✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ አውታር
ሕዝባችንን/ምእመን ፡ ላይ ላዩን በድራማዎች እና በ “አዲስ ዜና” ፕሮፓጋንዳዎች እያታለሉ ውስጥ ውስጡን ግን ሰይጣናዊ ህልሞቻቸውን በሥራ ላይ በማዋል ላይ ናቸው።
አለማወቅ፣ አለመጠየቅ … አያኮራም። አካባቢን ለማወቅ አለመፈለግ፣ ነገሮችን ሁሉ፣ በዙሪያችን የሚከናወኑትን ነገሮች ለመገንዘብ ፍላጎት ማጣት አያኮራም። ጭራሽ ስለ ሀገር አለማወቅና አለመጨነቅ፣ አለመጠየቅና አለመረዳት እንዴት ሊያኮራ ይችላል?
በመንበረት ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን መስቀል እየተረገጠ ነው! በምድር አሜሪካ የእሳት ማዕበል ተነስቶ ከተማውን ሲያወድም በመስቀሉ ተዓምር ደግሞ ዓለም ጉድ እያለ ነው!
ካቴድራል/Cathedral የሚል ተጨማሪ ወይም ቅጥያ ስያሜ የሚጠቀሙ አብያተክርስቲያናት የአምልኮ ሥርዓታቸው ከተዋሕዶ ይልቅ ለካቶሊካውያን ሥርዓት የመጠጋትቱ ዕድል የቀረበ ነው።
በምድረ ኢትዮጵያ ደግሞ ለ80 ዓመት መስቀልን ሲያስረግጡ የነበሩት የኢየሱሳዊያን ካቶሊኮች ሴራ በማራመድ ገንዘብንም ተቀብለው በዩኔስኮ/UNESCO ስላስመዘገቡት መስቀሉን ማስነሳት አይችሉም!!
ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ እባካችሁ ንቁ ወደዚህ የኢየሱሳዊያን ካቶሊኮች ካቴድራልን: "ቤተክርስቲያን ነው "ብላችሁ እንዳትሔዱ እባካችሁ!!!
"የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነውና።"
---1ኛ ቆሮ.1፥18
👉ኃይሌን ደግሞ አልረግጥም !!
"አቤቱ ጸሎቴን ስማኝ። አቤቱ ጩኽቴም ወደ አንተ ይድረስ፤ አቤቱ በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትመልስ ። አቤቱ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል። እቤቱ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ። "
--- መዝሙር 102
ታሪካችሁን እወቁ!
ሕዝብ ይንቃ!
ሀገር ይስማ!!
Blogger Comment
Facebook Comment