የነገሩን እንዲህ እንየው እስልምናም ክርስትናም ሁለቱም እምነቶች መነሻቸው ከመካከለኛው ምስራቅ ነው። ነገር ግን በታሪክ፣ በሥነ-ልቦና እና በሕግ መነጽር ስንመለከተው፣ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት "እንደ ሰማይና ምድር" የራቀ ነው።
አንድ ነገር ከውጭ መጣ የሚባለው "ባዕድነቱን" ጠብቆ እስካለ ድረስ ነው። ክርስትና ግን ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ኢትዮጵያዊ ማንነትን ወልዶታል።
ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ እንደ አዲስ እምነት ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ሀገር ግንቢ (State Builder) ነው የመጣው።
ያመጣውም እራሱ ኢትዮጵያዊ ሰው ጃንደረባው በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ነው። የአክሱም ነገሥታት ክርስትናን ሲቀበሉ፣ እምነቱን ከግዕዝ ፊደል፣ ከሥነ-ሕንጻ ጥበብ (Obelisks to Cathedrals) እና ከባሕላዊ እሴቶች ጋር አዋህደው አዲስ "ኢትዮጵያዊ" ማንነት ፈጠሩ።
በ1ኛው ክፍለ ዘመን በጃንደረባው በኩል ዘር ተዘርቶ፣ በ4ኛው ክፍለ ዘመን (በ330 ዓ.ም አካባቢ) የአክሱም መንግሥት ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኗል። ይህም ማለት ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ክርስትናን በመንግሥት ደረጃ የተቀበለች ሁለተኛዋ ሀገር ናት።
ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ኢትዮጵያ የራሷ ፊደል (ግዕዝ)፣ የራሷ ዜማ (ያሬዳዊ)፣ የራሷ የሕግ ሥርዓት (ፍትሐ ነገሥት) እና የራሷ የቀን መቁጠሪያ እንዲኖራት አድርጓል።
ለምሳሌ እንግሊዘኛ ቋንቋ የጀርመንና የፈረንሳይ ቅልቅል ነው፤ ስለዚህ እንግሊዝ የራሷ ቋንቋ የላትም" እንደማለት ነው። ክርስትና የኢትዮጵያ DNA ነው።
እስልምና ግን በኢትዮጵያ ውስጥ የራሱን ፊደል፣ የራሱን የቀን መቁጠሪያ ወይም የራሱን የሕግ ሥርዓት አልፈጠረም፤ ይልቁንም በነበረው የኢትዮጵያ ማንነት ውስጥ "ተሳፋሪ" ሆኖ ነው የኖረው።
አንድ እምነት "የሀገር" የሚባለው ምንጩ ስለተገኘበት ቦታ ሳይሆን፣ በሀገሪቱ ባህል፣ ቋንቋና ስነ-ጥበብ ውስጥ በፈጠረው ጥልቀት ነው።
ስለዚህ ክርስትና በኢትዮጵያ ውስጥ "ተወላጅ" (Indigenous) የሆነ ማንነት ገንብቷል።
ሁለቱም ከውጭ መጡ" የሚለው ንግግር በሁለቱ መካከል ያለውን የ ፮፻ (600) ዓመታት ልዩነት ሆን ብሎ ይዘላል።
ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት በሆነበት በ ፬ኛው ክፍለ ዘመን፣ እስልምና የሚባል እምነት በዓለም ላይ ጭራሽ አልነበረም። ክርስትና ኢትዮጵያን ለ ፪፻ ዓመታት ካስተዳደረ በኋላ ነው መሐመድ የተወለዱት።
አያትህም አባትህም ከውጭ ነው የመጡት" ብሎ መከራከሪያ ሊሆን አይችልም። አያትህ የቤቱ መሥራች ነው፤ አባትህ ደግሞ በቤቱ ውስጥ የተወለደ ነው። ክርስትና የኢትዮጵያ ዘመናዊ መንግሥት "አያት" (Founding Father) ነው።
እስልምና የመጣው ቤቱ ተሠርቶ፣ ፊደሉ ተቀርጾና ሥርዓቱ ተዘርግቶ ካበቃ በኋላ ነው።
የኢትዮጵያ ክርስትና "ከውጭ" የመጣ ቢሆንም፣ በውጭ ተጽዕኖ ሥር አልወደቀም።
ኢትዮጵያ ክርስትናን የተቀበለችው እንደ አውሮፓውያን በቅኝ ግዛት ወይም እንደ መካከለኛው ምስራቅ በሰይፍ ተገዳ አይደለም። በራሷ ፈቃድና ማንነት አዋህዳው ነው።
አንድ ነገር "ከውጭ የመጣ" ተብሎ የሚታገለው ነገር ባዕድነቱ ሲቀጥል ነው። የኢትዮጵያ ክርስትና ግን ከውጭ ከመጣው የዓለም ክርስትና በተለየ መልኩ በራሱ ሰዎች(Ethiopianism) ሆኖተገኝቷል።
እስልምና ግን አሁንም ድረስ ፊቱን ወደ መካ፣ ቋንቋው ዓረብኛ አድርጎ የሚኖር ከአረበኛ ውጭ ሌላ የማያውቅ እምነት ነው። በኢትዮጵያ "ባዕድነቱን" (Foreign element) ጠብቆ የሚኖር እምነት ነው።
ኢትዮጵያ ለክርስትና "ማደሪያዋ" ናት፤ ለእስልምና ግን "መድኃኒቷ" (መጠጊያዋ) ናት።
የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች (ሰሃባዎች) አክሱም ሲገቡ የጠየቁት "እኩልነት" አልነበረም፤ ሕይወታቸውን እንዲያተርፉ ነበር።
ነቢዩም ሲልሷቸው "«ወደ ሀበሻ ምድር ብትሄዱ (ይሻላችኋል)፤ እዚያ ዘንድ ማንም የማይበደልበት ንጉሥ አለና። እሷ (ሀበሻ) የእውነት ምድር ናት፤ አላህ ካላችሁበት ጭንቅ መውጫ እስከሚሰጣችሁ ድረስ (እዚያው ቆዩ)።» ብለው ነው።
ነቢዩ "አላህ መውጫ እስከሚሰጣችሁ ድረስ" ማለታቸው፣ ጉዟቸው ጊዜያዊ ስደት (Refugee status) እንጂ ባለቤትነት አለመሆኑን ያረጋግጣል።
ክርስትና የመጣው ኢትዮጵያን 'ኢትዮጵያ' ለማድረግ ነው፤ እስልምና የመጣው ግን 'ኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር' ነው።
ክርስትና ባለቤት ሆኖ ፊደል ሲቀርጽ አገር ሲሰራ ሕግ ሲያጣ ላሊበላን ሲሰራ አክሱምን ሲገነባ እሴት ባህል ሲያዋቅር እስልምና አልነበረም።
በ7ኛው ክፍለ ዘመን (በ615 ዓ.ም አካባቢ) በስደት በኩል የገባ ነው። ክርስትና ወደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሲሆን ከእስልምና ቢያንስ በ300 ዓመታት ይቀድማል።
ከ1,700 ዓመታት በላይ የአንድ ሀገር መታወቂያ፣ የሥልጣኔ መሠረትና የመንግሥት ሥርዓት ሆኖ የቆየን እምነት፣ ከ600 ዓመታት በኋላ ከመጣ እምነት ጋር "እኩል ከውጭ የመጡ ናቸው" ማለት ታሪካዊ ሚዛኑን ያሳጣዋል።
ይህ አባባል "አያቴ አባቴን ስትወልድ እኔ ነበርኩ" እንደ ማለት ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment