[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፯፡፰]
❝ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።❞
ለበጎ ነገር ያድርገውና ዶ/ር ዶ/ር ቴዎድሮስ ገና እንደተመረጡ ❝ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖምን የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ አርገው መሾማቸው በተለይ በኢትዮጵያውያን ላይ ያዘጋጁት ተንኮል ስላለ ነው።❞ ማለቴ ያለምክኒያት አይደለም።
ዲያብሎስ እላይ ከፍ አድርጎ ያወጣህና አሽቀንጥሮ ወደ ታች ይወረውርሃል። ታዋቂ፣ ዝነኛ፣ ሃብታም፣ ተሸላሚ ያደርግህና ጊዜህ ሲደርስ የለመደውን የደም ግብሩን “አምጣ!” ብሎ ይደፋሃል።
፳፬ /24 ቁጥር ያረፈበትን ማልያ ለብሶ ሲጫወት የነበረው ዝነኛው ጥቁር አሜሪካዊ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቤ ብራያንት እና ሴት ልጁ ከወር በፊት ልክ በዚህ ዕለት በፈረንጆቹ 01/26/2020 ዓ.ም በሄሊኮፕተር አደጋ ተከስክሰው ለሉሲፈር ኢሉሚናቲዎች ተሰውተዋል።
አሁንማ የሚደብቁት ነገር የለም፤ ሃሳባቸውንና ዕቅዳቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልክ፣ ወደውም ሆነ ሳይወዱም፣ አውቀውም ሆነ ሳያውቁም ሁሉንም ነገር በቅደም ተከተሉ እያሳዩን ነው።
"ትንቢት?”
👉 ከአራት ዓመታት በፊት፡ እ.አ.አ በ 2016 ዓ.ም ላይ ኮቤ ብራያንት በሄሊኮፕተር ሲከሰከስ የሚያሳይ የካርቱን ፊልም “ኮሜዲ ሲንትራል” በተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዲተላለፍ ተደረገ።
👉 እ.አ.አ. ጃንዋሪ 25 / 2020 ላይ ኮቤ ተከስክሶ ሊሞት አንድ ቀን ሲቀረው ሌቦርን ጀምስ የተሰኘው የሎስ ኤንገልስ ሌከርስ የቅርጫት ኳስ ኮከብ የኮቤ ብራያንትን የቅርጫት ኳስ ሬከርድ ሰበረው።
👉 በበነገታው እ.አ.አ ጃንዋሪ 26 / 2020 ዓ.ም ላይ ዝነኛው የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ኮቤ ብርያንት፣ ሴት ልጁና ሌሎች ስምንት ሰዎችን ጨምሮ በካሊፎርኒያ ሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
👉 ኮቤና ልጁ በሞቱበት በዚሁ ዕለት ቻይና በተቀሰቀሰው ኮሮና ቫይረስ 41 ሰዎች መሞታችውና 1300 ሰዎች
መታመማቸው ታወቀ። በዚሁ ዕለት ኮቤ 41 ዓመቱ ልጁም የ13 ዓመት ልጃገረድ ነበሩ።
👉ባለፈው ሳምንት በቺካጎ ከተማ በተካሄደውና ለኮቤ መታሰቢያ እንዲሆን የተደረገው የሁሉም-ኮከብ የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ላይ ድጋፍ ሰጭ /ስፖንሰር የነበረው ኩባንያ የሜክሲኮው ቢራ አምራች “ኮሮና / Corona ነበር”
👉 በዚሁ ሰሞን የኮሮና ቢራ ምናልባት ከቫይረሱ ጋር ይገናኝ ይሆናል በሚል ፍራቻ ብዙ ሰዎች ጉግል ላይ
“የኮሮና ቢራ ቫይረስ” የሚለውን ቃል ይፈልጋሉ።
👉 ባለፈው ሳምንት ላይ ኮቤ ብራያንት እና ልጁ CORONA del mar / ኮሮና ዴል ማር በሚባለው የካሊፎርኒያ መንደር ተቀበሩ።
በዕብራይስጥ ቋንቋ ኮቪድ/covid ኮቤ/cobe ይባላል
"ኮሮና" የሚለው የቫይረስ ስም፡ በግዕዝ ፊደል ቁጥር፡ ከ= 50፤ ረ= 6፤ ነ= 30፤ ድምር= 86 ይሆናል። ይህ 86 ቁጥር ደግሞ፡ ትናንት በስልክ ካወራነው፡ "ዘር" ከሚለው የ86 ቁጥር ጋር ተመሳሳይ ነው። ይህም፡ በዐብይ አሕመድ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ንፁሓን ዜጎች ላይ ከተፈጸመው የ"ዘር/86" ማጥፋት ምሥጢር ጋር በቀመር እኩል ነው።
ዮሐንስ በራዕዩ፡ ንጉሡ ሄሮድስ የገደላቸውን ሕፃናት ቁጥር ድምር፡ የ"አዳም" ዘር ናቸውና "ኢየሱስ" የሚለውን 144 የስም ቁጥር በሺ አብዝቶ፡144ሺ ናቸው ብሎ በአሥራ ሁለቱ የዕብራውያን ብሔሮች ቁጥር ልክ ዘርዝሮ እንደገለጸው ማለት ነው።
👉 ሌላው፦ ኮቤ ብራያንት ሊከሰከስ አስር ቀን ሲቀረው በ ኮቤ (ጃፓን) በ እ.አ.አ በጃንውሪ 16/17 /1995 ዓ.ም ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ 7ሺ ሰዎች ሞቱ። ባለፈው ወር በ 01.16/17.20 ላይ 25ኛው ዓመት(ኢዮቤልዮ)ታስቦ ውሎ ነበር።
ባለፈው ዓመት በዚሁ በሎስ ኤንጀልስ የተገደለውና የሀበሻ ዝርያ የነበረበት ራፐር “Nipsey Hussle / ኒፕሲ ሃስል”ም እንዲሁ ለዲያብሎስ የደም ግብር እንዲከፍል ነበር የተደረገው። በተለይ አንድ ኢትዮጵያዊ ከገደለው ሌላው ራፐር “Snoop Dog/ ስኑፕ ዶግ” እና በዘጠናዎቹ አጋማሽ ላይ ከተገደለው ከሌላው ራፐር “Tupac Shakur/ቱፓክ ሻኩር“ ጋር በመንፈስ የተያያዘ አስገራሚ ጉዳይ ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment