የጠበብቶችና የፖለቲከኞች ሚና በእግዚያብሄር ቁጣ ላይ

March 6 2019
✍ አየነው ገብረመስቀል

ያለና የሚኖር አምላክ እግዚያብሄር ህዝቡ ንስሀ እንድገባ ባስቀመው የጊዜ ገደብ ውስጥ ንስሀ ባለመግባቱ የቁጣውን መቅሰፍትና ለምልክት እንድሆናቸው ከቅርብ ጊዜ እንኳን ብንነሳ ከሀምሌ 5 2008 ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ጊዜና ቦታ ከታናናሽ ጥፋቶች ጀምሮ ዘግናኝ የሆኑ ቁጣዎችን አይተናል፡፡በመሆኑም ህዝቡ፤ጠበብቶችና ፖለቲከኞች ንስሀ ከመግባት ይልቅ በጥበባቸው ለመፍታት በየመድረኩ የተለያዩ ህጎችን በማውጣት የእግዚያብሄርን አላማ ለማሰናከልና ችግሩም እንድቀረፍ በስጋዊ ደማዊ አስተሳሰባቸው ሲታገሉ ኖረዋል፡፡በመሆኑም አንድም መሬት ላይ ጠብ የሚል መፍትሄ ሳያመጡ እንደውም የእግዚያብሄር ቁጣ የከፋ እየሆነ መጥቷል፡፡ይህ የምሁራኖች መፍትሄ (ስራ)፤ የሚቃጠልን ቤት በልብስ በመሸፈን ወደ ሌላኛው ቤት እንዳይዛመት ያደረጉት ትግል ሳይሣካ እንደውም ቃጠሎውን እያባባሰው መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ነገር ግን እኔን የሚያሳዝነኝ የንስሃ ባላባት የሆነ የዳዊት ልጆች፤የጴጥሮስ ልጆች፤የጳውሎስ ልጆች የሰለሞን ልጆች የሆኑ፡ እና ነን ብለው የሚያስቡ ሁሉ የእምየ የኢትዮጵያ ልጆች ለምን ንስሀ ገብተው የእነሱን ስራ እንደማይሰሩ ነው፡፡የአብርሃም ልጆች ነን የምንል ነገር ግን የአብርሃምን ስራ የማንሰራ አስመሳዮች!ህዝቦቿም አመፁ ጠቢባኖቿም ተግሳፄን ተቃወሙ ተብሎ ወደፊት በታሪክ የሚፃፍብን ይመስለኛል፡፡ዛሬ አለም በተፈጥሮ አደጋ ማለትም በመሬት መንቀጥቀጥ፤እሳተ ገሞራ፤በጎርፍ፤በማእበል፤በበረሃማነት፤በተለያዩ አይነት ነፋሳት፤እንድሁም ሰው ሰራሽ በሆኑ አደጋዎች ህዝብ በህዝብ ላይ መነሳት፤ሃገር በሃገር ላይ መነሳት፤ረሃብ፤ጦርነት፤መጠላላት፤ክህደት፤አመፅ፤ጣዎት ማምለክ፤666ን ማገልገልና እሱን የሃይልና የሀብት ምንጭ ማድረግ እንድሁም እሱን አምላክና የጥበባቸው ጌታ አድርገው መውሰድ…ወዘተ በምትናጥበት ሰዓት የትንቢቱና የተስፋው ቃል የበላይ ባለቤቶች እኛ ኢትዮጵያውያኖች እንደት የምጡ ምልክት አይገባንም?ገዳማውያን አባቶቻችን በየዘመኑ እየነገሩን እንደት ሊመጣ ያለውን መገመት ይሳነናል?እናንት ጎሰቋሎች ጠቢባን ሆይ የመለኮትን ቁጣ በጥበባችሁና በእውቀታችሁ ልታስቀሩት ይቻላችኋልን?የድያብሎስ ጉዳይ አስፈፃሚ የሆናችሁ የሃይማኖት አባቶች ሆይ በምድር ላይ አጋንንት ጋር ተፈራርማችሁ የልዑልን ዓላማ በማድበስበስ ልታስተጓጉሉት ወይስ አንድ ቀን ልታራዝሙት ትችላላችሁን?አይደለም ጊዜው ገና ነው እያላችሁ ትውልዱን ታደነዝዙት ዘንድ አይገባም፡፡ጊዜው አሁን ነው፡፡ሰዓቱም አሁን ነው፡፡ነገር ግን የክፉ ትንቢት ፈፃሚዎች የቀረቻቸው የመጨረሻዋ ጥንፋፊ ስራ ሰላላለቀች ነበር፡፡እነሱ አንዴ እንደ ይሁዳ የተሰጣቸው የቤት ስራ(ተልእኮ)ነበርና፡፡        
ወዮልሽ ቅፍርናሆም ወዮልሽ ኮራዚ የቁጣው ጢስ እንፋሎት ሊያጠፋሽ ተቃርቧልና፡፡አይ የኢትዮጵያ እናቶች ማህፀናችሁ ምኖቹን ጉዶች ወለደ! መናፍቅ ትወልዱ ዘንድ እንዴት አምላካችሁ ጠላችሁ? ለነፍሳችን እረፍት የሚሆኑንን ቅዱሳኖችን የሚዘልፉ ራሳቸውን የማያውቁ ሀቅለ ቢሶች ትወልዱ ዘንድ እንደት ልዑል አሰናበታችሁ? አምላካቸውን ደስ ያሰኙና የታመኑለት፡ድያብሎስን ያንበረከኩና ተስፋ ያስቆረጡ ብሩካንና ቅዱሳን የሆኑትን ይሳደቡ ዘንድ እንደት ደፈሩ? ወዮልሽ የኢትዮጵያ ህዝብ፤ወዮልሽ የአዳም ዘር ሁላችሁ ላትኖሩበት ነገር ይህ የእኔ ዘር ነው፤ይህ የእኔ ህንፃ ነው፤ይህ የእኔ ወገን ነው፤ይህ የእኔ ብሄር ነው፤ይህ የእኔ ሰፈር ልጅ ነው፤ይህ የእኔ ወገን ነው፤ይህ የእኔ ግዛት ነው እያላችሁ ርስ በእርሳችሁ ተበላላችሁ፤ተገዳደላችሁ፤ለአጋንንትም በራችሁን (ልባችሁን)ክፍት አድርጋችሁ ሰጣችሁ፡፡ አይ የሰው ዘር ሆይ እውነት እላችኋለሁ ይህን የምትጋደሉበትንና ለዘላለም የምትኖሩበት የመሰላችሁን ክልል፤ሃብት፤እውቀትና ጥበብ አትጠቀሙበትም አትኖሩበትምም፡፡ይችስ ምድር አላማውን ለሚፈፅሙና ለሚያስፈፅሙ ስርዓቱ ለተፋቸው፤ለተገፉትና ለተመረጡት ተላልፋ ተሰጠች፡፡የእናንተ እጣፈንታችሁ ርስታችሁም በምድር ሰይፍ፤ረሃብ፤በሽታ፤ሞት፤ቸነፈር፤በሰማይም ድቅድቅ የእሳት ባህር(ሲኦል)ነው፡፡አሁን ተቧድናችሁ የምትጋደሉበት ምድር የእናንተ አይደለም፡፡ለምን ትደክማላችሁ፤አትድከሙ የእናንተ ምድር፤ክልል፤ጎጥ፤ሃገር፤አህጉር አይደለም፡፡የሌሎች የተመረጡትና የተገፉት ስርዓቱ የተፋቸው ነች፡፡ለእናንተ ግን አባታችሁ ድያብሎስ መዋኛ የእሳት ገንዳ አዘጋጅቶላችኋል፡፡በመፅሃፍ ጎተራውን ለቅልቆ ነፍሴ ሆይ እንደፈለግሽ ብይ ሲል ዛሬ መላከ ሞት ነፍስህን በዚች ሌሊት ካንተ ይወሰዳታል እንዳለው፡፡አሁንም ይህ በሁሉ ላይ በሞት የተሾመው መላከ ሞት ነፍሳችሁን ከእናንተ ይፈልጋታል፡፡እጅግ እንኳን ቢበዛ ከሁለት አመት የማይበልጥ ጊዜ ነው ያላችሁ፡፡ለእኔ እና ለእናንተ የሚያለቅስልን አጣን!ወየሁ እኔ በዚህ ዘመን መፈጠሬ፤ወየሁ ለእኔ በሀፅያት ላደፍኩት!እናንተ ጠቢባን ሁላችሁ ወዮላችሁ፤እናንተ በአግባቡ ያላገለገላችሁ የቤተ ክህነት ሰዎች ወዮላችሁ፤እናንተ ነገስታት ወዮላችሁ፤እናንተ በንጉሱና በካህኑ አዳም ስልጣን የተሾማችሁ ሴቶች ወዮላችሁ፤እናንተ ወንዶችን የምታማልሉ የኢትዮጵያ ቆነጃጅት ወዮላችሁ መላከ እግዚያብሄር እንደ ጤፍ ሊያጭዳችሁ ተዘጋችቷልና የምትለብሱት ሱሪ የምትለብሱት አጭር ቁምጣ የሆነ ለስም ቀሚስ ስርዓት የሌላችሁ መረን አጉራ ዘለል ሴቶች ሆይ ጊዜያችሁ ተከደነ፤ለከንፈራችሁ እሳትን ቀባችሁት ኃላ በሲኦል በዉሃ ጥም እንድህ ይሆናልና፤የሃጥያተኛን ቅባት አልቀባም እንዳለ አባቴ ዳዊት ፀጉራችሁን የቀባችሁ ሴትም ሆናችሁ ወንድ ወጣትም ሆነ ሽማግሌ ዎዮላችሁ፤አምላክ በሰጣችሁ ፀጉር ላይ ሌላ የጨመራችሁ ቆነጃጅቶች ሆይ ለእናንተስ ቀሳፊው ፈጠነሳ?የአለም መሰረት ማሪያም ጠላቶች መናፍቃን ሆይ የእናንተ መቅሰፍት ከሁሉም እንደሚብስ ህያው እግዚያብሄር ምስክሬ ነው፤እናንት የምንፍቅና እሾህን በሃገሬ የዘራችሁ ካቶሊኮች ሆይ ወዮላችሁ፤እናንተ ሰው ገለን እንፀድቃለን የምትሉ እስላሞች ሆይ ወዮላችሁ፤እናንተ የልዑልን ተግሳፅ የናቃችሁ ህዝብና አህዛብ ሁላችሁ ወዮላችሁ፡፡ጊዜያችሁ ተከደነ ዘመናችሁም ተፈፀመ፡፡የተሰጣችሁ የንስሃ ጊዜ ተጠናቀቀ፡፡ለሁሉ ፈጣሪ ለስላሴ የምትንበረከኩበት ጊዜ አጣችሁን?እናንት የምድር ጠቢባን ሆይ የወደቁት ከእናንተ በላይ ጠቢባን ሊሆኑ ነው፡፡የእናንተ ጥበብ መኪና መስራት፤ፈራሽ ህንፃ መስራት፤አውሮፕላን መስራት፤እፅዋትን፡እንሰሳትንና የሰውን ልጅ የሚገድል መሳሪያ መስራት ነው እናንተ የምታውቁት፡፡አእምሮ ቀሊላን ሁሉ፤የልዑልስ ጠቢባኖች በምድርም በሰማይም እውቀትና ጥበብ ተሰጣቸው፡፡ባለ አእምሮም ተባሉ፡፡እናንት ነገስታቶች ስልጣናችሁ ተነጥቆ ለልዑል ባለሟሎች ተሰጠ፡፡ወንበራችሁ ተገለበጠ፡፡እናንተ የሃይማኖት መሪዎች ሆይ የአንዱን የሁሉን ፈጣሪ የስላሴን ሃይማኖት ክዳችሁ፤ንቃችሁና አቃላችሁ እንደ አሸን የበዛ ሃይማኖታችሁን ይዛችሁ ከአምላካችሁ ከድያብሎስ ጋር ሲኦልን ልትሞሏት ነው፡፡መፅሀፋችሁ፤የሀሰት ነቢያቶቻችሁና ነገስታቶቻችሁ ከእናንተ ጋ ናቸው፡፡ሁላችሁም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ውጭ ያላችሁ ሃይማኖቶች ዋና ዋናዎቹ የድያብሎስ መመሸጊያዎች እስልምና፤ፕሮቴስታንት፤ካቶሊክን ሌሎች በብዙ ሽህ የምትቆጠሩ ድርጅቶች ሁላችሁም ትደመሰሳላችሁ፤ትጠረጋላችሁ፡፡አንድት መንግስት፤አንድት ሃይማኖት፤አንድት አገዛዝ በአለም ላይ ትኖራለች፡፡በቅዱስ ሳልሳዊ ቴዎድሮስ የሚመራው መንፈሳዊ የሆኑት  የክርስቶስ ወታደሮች የአለምን መንበረ ስልጣን ይቆጣጠራሉ፡፡በቅፅበት ወደ ስልጣን ያለምንም የጦር መሳሪያ በመንፈሳዊ መሳሪያ ብቻ ታግዘው ስልጣኑን ይጨብጣሉ፡፡በዚህም የመጀመሪያው ፍርድ በድያብሎስ ላይ ይሆናል፡፡       

ይህም ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ከመምጣቱ በፊት የሚደረግ በአጋንንትና ሰራዊቱ ላይ የሚደረግ ፍርድ ነው፡፡

የተፈጥሮ ሃይላትን በመጠቀም አመፀኞች ያረከሷትን ምድር ያፀዳሉ፤ለዚህም ቅዱሱ የተፈጥሮ ሃይላት ይታዘዙለታል፡፡እንደ ኤልያስ ከሰማይ እሳት ማውረድ፡እንደ ኃያሉ ጊዮርጊስ ምድርን አፍሽን ከፍተሸ እነኝህን አማፅያን የድያብሎስ ሎሌዎች ዋጫቸው ቢላት ትታዘዝለታለች፤ከ12ቱ የነፋስ መዛግብት 4ቱ የምህረት ቢሆኑም ከ8ቱ የጥፋት የነፋስ መዛግብት አንዱን ቢያዘው የዚች ምድር ጠበብቶች የሰሩትን ህንፃ ነቅሎ እንደ ጉም አብኖ እንደ ጭስ አትኖ ወደሰማይ ይውጣ ወደ ምድር ሳይታወቅ አሻራውን ጭምር ያጠፋዋል፡፡አሁን በምድራችን የሚታዩት አሜሪካንና ቀሪው የአለም ሃገራት አስቸግሮናል የሚሉት ጥቅል አውሎ ነፋስም ሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ለምልክት እንጅ ገና አልጀመረም፡፡ውሃንም ቢያዘው በሰው ደምና በድያብሎስ እገዛ የተገነቡ የአለም ከተሞች ከነ ጥበባቸው፤የምርምር መሳሪያቸው፤ከነ ህንፃዎቻቸው እንዳልነበረ ያደርግለታል፡፡ይህ ቅዱስ በውስጡ የተዋሃደው መድህን ክርስቶስ (ስጋየን ብትበሉ ደሜንም ብትጠጡ እኔ በናንተ እኖራለሁ፤እናንተም በኔ ትኖራላችሁ ብሏል)በመሆኑ ስራውንም የሚሰራው ራሱ አምላካችን ስለሆነ ቴዎድሮስን እንደ ማይክ ወይም እንደ ዉሃ ቧንቧ ይጠቀመዋል ማለት ነው፡፡ምክንያቱም ሰው በራሱ ምንም መስራት የማይችል ደካማ ፍጥረት ነው፡፡ነገር ግን በአምላኩ ሲታመን ከምንም ተነስቶ አለምን ይገዛል፡፡በእኔ ብታምኑ እኔ እምሰራውን ትሰራላችሁ ብሏልና፡፡አዎ ሰው የመንፈስ ማደሪያ ነው ብቻውን ይኖር ዘንድ የማይችል ፤ እንደ ነጭ ወረቀት ሁሉን የሚቀበል፤ ሁለቱንም ዓይነት መንፈስ የሚያስተናግድ ቢሆንም መንፈስ ደግሞ ቅዱስም እርኩስም መንፈስ አለ፡፡የሆነ ሆኖ ግን በሰማይም ይሁን በምድር የተሰሩት ነገሮች ሁሉ መጀመሪያ በመንፈስ ይከናወናሉ፡፡እኛም ይህ ስጋችን ረቂቅነትንና ማወቅን ቢከለክለንም ነፍሳችን መንፈስ ሰለሆነች ከእንሰሳት በተለየ እናውቃለን እንሰራለን፡፡እንደውም ስጋችን እንደነ ገናናው ፃድቅ የክብር ኮከብ የኢትዮጵያ ብርሃን ተክለ ሃይማኖት ብንክደው ከእግዚያብሄር የሆነውን ሁሉ በባለሟልነት እናውቃለን ከፅንፍ እስከ ፅንፍ እንበራለን፡፡ነገር ግን ይህ ራስን አሳልፎ ለባለቤቱ መስጠትን ይጠይቃል፡፡ዉድ የሆነ ዋጋም ያስከፍላል ይኸምውም የጨለማን ስራ መፀየፍ ነው፤በህግ መኖር ነው፡፡ ለዚያ ነው የሰው ልጅ ከአምላኩ ጥበብን ከመጠየቅ ይልቅ ከጨለማው ገዥ ጋር ተፈራርሞ የአመፅን ስራ የሚሰራው፤ለዚህ ነው የሰው ልጅ አጋንንትን እንደ እውቀት ምንጭ፡የሃብት ምንጭ፡የስልጣን ምንጭ፡የክብር ምንጭ አድርጎ እየተጠቀመ ያለው፡፡ ስጋዊ ደማዊ ሰው እንደት መንፈሳዊና ረቂቅ የሆነን ነገር ሊያውቅ ይችላል፡፡በመንፈሳዊና በቀለማዊ መካከል ልዩነት አለ፡፡እውሮች ሆነው ሳለ እንደት የተሰወረውን ሊያውቁ ይችላሉ? አሱ እግዚያብሄር ከገለጠለት በቀር ማን ህልም ሊፈታ ይህችላል እንዳለ ነብዩ ዳንኤል፡፡ 
 

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment