ኢትዮጵያ አሁንም በንጉሳዊ መንግስት ስር

✍ አየነው ገብረመስቀል

የንጉሱን ስርዓት ገርስሰነዋለ ከእንግድሀ አፈር አራግፎ አይነሳም ሃይማኖት የሌለው መንግሰት መመስረት ችለናል እየተባለ ጀብዱ ይወራል፡፡እንደሚታወቀው ሃገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን የመንግስት አስተዳደር የነበራት ጥንታዊት ሃገር መሆኗ ይታወቃል ከቀዳማዊ ሚኒልክ እንኳን ብንጀምር እንደነገርኳችሁ አባቱ ጠቢቡ ሰለሞን ሶስቱን ልጆቹን በይሁዳ፤በሮም እና በአክሱም ካነገሰ በኋላ ሃገራችን ኢትዮጵያ ለዳዊት የተገባለት ቃልኪዳን ምንም ሳይጓደል ከ3000 አመታት በላይ በንጉሳዊ አስተዳደር ኖራለች፡፡ስዩመ እግዚያብሄር ሆኖ ንጉሱ በንጉሳዊ አስተዳደር መኖፘም ቤተ መንግስቱ ብቻ ሳይሆን ቤተ ክህነቱም ጭምር የመሪነት ሚናውን በመወጣት መልካም አስተዳደር እንድሰፍን፤ስርዓት አልበኝነት እንዳይኖር  እንድሁም የሁሉ ፈጣሪ የሆነውን የእግዚያብሄርን ቃል ለትውልዱ እንድተላለፍ እግዚያብሄርም እንድመሰገንና እንድመለክ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሲያደርግ ኖፘል፡፡በዚህም ህዝቡ እግዚያብሄርን በማምለኩና በማመስገኑ የሰላም ባለቤት እጌዚያብሄር በምድር ላይ በግዛታቸው ሰላም፤ጥጋብና ደስታ አብዝቶላቸው በፍቅርና በመዋደድ የተለያዩ ነገዶች ሆነው ሳለ እንደ አንድ ነገድ ሆነው ለረጅም ዘመናት መኖርቸው ይታወቃል፡፡ይህ መሆኑም አሁን ላይ ያሉት ብሄር፤ብሄረሰቦች ድሮም መኖራቸውና እንደ አሁኑ ያለ የመጠላላት፤መገዳደል፤ረሃብ፤ቸነፈር፤አመፅና ክህደት አለመኖሩ የድሮው ንጉሳዊ አስተዳደር በፈጣሪ ፈቃድ ምንኛ ጠቅሞን እንደነበር አመላካች ጉዳይ ነው፡፡       
ሀገራችን ኢትዮጵያ የካም ዘር ናት ብለን ከምናውቀው አጠቃላይ እውቀት በላይ በተለያየ ጊዜ ከካምም ሆነ ከሴም ዘር ከመካከለኛው ምስራቅ እየመጡ ለሰው ልጅ መኖሪያ ምቹ ወደሆነችው ወደዚች ሃገር በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ ሆነው መግባታቸው በታሪክ ይታወቃል፡፡እንደውም ሃገሪቱን መጥተው ሰልለው ሂደው ሚሰቶቻቸውን ይዘው መጥተው በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ልጅና መንደር መስርተው ቢኖሩም ልጆቻቸው፤አባታቸውን ጫካ ወለደው እስኪባሉ ድረስ በተለያየ ጫካ ውስጥ እየመነጠሩ መኖራቸው ይታወሳል፡፡የሆነ ሆኖ ግን የሰው ልጅ በተለያየ የአለም ክፍል መበታተናቸው አድስ ቋንቋ፤ከለር፤ባህል፤ሃይማኖት….ወዘተ መፍጠራቸው አይቀሬ ነው፡፡ቢሆንም ግን የሁላችንም የዘር ግንድ አንዱ አዳም እንጅ 100 አዳም አልነበረም፡፡ሲጀመርስ የሰው መለኪያው ሰውነትን(ስብአዊነትን) እና በስላሴ ፈቃድ የሚኖር መሆኑን እንጅ ዘራችን ለምን ይሆናል፡፡

አዳም መልኩ ያማረ ዉብ በአምላኩ አርዓያ የተፈጠረ፤የክብሬ ወራሽ ተብሎ የሚጠራ ክቡር ፍጡር ነው፡፡ታዲያ እግዚያብሄር ያከበረውን እኛ ስለምን እንገፋዋለን፡፡በእርግጥ የሰው ልጅ ከስህተት የሚፀዳ የለም፡፡አባታችን አዳምም ገነትን የሚያክል ቦታ ስላሴን የሚያክል ጌታ በሰይጣን የተሸረበ ሴራ አምላክነቱን ሽቶ ከዚያች ምድር ወርዶ ተዋርዶ ወደዚች ምድር ወይም የደይንና የመከራ ቦታ ተጣለ፡፡አምላክነትን የሚወድ ሞክሮም ያልተሳካለት ድያብሎስም በደካማው የአዳም ውድቀትና ከአምላኩ መጣላት እጅግ አድርጎ ተደሰተ፡፡የአዳምን ሃዘን ወደጎን እንተወውና የሁሉ ፈጣሪ ቅድስት ስላሴም በአዳም ክህደት እጅግ አዘነበት፡፡ለወዳጆቹ ለመላእክትም አማከራቸው፡፡ንዑድ ሚካኤልን ጨምሮ ብዙወቹ ክቡራን መላእክት የአዳምን መሬታዊነት ተረዱለት፡፡በድርሳን እንዳነበብነው ቅዱስ ገብርኤል ሁሌ የአዳም ሀዘን ያሳዝነው ነበር፡፡የፍጥረት ሁሉ እመቤት የአለም መሰረት ማሪያምን ያበስራት ዘንድ አለውና፡፡ወደቀደመ ነገሬ ልመለስና ባልሳሳት በመፅኃፈ አክሲማሮስ እንደተዘገበ እጅግ ጥቂት የሚሆኑት መላእክቶች ቁጥራቸውም በመፅሃፈ ሄኖክ እንደተገለፀው ግን በልዑል ፊት ትምክተኝነታቸው እስኪታይ ድረስ ከልዑል ዘንድ ስላባታችን አዳም ተከራከሩ፡፡አዛኝ ይቅር ባይ ጌታም ባሪያየ አዳም እኮ የካደው ደካማ ፤መሬታዊ በመሆኑ ነው፡፡እናንተ ግን የመሬታዊነትን ባህሪ አልሰጠኋችሁም እናም አትፍረዱበት ቢላቸው፤ለአዳም የተሰጠው ፀጋ ከመላእክት ይበልጥ ነበርና እኛ በእውነቱ ለአዳም የሰጠኸውን ፀጋና የተገለፀበትን አካል ከነ መራቢያው(ፆታ) ብትሰጠንና ብትፈትነን አንክድህም አሉት፡፡ሁሉን ቻይ አዶናይም እንደፈቃዳቸው ለአዳም የሰጠውን ሁሉ ለነሱም ሰጣቸው፡፡ለአዳም የተሰጠው ፆታዊ አካልና ባህሪ እንድሁ ለእነሱም ካላቸው ላይ ጨመረላቸው፡፡ነገር ግን ልዑልን ይክዱት ዘንድ ፈቀቅ አሉ ከሴት ልጆችም ጋር አመነዘሩ ረጃጅም ረዋትንም ወለዱ፡፡ መጨረሻቸውም እነሱም ለዘላለም በጨለማ ተዘጉ ልጆቻቸውም በንፍር ዉሃ ጠፉ፡፡ጥብቅ ግን ፍትሃዊ እርምጃ የሚወስድ ንፁሃ ባህርይ እግዚያብሄርም የሁሉንም ጥፋት ያለ ቅጣት አልተዋቸውም፡፡የሰው ልጅ ነገስታቶቻቸው በስልጣን ጣዖት በማምለክ፤ህዝብና አህዛቡ በአምልኮ ምንዝር፤ህግ በማፍረስ፤በግብረ ሰዶምነት፤በጥንቆላ፤ነፍስ በመግደል በእግዚያብሄር ላይ ያላመፁበት ጊዜ ይኖር ይሆን?በሙሴ ዘመን ወይስ በኤልያስ ዘመን፤በኤሳያስ ዘመን ወይስ በኤልሳ ዘመን፤በዳዊት ዘመን ወይስ በሰለሞን ዘመን………ነገር ግን እንደቸርነቱ እስኪወለድ ድረስ ደርሶ አሻራውን፤ ዱካውን ትቶልናል እንከተለው ዘንድ የኛ ምርጫ ነበር፡፡ግን ምን ያደርጋል አዳም በቃሉ ብቻ ካደ እኛ ግን በቃላችንም በደማችንም ነፍሳችን ለአጋንንት ሸጥን፡፡አኛ ፈሪሃ እግዚያብሄር የለን ልጆቻችን እሱን አያውቁ፤እስኪ በዚህ ዘመን የማያስጠነቁል ማን ነው?እስኪ በዚህ ዘመን ሳያጭበረብር የሚከብር ነጋዴ ማን ነው፤እስኪ በዚህ ዘመን ቀኑን ሙሉ ሳይዋሽ የሚውል ማን ነው?እስኪ በዚህ ዘመን ቀንም ሌትም በልቡ እንደ ዳዊት እግዚያብሄርን ሲያስብና ሲያመሰገን የሚውል ማን ነው?በዚህ ዘመን ሰው ሁሉ ድያብሎስ ጋር ተፈራረሟል፡፡የተከፈለለትንም ውድ ዋጋ አቃሏል፡፡ሆኖም ግን እግዚያብሄር እንዴ እናንተ ስላልሆነና ፍርድም ሁሉ ስልጣንም ሁሉ የራሱ ስለሆነ የጠላችሁትን ንጉሳዊ አስተዳደር ለልጅ ልጅ ጭምር የሚተርፈውን ስርዓት በድጋሚ ለቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ እና ለአለም ህዝብ በቅርቡ ይመሰርታል፡፡
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment