ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን በዉጪ ስላሉ ኢትዮጵያዉያን!!


በዉጪ በስደት ያላችሁ ወገኖቻችን አገራችሁን እየወደዳችሁ በችግር የሄዳችሁ የችግር ምልክት የሆነዉን ዜግነታችሁን ያልጣላችሁ ያልለወጣችሁ የፈጣሪዬና የምዩ ልጆች ጊዜዉ ስለመሸ እራሳችሁን እንደ ሎጥ ከሰዶም ከተማ ለማስመለጥ ከፈጣሪአችሁ ጋር በብርቱ ተነጋገሩ፤ እመቤቴን ጠይቁ፤ ጊዜም አታጥፉ! አጥፊዉ በመላዉ አለም በሁሉም ስፍራ ታዞ በደጅ ቆሞአልና!!

የአገራችሁ ትንሳኤ እነሆ እንደ ፀሀይ ሊያበራ ነዉ፡፡ የምዩ ልጆች እውነተኛ ተዋህዶ ኦርቶዶክሶች አይዞአችህ አምላካችሁደርሶአል፡፡ በደጅም ቆሞአል ራሳችሁን አዘጋጁ ጊዜ የለም! አትዘናጉ ተፈጽሞአል፡፡
በሌላ አኩአያ ኢትዮጵያዊ የነበርክ ኢትዮጵያዊነትህን የናቅህ ዜግነትህን የለወጥህ ለፍርፋሪ የሸጥህ ብኩርናውን ለምስር ወጥ እንደ ሸጠዉ ኤሳዉ ክብርህንና ብኩርናህን ለለወጥህ ምንዝርናን የለመድህ ከአህያ የዋለች ጊደር ፈስ ትማራለች እንደተባለ ምንዝርናን፣ ዉሸትን፣ ንቀትን፣ስስትን፣የተማርክ ተዋህዶ እምነትህን ንቀህ ከፈረንጅና ከአረብ እምነት የቃረምክና የተቀበልክ፣ መንገድህ ያድንህ፣ ያመንክበት ይከልልህ ለካቶሊኩም፣ ለፕሮቴስታንቱም፣ ለእስላሙም፣ ለሂንዱም፣ ለቡዲሂዝሙም ተከታይ ሁሉ የሚጠብቀው ሁሉ ላንተም ይጠብቅሃል ተዝጋጅተህ ጠብቅ!!

ህዝቅኤል ምእ ፡ 14 ፡ 12 – 20 ዘጸአት ምእ ፡ 12 ፡ 21 - 28
ኢሳኢያስ ምእ ፡ 40 ፡ 6 - 8 ኢሳኢያስ ምእ ፡ 57 ፡ 11 – 13
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment