ታላቁ ንጉሥ ጠቢቡ ሰለሞን ስርአተ ንግሥናውን የፈፀመው ኢትዮጵያ ውስጥ ጣና ዳር ነው

ጠቢቡ_ሰለሞን ቅብዓ መንግሥቱን የተቀባው በግዮን እና በጣና ዳርቻ ነው! እስራኤልን ለመግዛት ንግሥናውን የፈፀመው ምድረ ገነት በሆነው ግዮን ላይ ነው! መፅሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ላይ እንዲህ ይላል;

"ንጉሡም ዳዊት ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ጥሩልኝ አለ! ወደ ንጉሡም ፊት ገቡ! ንጉሡም አላቸው የጌታችሁን ባሪያዎች ይዛችሁ ሂዱ ልጄንም ሰሎሞንን በበቅሎዬ ላይ አስቀምጡት ወደ ግዮንም አውርዱት በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቀቡት ቀንደ መለከትም ነፍታችሁ ሰለሞንን ሺህ አመት ይንገሥ በሉ! (1ኛ ነገሥት 1: 32-35) ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን የዮዳሄም ልጅ በናያው ከሊታውያንና ፈሊታውያንም ወረዱ ሰለሞንም በንጉሡ በዳዊት በቅሎ ላይ አስቀምጠው ወደ #ግዮን አመጡት! ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅብዓቱን ቀንድ ወስዶ ሰለሞንን ቀባ ቀንደ መለከትም ነፍ ሕዝቡም ሁሉ ሰለሞንን ሺህ ዓመት ይንገሥ አሉ! ሕዝቡም ሁሉ እርሱን ተከትለው ወጡ" (ሙሉ ምእራፍ አንድን ያንብቡ)

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment