የመልከ ጸዴቅ እና የኢትዮጵያ ጊዜ

ኃይል ከእሥራኤል ወደ ኢትዮጵያ ይዞራል
ከ"ዘእምነገደ ይሁዳ" ወደ "ዘእምነገደ ኢትዮጵያ"

"የህሊና እዳ" የተሰኘ መጽሃፍ ንግስት ሳባ ወደ ሰለሞን እንዳልኼደች እንዲያውም ራሱ ወደ እሷ እንደመጣ፤ የኢትዮጵያን ከእሥራኤል በላጭነት በሚያስረዱ መረጃዎች አጅቦ ያቀርባል። የሳባ ወደ ሰለሞን መኼድ የታመነ ነገር ነው፤ በወንጌልም ተረጋግጧል እንደዚሁም ሁሉ የኢትዮጵያ ከእስራኤል መብለጥ ብዙ ማስረጃዎች ያሉት ነው። የሆነ ሆኖ የመጽሃፉ ደራሲ በሳባ ወደ ሰለሞን የመኼድ ታሪክ አፍሯል። መፍቅሬ እንስት የሆነው ሰለሞን ከሳባና ከገረዷ ጋር መተኛቱም ለብሔራዊ ኩራታችን የማይመጥን ሆኖበታል...ወንድ ፍለጋ የኼደች ንግስት ሆና መቅረቧ ደብሮታል...እኔም ይኼ ስሜት ይሰማኛል።
 
በተጨማሪም ነገስታቶቻችን ከራሳችን ያልወጡ መሆናቸው ትንሽ ግራ ያጋባል።

ከንግስተ ሳባ በፊት የነበረው ንጉስ እስያኤል ፍጥረታትን በማዳቀል የተካነ ነበር ይባልለታል፤ ምናልባት ሳባ ከሰለሞን ብትዳቀል ከሁለቱም የተሻለ hybrid  ዝርያ ሊገኝ እንደሚችል አስቀድሞ አስተምሯት ሊሆን ይችላል።

አብርሃም ጠላቶቹን ካሸነፈ በዃላ ከምርኮው ላይ ለመልከጸዴቅ ገብሯል። ይህም የመልከጸዴቅን በላጭነት ያመለከተ ነው። መልከ ጸዴቅም አብርሃምን መርቆታል።

ከካም_ነገድ የተገኘውና ኢትዮጵያዊነቱ የተመሠከረለት መልከ ጸዴቅ ከሌዋውያን የበለጠ ነበር፤ ክህነትን ከንግስና የያዘም ተብሏል። ክህነቱ የዘላለም የሳሌም(የሰላም ንጉስ) ነው መልከ ጸዴቅ።

መልከ ጸዴቅ የአዳም መቃብርን ይጠብቅ ስለነበረ የቀረበለትን የሹመት ጥያቄ ውድቅ አድርጓል ሆኖም ወደ እሱ የኼዱትን ይሾምና ይመርቅ ነበር።

መልከ ጸዴቅ የክርስቶስ ምሳሌ ተደርጎ ነው የሚወሰደው፤ በብሉይ ኪዳን የክርስቶስ ምሳሌ የነበረው መልከ ጸዴቅ ነበር...እርሱም ኢትዮጵያን ያስጠራውን ኢትዮጵን ወለደ...ከኢትዮጵም የሙሴ አማች ዮቶር ተገኘ...መልከ ጸዴቅ አብርሃምን እንደመረቀ፣ የቤተሰቡን ቅድምና አስጠብቆ ዮቶርም ሙሴን አስተማረው።

በመሃከለኛው_ዘመን ምዕራባውያን ክህነትና ንግስና አስተባብሮ ስለያዘ አንድ ሰው ሰምተው ይደነቁ ነበር፤ የዚህንንም ሰው ሃገር ፍለጋ ብዙ ከኳተኑ በዃላ ሰውዬው (Prestor John) ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ደርሰንበታል አሉ። ይህ ሰው እስካሁን ማን እንደሆነ ባይደርስበትም ክህነትንና ንግስናን አስተባብሮ መያዙ ግን መልከ ጸዴቅን የሚገልጽ ሆኖ ተገኝቷል። በኢትዮጵያ ትንሳኤ የሚነሳው ንጉስም ንግስናን ከክህነት የሚያስተባብር እንደሆነ ይታመናል። ምዕራባውያኑም ጉዳዩን አጥብቀው የመረመሩት ለዚሁ ነው። ንጉሱ-ካህን (Prestor John) እና ለዘመኑ መጀመሪያ የለውም ክህነቱም የዘላለም ነው፤ የተባለለት መልከ ጸዴቅ ሁለቱም ምሥጢር ሆነው ቆይተዋል። የመልከ ጸዴቅ ሥርወ መንግስት መመለስ ክህነትን ከንግስና አስተባብሮ በሚይዝ መሪ እንዲሁም ኢትዮጵያዊነትን ከእስራኤላዊነት በሚያስበልጥመሪ ሊገለጽ ይችላል።

ኢትዮጵያ ከአይሁድ ለመብለጧ ምስክሮቹ ብዙ ናቸው። የኢትዮጵያዊው መልከ ጸዴቅ የክርስቶስ ምሳሌነት፣ አብርሃም በመልክ ጸዴቅ መመረቁና ለመልከጸዴቅ መገበሩ፣ ዮቶር ሙሴን ማስተማሩ፤ ትንቢተ ኢሳያስ፣ መጽሐፈ ሔኖክ፣ ዘፍጥረት የመሣሠሉት የብሉይ ኪዳን መጻህፍት የኢትዮጵያ መሆናቸው መረጋገጡ፣ ኖህ ኢትዮጵያዊ መሆኑ መረጋገጡ (መቃብሩም በጎንደር ቤተ መንግስት ሥር መሆኑ...) የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት፣ ቀዳማዊ ምኒልክ ከእስራኤል ይልቅ ኢትዮጵያን መምረጡ፣ የአይሁድ ክርስቶስን መካድና የኢትዮጵያውያን ክርስቶስን መቀበል፤ በዓለም ታሪክ ውስጥ የኢትዮጵያውያን ተወዳጅነት እና የአይሁድ መጠላት፣ የአይሁድ በሁሉም ሃያላን ሃገራት መወረር እና የኢትዮጵያ በማንም አለመገዛት በሁሉም ወገኖች መተረኩ.....!

ቀዳማዊ ምኒልክ በሳባ በኩል  የመልከ ጸዴቅ ደም ቢኖርበትም ንግስናው" ዘእምነገደ ይሁዳ" መሆኑ የኢትዮጵያን የበላይነት ያልመሠከረ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ አይሁዶችን ያነገሰችም ያዋረደችም(ፈላሻዎችን) ብቸኛዋ የዓለማችን ሃገር መሆኗ በራሱ አስደናቂ ነገር ነው። ቀዳማዊ ምኒልክ ከእስራኤል የመጣው ኢትዮጵያን አስበልጦ ነው። ለታቦተ ጽዮንም ከእስራኤል ይልቅ ኢትዮጵያ የተሻለች መሆኗ ታምኖበታል....እና የመልከጸዴቅ አሠራር መመለስ በሁለት ነገር ይረጋገጣል...ንግስናን ከክህነት በያዘ ንጉስ እንዲሁም "ዘእምነገደ ኢትዮጵያ"የሚል ኢትዮጵያን ከእሥራኤል በሚያስበልጥ ሥርወ መንግስት፤ የኢትዮጵያ ጊዜ መሆኑም የሚመሠከረው አሁን ዓለምን ጨብጠው የያዙት አይሁዶች የኢትዮጵያን የበላይነት ሲመሠክሩ ነው። በዚህም ጊዜው ከአይሁድ ወደ ኢትዮጵያ ይዞራል። 

አሁን ጊዜው በሁሉ ነገር መሪነትን የጨበጡት የአይሁድ ነው! እና ይህ መሪነት ወደ ኢትዮጵያውያን ይዛወራል በዓለም ዙሪያውን ኢትዮጵያውያን መሪነትን ይቆናጠጣሉ...የአይሁድ በሆነው ቦታ ላይም ይቀመጣሉ! ታሪካችንም ይኼው ነበር ይታደሳልም... ይኼው ነው የመልከጸዴቅ ንግስናና ክህነት፣ የኢትዮጵያ ጊዜ!!!

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment