ይድረስ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን

✍ ቆሞስ አባ ጳውሊ | ከግንባር

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በታሪኳ አይታው በማታውቀው የአምባገነንነት አገዛዝ ስር ወድቃ ትገኛለች። ስርዓቱ ስልጣኑን ለማራዘም ሲል የህዝቦችን ደም እንደ ውሃ እያፈሰሰ ሀገሪቱን ወደ አልተፈለገ የመበተን አደጋ እየነዳት ይገኛል። ይህንን ሀገራዊ መከራና የህዝቦች ሰቆቃ ለማስቆም የአማራ ፋኖ ነፍጡን አንስቶ የህልውናና የነፃነት ትግል እያካሄደ ይገኛል። ፋኖ የወገኑን መበደል ለማስቆም ብሎም  መላዋን ኢትዮጵያ ከጥፋትና ከብተና ለማታደግ በተለያዩ መዋቅሮች ተደራጅቶ የሚፋለም ታላቅ ህዝባዊ ኅይል ነው። ይህ ህዝባዊ ኃይል ለህዝብ መስዋዕትነት እየከፈለ የአምባገነኑንም መንግሥት ስርዓት እያፈ*ራረሰው ይገኛል::  ይህን የህዝብ እንባ ጠባቂ ኃይል ሌሎችም ኃይላት አብረውት ኢትዮጵያን ለማዳን ሰሞኑን እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ:: ይህ ለኢትዮጲያ ታላቅ ብሥራትና የሚደገፍ የተቀደሰ የፍቅርና የአንድነት መንፈስ ነው:: 

ሆኖም በቅርቡ የተፈጠረው የአማራ ፋኖ እና አጠቃላይ ለነፃነት የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያን ለመታደግ የሚፈልጉ ኃይላት ህብረትና ጥምረት የአምባገነኑን ስርዓት መዋቅርና የስልጣን መሰረት ያወከ ታሪካዊ እርምጃ ስለሆነ ብልጽግና እየተሸበረ ይገኛል:: ይህ ጥምረት ስርዓቱን  ካ*ስ*ወ*ገ*ደ  በኋላ ፍፁም ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና አሳታፊ የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለመ እንደሚሆን የታመነ ነው። ነገር ግን አገዛዙ የዚህን ጥምረትና የአንድነት ግስጋሴ አጥብቆ ስለፈራው አብሮነታችንን ለማፍረስና የህዝቦችን ትግል ወደኋላ ለማስጎተት አደገኛ ሴራዎችን እየሸረበ ይገኛል። በተለይም የወሰንና የማንነት ጥያቄዎችን እንደ ምቹ ምክንያት በመጠቀም የአማራ ህዝብ እና ሁሉም ህዝቦች በጋራ እንዳይቆሙና ወደ አላስፈላጊ የእርስ በርስ ግጭት እንዲገቡ በማድረግ ላይ አትኩሯል።በሌላ በኩል የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአገዛዙ የሐሰት ትርክትና በአማራ ህዝብ ላይ በተሰራጨ ጥላቻ ተታለው በመከላከያ፣ በፖሊስ፣ በሚሊሻና በልዩ ኃይል ስም ወደ አማራ ክልል እየገቡ የሚያካሂዱት ጦርነትና የሚከፍሉት መስዋዕትነት ፍጹም በስህተት የተመራና ከንቱ እንደሆነ መገንዘብ አለባቸው። ወታደሩም ለአንድ አገዛዝ ዙፋን ለማስጠበው በከንቱ እየተቀሰፈ ስለሆነ ህዝብ ከእንቅልፉ መንቃት አለበት:: ይህ አካሄድ ሀገሪቱን ወደ ከፋ ጥፋት ከመክተትና የንጹሃንን ህይወት ከማጥፋት ባለፈ ለህዝቡ ምንም ጥቅም ሊሰጥ አይችልም:: ይልቁንስ ባህልን፣ ሃይማኖትን፣ ነባር እሴቶችን፣ ማንነትን፣ አንድነትንና ኢትዮጵያዊነትን እየደ*መሰሰ ያለውን አገዛዝ በአንድነት መታገል ይገባል። ውድ ኢትዮጵያውያን ሆይ ብልፅግና ሀገሪቱን ከፋፍሎ ለጥፋት ስለዳረጋት ከስሜታዊነትና ከጥላቻ ወጥተን ከዚሁ አገዛዝ የሚመጡ የመከፋፈያ ዘዴዎችን በመበጣጠስና በመቃወም ሁላችንም  በአንድነት ቆመን ሀገር የምናድንበትን መንገድ ልንፈልግ ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን የኑሮ ውድነቱ ከዚህ የበለጠ ይከፋል፤ ኢትዮጵያም ከዚህ በላይ ትበታተናለች እንጂ ምንም አይነት ዘላቂ መፍትሔ በፍጹም አይገኝም። በግደለሽነት በምን አገባኝ ከሚመጣብን ጥፋት ሁላችንም ማምለጥ እንደማንችል መገንዘብ ይኖርብናል::  ከአንቀላፋን የመከራው እሳት በሁላችንም በር እያንኳኳ መምጣቱ የማይቀር ነው:: 

ከዚህም በተጨማሪ በትግሉ መዋቅር ውስጥና ሰርገው በመግባት በነጻነት ኃይሎች ስም የተሸሸጉ ኢትዮጵያ ከውድቀቷ እንድትነሳ ከሚፈልጉ ኃይላት ጋር የሚደረገውን አንድነት በመቃወም ጦርነቱ እንዲራዘም በማድረግ ላይ ናቸው። እነዚህ አካላት ህዝቡ ቶሎ ነፃ እንዳይወጣና መከራው እንዲቀጥል የሚያደርጉበት ዋና ምክንያት የትግሉን ጊዜ እያራዘሙ በህዝብ እንባና ደም ላይ የግል ጥቅማቸውን ለማካበትና ለመበልፀግ በመስራት ላይ የሚገኙ በመሆናቸው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በህዝብ ትግል ስም ተሸፍነው ከአምባገነኑ ስርዓት ጋር በስውር በመመሳጠር የትግሉን እድሜ ለማራዘም የተላኩ የውስጥ ሀሳዊያን ናቸው። ስለሆነም በአሁኑ ወቅት የአማራ ፋኖ እና አጠቃላይ ለነፃነት የሚንቀሳቀሱ ኃይላትን ጥምረት የሚያናንቁ፣ የሚቃወሙና ጥላቻን የሚያሰራጩ አካላት በሙሉ የአገዛዙ አገልጋዮችና ህዝቡ ቶሎ ነፃ እንዳይወጣ የሚፈልጉ የህዝብ ጠላቶች ናቸው። አባባሉ እንኳን "ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለሃምሳ ሰዎች ግን ጌጥ ነው" አይደል የሚለው? ፋኖ ብቻውን የህዝብን ቀንበር ይሸከም ዘንድ ከንቱ ምኞትን አትመኙ! 

ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ ውጣ ውረድና ውስብስብ ሁኔታ ስንመለከት አንድ ብሄር ብቻውን የዚህን ሁሉ አምባገነናዊ አገዛዝ ግፍና መከራ ተሸክሞ ሀገሪቱን ከጥፋት ሊታደጋት አይችልም። አምባገነኑን ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አ*ስ*ወ*ግ*ዶ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት መላው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ከፋኖና አጠቃላይ ለነፃነት ከሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያ እንድትድን ከሚፈልጉ ኃይላት ጋር በአንድነት ሊሰለፉ ይገባል። አገዛዙ ይህንን ህዝባዊ ህብረት ለማፍረስ በፋኖ እና በሌሎች ሀይሎች ስም እንዲሁም በአማራ ህዝብ እና በሁሉም ብሄረሰቦች ስም ሀሰተኛ አካውንቶችንና ሚዲያዎችን በመጠቀም የጥላቻና የመለያየት አጀንዳዎችን እየዘራ ይገኛል። መላው ህዝብ ፣ ታጋዩና ደጋፊው የዚህን የስርዓቱን አደገኛ የከፋፍለህ ግዛ ሴራ ተረድቶ በከፍተኛ ንቃትና ብስለት ሊመክት ይገባል። በሁሉም ህዝቦች መካከል ከዚህ ቀደም የተከሰቱት የደም መፋ*ሰሶችና ቅራኔዎች በሙሉ የህዝቦች ነባር ቁርሾዎች አይደሉም። የችግሩ ዋና መንስኤ ስርዓቱ ስልጣኑን ለማራዘም ሲል የሸረበው አደገኛ የፖለቲካ ሴራና ስብራት ውጤት ነው። ይህን የፖለቲካውን ስብራት በፖለቲካዊ ብስለትና በመተሳሰብ በማከም የትናንትናውን ቁስል በነገው አዲስ ተስፋ ማደስ እንችላለን። ነገር ግን ሁልጊዜ በሴራና በክፋት ለመጓዝ የሚሞክሩ አካላት ሀገሪቱን ወደ ከፋ መከራ የሚያስገቧት ሲሆን ፈጣሪም እንደዚህ ያሉ ሴረኞችን በራሳቸው በቆፈሩት ጉድጓድ እንደሚጥላቸው የታወቀ ነው።

በኢትዮጵያ ክልሎች መካከል የሚደረጉ የወሰንና የደብረ ገበታ ውዝግቦች ሀገሪቱን ወደ ከፋ ጥፋት የሚያመሩ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ አያመጡም። ሀገሪቱን እያደማ ያለውና ህዝብን ከህዝብ፣ ቋንቋን ከቋንቋ የሚያጋጨው ብልሹ የመከፋፈል ስርዓት ሙሉ በሙሉ መ*ወ*ገ*ድ አለበት።  ያኔ ችግሮቻችንን ሁሉ በውይይት እንፈታለን! የማንኛውም አካባቢ መሬትና ወሰን ጥያቄ መፈታት ያለበት በኃይል ወይም በጉልበት ሳይሆን አምባገነኑ ስርዓት ከ*ተ*ወ*ገ*ደ በኋላ በወንድማማችነት፣ በፍቅርና በህዝባዊ ውይይት ብቻ ነው። ከትናንት ስህተታችን ተምረን  ነገ አዲስ ታሪክ ለመስራትና ሀገራችንን ጠብቀን ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ መስራት ያለብን ሰዓት እነሆ አሁን ነው! ከዚህ መልካም አስተሳሰብ ወጥተን በፅንፈኝነትና በክፍፍል የምንቀጥል ከሆነ የነገዋ ኢትዮጵያ የተበታተነችና የታሪክ አቧራ የሆነች ሀገር እንደምትሆን አጥብቀን ልንገነዘብ ይገባል።
ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶችና የህዝብ ድምጽ የሆናችሁ አካላት በሙሉ ሁላችሁም በአሁኑ ወቅት ዋና ሀገራዊ ኃላፊነታችሁ የአማራ ህዝብንና የመላው የኢትዮጵያ ህዝቦችን አንድነት ማጠናከር ነው። እርቅና ሰላም የሚወርድበትን መንገድ በማመቻቸት ረገድ ከፍተኛ አዎንታዊ ሚና ልትጫወቱ ይገባል፤ ህዝብን ከህዝብ የሚለያዩና ጥላቻን የሚዘሩ ንግግሮችን በፍፁም ማስወገድ አለባችሁ። ፖለቲካና የፖለቲካ አሰላለፍ በየጊዜው የሚቀያየር ጊዜያዊ ክስተት ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝቦች ግን ዘላቂ ወንድማማቾች ናቸው። ህዝቡ እርስ በእርሱ ጠላት አይደለም፤ ጠላቱ ህዝብን የሚያጋጨው አምባገነኑ አገዛዝ ብቻ ነው። አንዳንድ ፖለቲከኞች ይህንን አጋጣሚ ለተንኮልና ለግል ፍላጎታቸው ለማዋል የሚያደርጉት ጥረት በፍጹም እንዲሳካላቸው መፍቀድም የለብንም:: በመሆኑም መላው የሰላምና የፍትህ ኃይላት በአንድነት በመቆም አምባገነኑን ስርዓት በ*ማ*ስ*ወ*ገ*ድ  ለሀገርና ለህዝብ የሚመጥን፣ የህዝብን እንባ የሚያብስ፣ ያለፉትን በደሎች የሚክስና ፍቅርና አንድነት የሰፈነባትን አዲሷን ኢትዮጵያ የሚያመጣ አድስ ሥርዓትን በጋራ ማዋለድ ይኖርብናል:: ከዚህ ውጭ ሌላ መፍትሄ በፍጹም ሊኖር አይችልም!

ኢትዮጵያን ለማዳን እኔ ፣ አንተ፣አንቺ ፣እርስዎ ሁላችንም አብረን እንነሳ!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment