✍ መስከረም ለቺሳ (ዶ/ር) | ዮቶጵያ
ገንዘብ የሚያመልክ ሰው፡ ድሃ ነው። ምክንያቱም፡ ገንዘቡ ካለቀበት፡ ሌላ ነገር የለውም።
ገንዘብ የሚያመልክ መንግሥትም፡ ድሃ ነው። ምክንያቱም፡ ገንዘቡ ካለቀበት፡ ሌላ የሚቆምበት እሴት፣ መርኅ፣ ዓላማ ወይም ታሪክ የለውም። መርኁ ገንዘብ ብቻ ስለኾነ፡ ከሕዝብም ኾነ ከሌላ፡ እንዴት ገንዘብ እንደሚሰበስብ ብቻ ያስባል።
ገንዘቡን (አምላኩን) ደግሞ በአደባባይ ማምለክ ይወዳል። አምላኩን የሚያመልከበት የዐደባባይ ሥርዓቱም፡ ይፋዊ ቅንጦት ነው።
እንዲያም ኾኖ ግን፡ ውስጡ ገንዘብ በማጣት ስጋት የተመታ ነው። ምክንያቱም፡ ገንዘቡ ካለቀ ምንም የለውም። ከገንዘቡ ውጪ፡ እሱ ማንነት የለውም። ገንዘቡ እሱ፥ እሱም ገንዘቡ ናቸው።
ይኽ "መካከለኛው ዘመን" ብለው በሚጠሩት በጨለማው ዘመን (Dark Age)፡ የአውሮፓ ነገሥታት የነበሩበት የወደቀ ስነ ልቦና ነው።
ነገሥታቱ፡ ከሕዝባቸውና ከወረሯቸው አገራት፡ ገንዘብ መሰብሰብ፣ መዝረፍ፣ መማረክ፣ መቀጮ መጣል፣ መውረስ ላይ ተጠምደው ነበር። ሕዝቡም፡ ከነሱ ተምሮ፡ ገንዘብ ወዳጅ ኾኖ፡ ከመሥረቅ በቀር፡ ሌላ ሥራ አልነበረውም። ለዳቦ ብሎ ይገድላል፤ ለዳቦ ብሎ ይገደላል።
በወቅቱ፡ በአውሮፓ ትልቅ ተጽዕኖ እያሳደሩ የነበሩት እምነቶች ደግሞ፡ እስልምና፣ ካቶሊክ፣ እና gnosticism/hermeticism (ኮከብ ቆጠራ) ናቸው።
በኋላ ግን፡ ሕዝቡ፡ "በቃኝ!" አለና፡ ከቄሱ ዮሓንስ አገር ኢትዮጵያ፡ ከነላሊበላና ይምርኃነ ክርስቶስ፡ ብዙ ክርስቲያናዊ የአስተዳደርና የአኗኗር ትምህርቶችን እየተማረ፡ ወደ Utopianism ገሠገሠ።
ተዋሕዶ/ዩቶፕያ፡ አገርን ከጨለማ ዘመን ሥርዓት ነፃ ታወጣለች።
በተዋሕዶ/ዩቶፕያ፡ የሚመለከው፡ ገንዘብ ሳይኾን፡ ሰው ነው።
በተዋሕዶ/ዩቶፕያ፡ ሰው ክቡር ነው። ምክንያቱም፡ የሚመለከው፡ ሰው የኾነው አምላክ ነውና፡ የሰው ባሕሪው ከብሯል።
በተዋሕዶ/ዩቶፕያ፡ ትግሉ ኹሉ፡ ሰውን፡ ወደ ሰብአዊ ብቻ ሳይኾን፡ ወደ አምላካዊ ክብሩ መመለስ ነው። ሰው፡ በክርስቶስ ምክንያት፡ የፀጋ አምላክ ኾኗልና።
በተዋሕዶ/ዩቶፕያ፡ ገንዘብ፡ የሰው መጠቀሚያ ብቻ ነው። የሰውን ባሕሪ የማማሰን (የማበላሸት) ዓቅም ስላለውም፡ ከትልልቅ ሰዎች በቀር፡ ልጆች ምን እንደኾነ እንዲያውቁት አይደረግም ነበር። "ልጅ ፍራንክ አይዝም!"
አሁን ግን፡ ዕድሜ ለሌሎች እምነቶችና ለኮከብ ቆጣሪው ዓለም፡ ገንዘብ በቄሱ ዮሓንስ አገር አምላክ ኾኖ፡ ሰው ስለገንዘብ ጭዳ ግብር ይደረጋል።
ተዋሕዷዊ/ዩቶፕያዊ ዐብዮት ያስፈልገናል።
ይኽ በእንዲህ እንዳለ፡ የኢሉሚናቲ ዐብዮት አስጀማሪዋ ካቶሊኳ ፈረንሳይ ግን፡ በላሊበላ ምን እየሠራች ነው?
Blogger Comment
Facebook Comment