ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
መንፈሳዊ ወኔያቸው ተወዳዳሪ ባልነበረው በቀደሙት አባቶቻችን መስዋዕት ነፃነቷንና ማንነቷን ጠብቃ ለአምስት ሺህ ዓመታት የቆየችው ሀገራችን ኢትዮጵያ እውነት ዛሬ ሉዓላዊ ግዛት ናትን?የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስት ቴለርሰን ህወሓት መንግስቱን ለኦሮሞዎች አስረክባ ወደ መቐለ እንድትሄድ አዘዟት፤ ዛሬ ደግሞ የጣልያን ዝርያ ያላቸው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ ኢትዮጵያ ዓባይን ለግብጽ እንድትሰጥ፣ ግራኝ ዐቢይ አሕመድደግሞ እስረኞችን እንዲፈታ ትዕዛዝ ሰጥተው ሳውዲ ገቡ። እንዴት ነው፤ እግዚአብሔር በሰጠን ግዛት እኮ ማንኛውም ምድራዊ ኃይል "እንዲህ አድርጉ! አሊያ...” ብሎ ሊያዘን አይችልም። ሥልጣን ላይ የተቀመጡት ወንበዴዎች እኮ በታሪክ ተወዳዳሪ የሌለውን የክህደት ተግባር እየፈጸሙ ነው። ላለፉት 150 ዓመታት ከተፈጸሙት በመዋዕለ ሕፃናት ደረጃ የሚፈጸሙ ስህተቶች እንዴት መማር አቃተን?
እስኪ ተመልከቱ፦
ጠላቶቻችን መላዋን ኢትዮጵያን እንደ በሬ ቅርጫ ከዳር እስከ ዳር እየተከፋፈሏት ኢትዮጵያውያን ግን አትኩሮታቸውን፣ ጊዚያቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ገንዘባቸውን መጀመሪያ "በትንሿ" አዲስ አበባ ላይ ብቻ ከዚያም በአንድ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ ላይ፣ ቀጥሎም የክርስቲያኖች ደም በፈሰሰባት አንዲት ለአንድ በሬ የግጦሽ ቦታ እንኳን የማትበቃ ቦታ ላይ ብቻ እንዲያውሏቸው ኋላ-ቀር የሆነ ዲያብሎሳዊ ተንኮል ተጠቀሙ። በበታችነት ስሜት የተሞሉት ጉረኞቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች፤ "እንኳን ኢትዮጵያን መላዋ አፍሪቃን መምራት እንችላለን!” የሚል ከንቱ መፈክር በማሰማት ልክ በሬ ለመሆን ብላ ሰውነቷን ስትነፋ በመጨረሻ ፈንድታ እንደ ሞተችው እንቁራሪት በመነፋፋት ላይ ናቸው ፤ መንደርተኛ እንዲሆን የተደረገውና የተዳከመው ኢትዮጵያዊው ግን ለቁራጭ ቦታ እንኳን ከጠላቶቹ ፈቃድ እንዲሰጠው ደጅ በመጽናት ላይ ይገኛል። እግዚአብሔር በሰጠው ሃገር!
የኢትዮጵያ ርትዕት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመንግስት በላይ ናት፤ ስለዚህ በክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተችው ይህች ሐዋርያዊትና ርትዕት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፡ በቀራንዮ የፈሰሰው የጌታችን ደም አቅጣጫውን እንደጠቆማት፣ መንፈስ ቅዱስ እንደመራት በየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት፤ ከደቡብ ግብጽ እስከ ሞቃዲሾ ቤተ ክርስቲያን የመሥራት ሙሉ መብት አላትና የማንንም ፈቃድ መጠየቅ የለባትም። በ22/24 ስህተት የተፈጸመው፤ ልክ ቤተ መንግስት ቤተ ክርስቲያኑን ሲያፈርስና ሰማዕታቱ ወንደሞቻችንም በአብይ አህመድና ታከል ዑማ ትዕዛዝ ሲገደሉ ሕዝቡ ዶማና አካፋ፣ ሲሚንቶና ጡብ ይዞ ወደቦታው በማምራት የቤተ ክርስቲያን ህንጻ ግንባታውን ወዲያው መጀመር ነበረበት። አምስት ሚሊየን የአዲስ አበባ የተዋሕዶ ልጅ ወደዚያ ቢያመራ የትኛው ምድራዊ መንግስት ነው
ሊመክተው የሚደፍረው?!
ይህ አሁን መታየት የጀመረው የመንግስት መለሳለስ የተለመደው እባባዊ መለሳለስ ነው።
ምክኒያቱም፦
1ኛ. እንዲለሳለስ ትዕዛዙ የመጣው ከአሜሪካ ነው።
2ኛ. ኢንጂነር ስመኘውን፣ ጄነራሎቹንና ክርስቲያኖቹን የገደላቸው፣ እህቶቻችንን ያገታቸው/የገደላቸው
እርሱ መሆኑን እስራኤልና አሜሪካ በማወቃቸው "ይሄን ካላደረግክ፤ ዋ!” እያሉ ስላስፈራሩት ነው።
3ኛ. ሰሜናውያኑ/ ደገኞቹ የተዋሕዶ ልጆች "በመጭው የይስሙላ ምርጫ" እንደማይመርጡት ስላወቀ በመደናገጡ ነው።
ስለዚህ፤ ወገን ኧረ በቃህ! ኧረ አትታለል!ኧረ ከእባብ እንቁላል የዶሮ ጫጩት አትጠብቅ! ይህ መንግስት ስልጣኑን ሳይወድ በግድ አስረክቦ ለፍርድ እስካለቀረበ ድረስ ወደኋላ አትበል!ፍላጎቱንና ዕቅዱን ነግሮሃል፣ ተግባሩና ዓላማውም ቁልጭ ብለው እየታዩ ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment