የዓለም ፈውስ ኢትዮጵያ - አሜሪካ በዕጣን አጠነች!


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፥፲፮]
እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።”
እግዚአብሔር እኛ ኢትዮጵያውያንን በመላው ዓለም በስደትም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ከአገራችን አውጥቶ የሚልከን በርገር እየበላን በከንቱ እንድናውደለድል ሳይሆን እንደዚህ እጣኑን እያጨስን መንፈሳዊ ውጊያውን እንድንመራለት፣ ከጠፉት ጋር አብረን እንድንጠፋ ሳይሆን፣ ሁሉም እንዲድን መድኃኒቱን እንድናሳይ ነው። በእውነት ነው የምለው፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በከንቱ ሌላውን ለመምሰል ብንታገልም ምናልባት 90% መንፈሳውያን ሰዎች ነን።
እንግዲህ ያውልሽ አሜሪካ፤ ግብጻውያን አውሮፕላን አብርረው ከሰማይጠቀስ ፎቆችሽ ጋር በማላተም ሦስት ሺህ ዜጎችሽን ገደሉብሽ፣ ፕሬዝደንትሽ ለጉብኝት ወደ ግብጽ ሲመጡ በንቀት ጫማቸውን ወረወሩባቸውዛሬ የከዳሻቸው ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች ግን መቅሰፍቱ ሁሉ ከምድርሽ እንዲርቅ ክቡር እጣኑን ከደመናው ጋር አዋሐዱልሽ። ይህን ውለታ አትርሺ፤ አሜሪካ!
የፃድቁ አባታችን አቡነ ሃብተማርያም ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን የመጣውን መቅሰፍት ከአገራቸን ኢትዬጵያና ከመላው ዓለም ይሰውርልን!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment