ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እድገታቸው በ "ተሽከርካሪ" ላይ መሠረት እንደማድረጉ ፣ የፍልስፍናዊ፣ ርዕዮት ዓለማዊ ፣ ማሕበረሰባዊ፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎቻቸው ሁሉ በፈላስፋው ጆርግ ሄግል ጽንሰ–ሃሳብ ላይ፤ ሁሉም ነገር፦
ችግር – እርምጃ – መፍትሔ
ወረርሽኙን በአየር ላይ ይበትናሉ ፤(ከጥያራ፣ ሳተላይት፣ ማይክሮዌቭ የሞባይል አንቴናዎች (3G, 4G,5G) "ኡ! ኡ!"
ተራራቁ፣ አትሰባሰቡ፣ ዝጉ" የሚሉ መግለጫዎችን በየቀኑ ይሰጣሉ ፤ ከዚያም "በቃ መድኃኒት ተግኝቷል ይህን ኪኒን ውሰዱ፣ ይህን መርፌ ተወጉ" ይላሉ።
አብዮት አህመድ "ቤተ ክርስቲያናትን እናዘጋለን!" አለ፤ ተብሏል። ለብልግና ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳዎችን ለማካሄድ የሚሰበስብ ሰው፣ ብር ለማሰበሰብ ሺህ ሰዎችን በአዳራሽ ውስጥ የሚያጉር አስመሳይ ሰው አሁን ለምዕመናን ደህነነት አስቦ? ፣ "ዐምሓራና ትግራዋይ" የተባሉት ኢትዮጵያውያን እርስበርስ እንዲተላለቁ ሌት ተቀን የሚያውጠነጥን መሰሪ ግለሰብ የኢትዮጵያውያን ሕይወት አሳስቦት? ልጅ! እንደ ግብረ– ሰዶማዊው ግብረ–አበሩ ኢማኑኤል ማክሮን በፈረንሳይ በየሳምንቱ ሲካሄዱ የነበሩት ዓይነት ተቃውሞዎች ከማየትና ከመስማት አረፍ ይላል። አሁን ፖሊሶችን ወደ ቤተ ክርስቲያን በመላክ ምዕመናን በመግደል ቤተ ክርስቲያንን ማደናገጥና ማሸማቀቅ አያስፈልገውም፤ "ህገ መንግስቱ ቤተ ክርስቲያን እንድናዘጋ ያዘናል" ማለት ይደፍራልና። "እናንተን ብቻ አይደለም፣ ያው መስጊድንም አዘግቻለሁ" ይለናል። መስጊድ? እስልምና ኢ–አማኒያዊ የክርስቶስ ተቃዋሚ አምልኮ ነው፤ ክርስትና እስከተወገደለት ድረስ ሌላው ነገር ሁሉ ግድ የለውም፤ ሌላ ምንም የሚያጣው ነገር የለም።
የክርስቶስ ተቃዋሚው ጥልቅ የምድር ውስጥ ዋሻዎቹ ውስጥ በሚገኙት የምርምር ላብራቶሪዎች ውስጥ እንደ ኮሮና የመሳሰሉትን አጋንንት ማምረት ጀምሯል። ገና ከዘጠኝ ዓመት በፊት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ማስተዋወቃቸው ነበር ማለት ነው።
ለማንኛውም ይህን ቫይረስ የፈጠሩ ሉሲፈራውያን ተቀዳሚ ዒላማቸው የኢትዮጵያ ርትዕት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት። በየትኛውም የዓለማችን ሀገር እንደ ኢትዮጵያ ዜጎች ለእምነታቸው በብዛት የሚሰባሰቡባት ሀገር የለችም። በየቤተ ክርስቲያኑ በየገዳማቱ ለቅዳሴ፣ ጸበል ለመጠመቅና በዓላትን ለማክበር እንደ ኢትዮጵያ በዝተው የሚሰባሰቡባት የዓለማችን ክፍለ ሀገር የለችም። ምዕመናን በየቤተ ክርስቲያናቱ ሲሰባሰቡ የሚፈነጥቀውን ኃይል (Vibration) በቴክኖሎጂያቸው ሆነ በሌላ መልክ ደርሰውበታል፣ ከገዳማቱ የሚወጣውን ከፍተኛ ኃይል በትሪሊየን ፒክሰል/ ነጠብጣቦች ቁልጭ አድርገው የማንሳት ብቃት ባላቸው ሳተላይቶቻቸውና ቴሌስኮፖቻቸው ለማየት በቅተዋል።
ስለዚህ ሉሲፈራዊውን የአንድ ዓለም መንግስት (One World Order) ለመመስረት እንቅፋት የሆነችባቸውን ጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማጥፋት እንደሚኖርባቸው አምነዋል። ዋናው ዓላማቸው ክርስቲያኑ ከቤተ ክርስቲያን እንዲርቅና ተሰባስቦ እንዳይጸልይ፣ እንዳይባረክ፣ በጸበል እንዳይድን ነው።
አሁን እንደ ዱሮው ፋብሪካዎችን፣ ሱቆችና መጠጥ ቤቶችን አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት አቅራቢያ ሄደው መስራት አያስፈልጋቸውም ፤ ወረርሽኙን ተደብቀው አየር ላይ መርጨት የሚችሉበት ጊዜ ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment