ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ግራኝ ዐቢይ አሕመድ ፡ ሰውዬው ሰምተናቸው አይተናቸው ለማናውቃቸው ጭካኔ የተሞላባቸው ተግባራት ብቁና ዝግጁ ነው፤ መንግስቱ ኃይለማርያም ስጋን ብቻ ነው ሲገድል የነበረው ፤ ይህኛው ግን ነፍስንም እያሸተተ ለመግደል ነው የሚሻው፤ ሰውዬው በሰሜን ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች ላይ ሔሮድሳዊ የሆነና በቅናት መንፈስ የሚነዳ እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥላቻ ነው ያለው። በዚህ አትጠራጠሩ! የኢትዮጵያዊውን ወንድ ወኔ ለመስበር ልጃገረድ ተማሪዎችን ያግታል/ይገድላል ፥ የተዋሕዶ አማኙን ቅምስ ለመስበር ደግሞ ካህናትንና መነኮሳትን ይገድላል፤ አብያተ ክርስቲያናትን ያዘጋል።
ይህ አውሬ በዐምሓራ እና ትግሬ ኢትዮጵያውያን መካከል መተላለቅ የሚፈጥርለትን ክብሪት ሳይጭር እንቅልፍ የለውም። ለዚህም አስፈላጊውን ድጋፍ በራያ ኦሮሞዎች መንፈስ ውስጥ ከሚገኘው ህወሓት እያገኘ ይመስላል። ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጽም ሁሉም ጸጥ ማለታቸው ብዙ የሚነግረን ነገር አለ። እውነት ጄነራል ሰዓረን የገደላቸው ግራኝ ዐቢይ አሕመድ እንደሆነ የሚያጠራጥር አይደለም፤ ግን ብቻውን፤ ያለ ደብረ ጽዮን ፈቃድ ግድያውን ፈጽሞታልን? እስካሁን በምናየው የእነ ስብሐት እጅም አለበት። ምክኒያቱም አንድ እንደ ህወሓት የታጠቀ ቡድን አንድ ከፍተኛ ጄነራሉ ሲገደልብት ዝም አይልም፤ ወዲያው ነበር የሚበቀለው፤ እነ በረከትም ታሥራው ዝም፣ ደጋፊ ጋዜጠኞቻቸውም ታግተው፤ ዝም። አብረው ባይሠሩ አብዮት ሁለት ዓመት አይደለም አንድ ወር ሥልጣን ላይ አይቆይም ነበር።
ልክ ስልጣን ላይ እንደወጡ ሉሲፈራውያኑ የሰጧቸውን የኢትዮጵያ ካርታ ያለምንም ማመንታት በመቀበል ትልልቆቹን የኢትዮጵያ ግዛቶች የኢትዮጵያ ጠላቶች ለሆኑት ለኦሮሞዎችና ሶማሌዎች ሰጧቸው። ይህ አልበቃ ብሎ ለ27 ዓመታት ያህል በአላሙዲን በኩል ከሳውዲ ዓረቢያ የተገኘውን ገንዘብ ለኦሮሞ ባንኮች፣ ዋስትና ኩባንያዎች፣ ሰፋፊ እርሻዎች፣ ባሕል ማዕከላት ወዘተ በማስረከብ በዐምሓራ ላይ እያሴሩ እንደ ባርያ ሲያገለግሏቸው ከቆዩ በኋላ መጨረሻ ላይ ስልጣኑን አስረክበው ፈረጠጡ። ከሁሉ ወንጀል የሚከፋው ይህ ነው! የዐምሓራ ልሂቃኑም ተመሳሳይ ስህተት እየሠሩ ነበር፤ ዛሬም እየሠሩ ነው። ለሀገር የሚያስብ አንድ ቡድን ወይም ግለሰብ ለአንድ ሀገር-ወዳድ ቡድን ወይም ግለሰብ ስልጣኑን በማስረከብ በሚቀጥለው የተሻለ ሆኖ ለመቅረብ ይሞክራል። እነዚህ ግን "ከኔ የተሻለ መምጣት የለበትም" ፣ "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" በሚል ድንቁርና ዜጎችን አላግባብ ያሰቃያሉ። መቼ ይሆን ደገኞቹ የሰሜን ሰዎች ከአቴቴ እስር ቤት ነፃ ወጥተው ሕዝባቸውን ከጦርነት፣ ከረሃብና በሽታ የሚያድኑት?
እስኪ ሰሞኑን በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ እየታየና ኡ!ኡ! ከሚያሰኝ የዘርኝነትና የጥላቻ ዘመቻ ትንሽ ተምረው ይህን ያህል የሚጠሏቸው ሉሲፈራውያኑ ከሰጧቸው የመቶ ዓመት አጀንዳ ፎቀቅ ይበሉ። "ጎረቤትህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ" እንጅ ቃሉ የሚለው "የጎረቤቴ ጠላት ወዳጄ ነው" አይደለምና የሚለው ዛሬውኑ የጋራ ጠላታችንን መቀለቡን ያቁሙ።። ለሉሲፈራውያኑ የጎሳ ክፍፍላችንን ተጠቅመው የሚፈልጉት ዓላማ ላይ ከደረሱ በኋላ ሁላችንም "ኔግሮዎች" እያሉ መጥፎ ስም በመስጠት ሊጨርሱን እንደሚፈልጉ ነው የምናየው።
በጣም ያሳዝናል፤ መላው ዓለም በኮሮና ጉዳይ ትንፋሹን ይዟል እነዚህ አልማር-ባይ የዲያብሎስ የግብር ልጆች ግን በጎንደር፣ በቤኒ ሻንጉል፣ በአዲስ አበባ፣ በላሊበላ እና በዋልድባ የሽብርተኝነት ዘመቻቸውን አጧጥፈዋል። በዚህ የወረርሽኝ ጊዜ አረመኔዎች የሚባሉት የአፍጋኒስታን ታሊባኖች እና አይኤስ እንኳን "ሰልጥነው" ሰይፋቸውን ለማስቀመጥ ወስነዋል። የዋቄዮ-አላህ ልጆች ግን መነኮሳትን ይገድላሉ፣ ወጣቶችን ያድናሉ፣ እናቶችን ያፈናቅላሉ። በናይጄሪያም ፉላኒ የተባሉት ወራሪ ወንድሞቻቸው ተመሳሳይ ድርጊት እየፈጸሙ ነው፤ ትናንት በወጣው መረጃ ሃምሳ የሚጠጉ ክርስቲያኖች በጎራዴ እየተቆራረጡ ተገድለዋል።
አባትችን አባ ዘ-ወንጌል እንደነገሩን በአህዛብ የከፋ ጉዳት ከሚደርስባቸው ገዳማት መካከል ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ጉንድ ተክለሃይማኖት፣ አክሱም ጽዮን፣ ደብረ ሊባኖስና አሰቦት ሥላሴ ይይገኙበታል። ገዳማውያኑ የሰማዕትነት አክሊል እየተቀበሉ እንደሆኑ ያው እያየነው ነው።
እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በምህረት ተቀብሎ ከቅዱሳን ኅብረት ይደምርልን! አሜን!
Blogger Comment
Facebook Comment