የጌታን መስቀል የተሸከመው ኢትዮጵያዊ

ኢትዮጵያዊው ስምኦን የተባለውን የቀሬና ሰው የሮም ወታደሮች የጌታን መስቀል እንዲሸከም አዘውታል።

እርሱም አርብ ጠዋት በአምስተኛው መቆምያ በላይኛው እየሩሳሌም ከእየሱስ መስቀሉን ለእርዳታ ተቀበለው። ከእየሱስ ጫንቃ ላይ አውርዶ እስከ ቀራንዮ አንድ ምዕራፍ ተሸከመ።

የይሁዳና የሌዊ ነገድ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ የማርቆስ አጒት የማርያም ወንድም የቀሬና ሰው ስምኦን ወደ ቤተ-መቅደስ ሊሰግድ መጥቶ ከማርያም (የማርቆስ እናት) ቤት ነበር።

ስምዖን ጥቁሩ የጌታ መስቀል ክብደት፣ ስፋትና ርዝመት መስቀል መሸከምስ ምን ይመስላል? የሚሉትን መናገር የሚችል የነገረ መስቀል ሊቅ ነው።

ማርቆስ ስለ አጒቱ ስምኦን "አንድ መንገድ አላፊም የአሌክሳንድሮስና የሩፎስ (እርፍ) አባት ስምኦን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት (ማር 15፤21)

ቀሬና ማለት:- በአማርኛ የዘላኖች የቅራት መቅሪያ የከብቶች መከመርያ ማለት ነው።...ይህ ቅዱስ ስፍራ ተጓዥ ኢትዮጵያን የሚሰፍሩበትና የሚያርፉበት ሥፍራ እንደነበረ ይነገራል። (መሪ ራስ አማን በመክሱተ ምስጢር ጠቅሰውታል)

ቀራንዮ:- ንጉሥ ሰሎሞን ለሳባ (ኢትያ) ለርሷና ለወገኗ ማረፊያ ይሆናት ዘንድ ቀራንዮን ጒሎጒታን እንደሰጣትም ይታወቃል። (መሪ ራስ አማን በመክሱተ ምስጢር ጠቅሰውታል)

በጥቁርነቱ ቢስማሙም አንዳንዶች ቀሬና ሰሜን አፍሪካ የአሁኗ ሊብያ እንደሆነች ሐዋ ፮÷፱ በመጥቀስ ሚሞግቱም አሉ።

እላለሁ ሀገሬ የሌለችበት ታሪክ አይጣፍጥ ይመስል በሁሉም አለች በሰማይ በምድሩ።

እኛ ግን አናውቃትም። 


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment