ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ስለ አሁኑ መሪዎቻችን እና ስለ እጣፈንታቸው


እንግዲህ መሪዎቻችን ልታውቁት ይገባል፡፡ ያላችሁት በኢትዮጵያ ! እየገዛችሁ ያላችሁት በኢትዮጵያ ያለውን ህዝብ ነው፡፡ ይህ ህዝብ ደግሞ አናውቅም በምትሉት በእግዚአብሔር የሚገዛ የተወደደ የተመረጠ ህዝብ ነው፡፡ የመረጣትን ያጸደቃትን እምነት ተወህዶን ለብዙ ሺ ዘመን ሕይወቴ ብሎ ተሸክሞ የመጣ ሕዝብ ነው፡፡
ለማታውቁት እግዚአብሔር ማንነቱን በቤቱ የቅናት ቁጣ ሊያሳውቃቸው የወሰነ ስለሆነ ልትዘጋጁበት ይገባል፡፡ ጠመንጃና ታንክ ይመጣል ብላችሁ አትገሠሉ ያ የለም ፡፡ ከጠመንጀው ሁሉ የሚከፋው ሁሉን ከንቱ የሚያደርገው የእግዚአብሔር እሳት እዚያው አጠገባችሁ አለ፡፡ ስለሆነም ይህ የአፈጻጸም ውሳኔ ለህዝብ መበተን ሲጀምር ለእግዚአብሔር የብርሃን ተዋጊ መላእክቶች የልዑል እግዚአብሔር ትዕዛዝ ፈጻሚዎች አብሮ ይደርሳል፡፤ስለሆነም እግዚአብሔር ማንነቱን ካሰወቃችሁ በኋላ እንነጋገራለን ማለት ነው፡፡
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment