ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የብሪቲሽ ብሄራዊ ሙዚየም ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት በነበረው የመቅደላ ውጊያ በእንግሊዝ ወታደሮች ተዘርፈው የተወሰዱት እነዚህ ታቦታት በውሰት ሊመልስ ነው።
የሙዚየሙ ሀላፊዎች ጽላቶቹን በመመለሱ ረገድ ሀሳቡን እንደሚጋሩትና የህግ ጉዳይ ሆኖ በነፃ ለመመለስ መወሰን ባይችሉም፣ ታቦቶቾን በረጅም ጊዜ ብድር ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደሚሰጥ በቦታው ለተገኙት ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት አስታውቀዋል።
ሚኒስትሯ በሙዚየሙ የሚገኙ ታቦታት ለኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ልዩ ክብርና ቦታ ያላቸው ከፈጣሪያቸው ጋር የሚገናኙባቸው ህያው በመሆናቸው ወደ ትክክለኛ ቦታቸው እንዲመለሱ ጠይቀው ነበር።
ከእነዚህ ፲፩ ታቦታት መካከል ፱ኙ ከእንጨት ሲሆኑ ፪ቱ ደግሞ ከድንጋይ ናቸው። ሁሉም በእዚህ የብሪቲሽ ሙዚየም ድብቅ የዕቃ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው እንደተቀመጡና እስከ ዛሬ ድረስ፤ ኃላፊዎቹንም ጨምሮ፤ ማንም ከፍቶ እንዳላያቸው ተጠቁሟል። ታቦታቱ ላይ ምናልባት የተቀረፀ መስቀል ሳያርፍባቸው አይቀርም ተብሏል።
በሌላ በኩል የሙዚየሙ ሃላፊዎች ኢትዮጵያን መጎብኘትና አብረው ለመሥራት እንደሚፈልጉ፣ ወደፊት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡም የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረሙ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ቅርሶች በአብዛኛው በእንግሊዝ፣ በጀርመንና በጣልያን አገር ነው የሚገኙት።
መቅደላ ወይም በአሁኑ ስሙ አምባ ማርያም የሚባለው አምባ፣ ወሎ ውስጥ የሚገኝ በአጼ ቴወድሮስ ዘመን ለዋና ከተማነት ታጭቶ በመካከሉ በእንግሊዞች ጦርነት ወቅት የተቃጠለ ከተማ ነው።
የእንግሊዝ ጦር ውድ ብራናዎችን፣አክሊሎችን፣መስቀሎችን፣የወርቅ ዋንጫዎችን፣የንጉሳዊያንና የቤተ ክርስትያን ቁሳቁሶችን ጋሻና የመሳሰሉትን ቅርሶችን በመዝረፈ ፲፭ ዝሆኖችንና ፪፻ በቅሎዎችን ለማጓጓዣነት ተጠቅመው እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። ወሰዱ።
በጣም ይገርማል! እግዚአብሔር የሰጠንን የራሳችንን ንብረት በብድር መልክ ሊሰጡን ነው። ለመሆኑ ይህን ኢትዮጵያ የተረሳችበትን ቀውጥ ጊዜ ለምን መረጡ? ዓብያተክርስቲያናት በሚቃጠሉበትና በሚዘረፉበት ዘመን? ይህ ንብረት የመንግስት ሳይሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅርስና ንብረት ስለሆነ በቀጥታ የሚመለከታት ቤተክርስቲያንን ነው፤ ለምንድን ነው መንግስት ወይም የባሕል ሚንስቴር እዚህ ላይ እጁን የሚያስገባው? ምን ዓይነት ተንኮል ታስቦ ይሆን?
ወይስ ያለፈውን እና መጪውን "ቴዎድሮስን" ፈርተው ይሆን?
የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል አለማየሁ በዊንድሶር ቤተ–
መንግሥት በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ–ክርስቲያን ነው የተቀበረው። ከሁለት ሣምንታት በፊት የስሴክስ ልዑልን የወለደችው የእንግሊዝ ንጉሣዊ ቤተሰብ አዲስ ደም፡ ልዕልት ሜጋን ሜርክል ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ጊዜ የጋብቻ ሥነ ሥርዓቷን የፈጸመችው የልዑል አለማየሁ አጽም በሚገኝበት በዚሁ በውንድሶር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ–ክርስቲያን ነው።
ባለፈው ሣምንት የብሪታኒያ ንግሥት ኤልሳቤጥ የልዑል አለማየሁን አጽም ለኢትዮጵያ አልመልስም ብላ ነበር። ይገርማል!
ለማንኛውም ቅዱስ ታቦታቱን ይመለሱልን እና ሕዝባችንን አደንዝዞና አሥሮ ያለውን እርኩስ መንፈስ ካገራችን ያጥፉልን! እነርሱ ለክፋት አስበውት ሊሆን ይችላል እግዚአብሔር ግን ለበጎ ያደርገዋል።
የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን!
Blogger Comment
Facebook Comment