ፈጻሚዎች ጋር በቤተ ሉሲፈር ጸሎት ለማድረስ ደፍረዋል። ለማን ይሆን ጸሎቱን ያደረሱት? የጠፉት ልጆቻችን የት አሉ በማለት መንግስት ተብዬውን መወትወት፣ ማፋጠጥና ማስጠንቀቅ የሚገባቸው አባቶች እንዴት የወሮበሎች ታዛዦች ሊሆኑ በቁ? ምን እየነካቸው ነው? ለአቴቴ መተት እራሳቸውን አጋልጠው ይሆን? ወይንስ የሚደብቁት ሌላ ነገር አለ? መቼስ ከጣዖት አምላኪዎች ጋር በአንድነት እየጸለዩ፡ ልክ አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ለመስዋዕት ለማቅረብ መወሰኑን ከእግዚአብሔር ሌላ ማንም እንዳያውቅበት እንዳደረገው ዓይነት ድበቃ ሊሆን አይችልም።
ዓለምን ሁሉ መምራት የምትችል፣ ለመላው ዓለም መመሪያ መስጠት ብቃት ያላት ይህች ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የሦስተኛ ደረጃ ቧልተኛ ፖለቲከኞችን፣ ዶክተሮችንና ጋዜጠኞችን ምክር መቀበል ይኖርባታልን? እናገለግላታለን የሚሉት አባቶች ምነው ይህን የአውሬ መንግስት "በክርስቶስ ስም ሂድ! የምን ዛፍ ተከላ! የምን እጅ መታጠብ! የምን ገንዘብ ስብሰባ! ጥፋ፤ ዲያብሎስ!በቃ! በአምላካችን ሙሉ እምነት አለን፣ መዳን በክርስቶስ ብቻ ነው፣ ከግብር ልጆችህ ጋር አብረን አንሰራም፣ ትንኮላውን ከቀጠሉበት ጦርነት ውስጥ እንገባለን፣ ከእኛ ራቅ! ከጨለማ ጋር ህብረት የለንም፣ አሕዛብና መናፍቃን ወደ መድኃኔ ዓለም እስካልተመለሱ ድረስ መቅሰፍቱ እየከፋ ይመጣልና አብረን ልንጸልይ አይገባንም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ነው!" በማለት የነብዩ ዳንኤል እና ሠለስቱ ደቂቅ ዓይነት ድፍረት ማሳየት ያቃታቸው? ችግራቸው ምንድን ነው?
"በገሊላ ባህር ማዶ በቤተሳይዳ ዓሳ አጥማጅ ነበር፤ ሰውን ታጠምዳለህ ብሎ ጌታ ጠራው ተከተለው። ዓለምን ዞረው ለማስተማር ዕጣ ሲያወጡ ለቅዱስ እንድርያስ ልዳ ደረሰችው፤ ልዳ ማለት የቅዱስ ጊዮርጊስ አገር ናት፤ ሊአስተምር ወደዚያች አገር ገባ፤ ጣኦት አምላኪዎች ወሬውን ሰምተው ሊጣሉት ሾተል ይዘው ወጡ፤ ሐዋርያው እንድርያስ ግን ከፍ ካለ ቦታ ላይ ቆሞ እንዲህ ሲል ሰበከ፦
"የአህዛብ ጣኦታት የሰው እጅ ስራ ናቸው ዓይን አላቸው አያዩም፤...ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፤ እጅ አላቸው አይዳስሱም፤ እግር አላቸው አይሄዱም በጉሮሮአቸውም አይናገሩም የሚሰሯቸው የሚያምኑባቸው ሁሉ እንደ እነርሱ ይሆናሉ፤ መዳን በእግዚአብሔር ነው እርሱም እየሱስ ክርስቶስ ንው" እያለ ሰበከ። ቃሉ ጣዕም ከአንደበቱ ቅልጥፍና ከነገሩ ማማር የተነሳ የወገባቸው ትጥቅ ተፈታ ሾተላቸውን ጣሉ፤ በጌታችን አምነው ተጠመቁ።" ይላል።
የኛዎቹስ?
"ጸሎቱ ለሀገር ሲባል ነው፣ ችግሩን በአንድነት ለመዋጋት ነው" ይሉናል ያለማፈር። በመጀመሪያ ችግሩን ማን አምጥቶት? ከማን ጋርስ ነው ህብረቱና አንድነቱ? በሲዖል ጭካ እያቦኩ የሚንጫጩትም እኮ በጨለማው ውስጥ አንድነት አላቸው! አንድነት ከሲዖል ያወጣቸዋልን? ስንዴው ከእንክርዳዱ፣ በጉ ከፍዬሎች የመለየት ጥሩ ዕድል በተሰጠበት በዚህ ዘመን ከክርስቶስ ተቃዋሚዎች ጋር አንድነት ለመፍጠር የሚሹ እነማን ናቸው?መልሶ ተመላልሶ ጭቃ ውስጥ? ለየትኛዋስ ሀገር? ለትናንትናዋ፣ ለዛሬዋ እና ለነገዋ ኢትዮጵያ ከሆነ በቂና ድንቅ የሆነ የራሳችን ቦታ አለንኮ፤ ቤተ ክርስቲያን፣ የጸሎት ቤት የሚባል ፣ መንፈስን የሚያድስና ለሁሉም ክፍት የሆነ።
የቤተ ክርስቲያን ጠላት መሆኑን ባስመሰከረው በቤተ ሉሲፈር (ቤተ መንግስት)ተገኝቶ ኢትዮጵያን ከሚያጎድፉ እና ክርስቶስ አምላኳን ከካዱ የዲያብሎስ የግብር ልጆች ጋር የሚደረገው "ጸሎትስ" በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ይኖረዋልን? በፍጹም! እዚያ የሄዳችሁት አንድም ወንበራችሁን ለማዳን(የአንዳንዶቹ "አባቶች" ወንበር የእነ "ቢል ጌትስን" ወንበር ያስንቃል) ብሎም ለገዳዩ መንግስትና ለጣዖቱ ዋቄዮ-አላህ እውቅናን ለመስጠት ነው። ድግሞ እኮ፡ "ሁሉም በየእምነቱ ይጸልይ!" ይላሉ። ይህን ዓረፍተ ነገር ከአንድ "የተዋሕዶ ልጅ ነኝ" ይገርማል፣ ያንገፈግፈኛል። መሐመዳውያኑ እና መናፍቃኑ ለዲያብሎስ እንደሚጸልዩ የሚጠራጠር የክርስቶስ ልጅ ይኖራል ብዬ አላስብም ፤ ታዲያ "ለሀገራችን ሰላምና በጎነት እኛ ለእግዚአብሔር አምላክ እንጸለይ ፣ እናንተ ደግሞ ለዲያብሎስ አምላካችሁ ጸልዮ!" የሚለው ምን የሚሉት አነጋገር ነው? እንዴት ነው ሰው ማስተዋል የተሳነው? ኢትዮጵያችን እዚህ ሁሉ መቀመቅ ውስጥ የገባችው መሐመዳውያኑ እና መናፍቃኑ ምድሯን ከረገጡበት ዕለት አንስቶ መሆኑን እንዴት መገንዘብ አቃታቸው? ለምንድን ነው እጅና እግሮች የተሰጡት፣ አእምሮ ያለው አንድ ሰው የራሱን የቤት ሥራ ከታሪክ እየተማረ በአግባቡ የማይሠራው? ለምንድን ነው ችግሩን ሁሉ በራሱ ዘመን ለማስወገድ እንደመትጋት በስንፍና "እግዚአብሔር ያውቃል!"እያለ ነገሮችን ሁሉ ለመጭው ትውልድና ለልጆቹ የሚያሸጋግረው? ለምንድን ነው እግዚአብሔርን የሚፈታተነው? ማንንስ እያታለለ ነው?
ቤተ ክርስቲያን በዚህ ከባድና ውስብስብ ዘመን የዕጣን ፈውስን፣ ጸሎቱንና ጸበሉን ለተቀረው ዓለም በነጻ በማበርከት ላይ እያለች እንኳን ሰው ከከንቱ ዓለማውያኑ በገንዘብ የሚገኘውን የኪኒን ቆሎ እየቃመ እንዲመረዝ አልያም የ666ቱን ክትባት ተስፋ አድርጎ መኖር እንደሚገባው ሌተ ተቀን ሲወተውቱት እና ሊያሳምኑት ሲሞክሩ ይታያሉ። መገናኛ ብዙኅን ወዮላችሁ! ልጆቻችሁን የምታስከትቡ ወላጆች ወዮላችሁ! የሚገርመው፤ "በኢትዮጵያ የተመረተ ተዓምረኛ መድኃኒት ተገኘ!" አሉ ቶሎ ብለው፡ ሰውን ከቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከዕጣኑ እና ጸበሉ ለማራቅ። መላው ዓለም ወደራሱ ተመልሶ የመድኃኔ ዓለምን ፈውስ ለማግኘት በሚሯሯጥበት በዚህ የፈተና ዘመን የኛዎቹ ጉደኞች ዜጎች በተስፋ-ቢስነትና በድንጋጤ ለፈረንጆች ሳይንስ የሙከራ አይጠ-መጎጥ እንዲሆኑ ተግተው በመሥራት ላይ ናቸው። ይህ ታዲያ ኃላፊነት የጎደለው ወንጀል አይደለምን?ምን ዓይነት መርገም ቢሆን ነው!?
አንድ እንግሊዛዊ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፦ "ኢትዮጵያውያን እግዚአብሔር አላቸው፤ በኪሳቸው ይዘውታል፣ ግን እርሱን ከኪሳቸው ለማውጣት ያመነታሉ"
አዎ! አባቶች በጎቻቸውን ከተኩላዎች የማዳን ግዴታቸውን ረስተው በጎቻቸውንን እየበሉባቸው ያሉትን ተኩላዎችን በመቀለብ ላይ ናቸው። አባታችን አባ ዘ-ወንጌል "ከመቶ አሥሩ ብቻ ናቸው ድነው የኢትዮጵያን ትንሣኤ የሚያዩት" ሲሉን ትክክል ናቸው። ይህ ብቻ መሆኑ ያሳዝናል ግን ምን ይደረግ፡ ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ ወዮላቸው የሚያስቱትም!
Blogger Comment
Facebook Comment