✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር
ኢትዮጵያ ማለት የቃሉ ትርጉም የተቃጠለ ፊት ማለት ሳይሆን ኢትዮጵያ ማለት “ለአምላክ የሚሰጥ የወርቅ ሥጦታ” ማለት ነው። ሲተነተንም ኢት=አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ማለት ሲሆን ዮጵ= ቢጫ ወርቅ፣ ውድ ወርቅ፣ ልዩ ወርቅ ማለት ነው።
ሊቀ ነብያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ ያስተማረው ኢትዮጵያዊው ዮቶር ነው። ስለዚህ ለእስራኤል ከፈርዖን ነጻ መውጣት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና አለበት ማለት ነው። አሁንም የሊቀ ነብያት ሙሴ ሚስት ሲጳራ ኢትዮጵያዊት ነች። ሐበሻዊት ሲጳራ የኢትዮጵያዊው የዮቶር ልጅ ነች። አልአዛር እና ጌርሣም የሚባሉ ልጆችንም ወልደዋል። ሙሴ ይቺን ሴት በማግባቱ ወንድሙ አሮንና እህቱ ማርያም ያጉረመርሙበት ነበር።
የመጀመሪያው ካህን መልከጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነው ይህ ካህን በክርስትና አስተምህሮ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ተደርጎ ይቆጠራል። ከባቢሎን ዘመን አስቀድሞ የነበረው ብቸኛው የሰው ልጅ ቋንቋ (ግዕዝ) የሚገኘው ኢትዮጵያ/ቤተ ክርስትያን/ ውስጥ ነው። ጻዲቁ አባታችን የሄኖክ የልጅ ልጅ ኖኅ የተቀበረው ኢትዮጵያ/ጎንደር/ ውስጥ ነው። ኖኅ ራሱንና ልጆቹን ከንፍር ውኃ ያዳነባት መርከቡን ያሳረፋት ኢትዮጵያ ጣና አካባቢ ከሚገኘው አራራት ተራራ ላይ ነው።
የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረው ከአራት ባህሪያተ ስጋ ነው። ከእነዚህም መካከል ደግሞ የተፈጠረበት እሳት ውኃና ነፋስ የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው። ከዚህም በመነሳት አዳምና ሄዋን ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ነች። ኖኅ በጣና ነበረ።ኖኅ የዘመኑ ፍጻሜ እስከሚቀርብ ይኖር የነበረው በአራራት ተራራ ነው። የኖኅ መርከብ ሐመር ያረፈችበት ስሙ ሉባር ተራራ ይባላል። (ገድለ አዳም፣157-167፣ኩፋሌ 8፥1)
#አራራት_ተራራ 150 ሜትር ርዝመት አንባ ሊኖረው ግድ ይላል ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ #ሐመር አሠራር የሚነግረን ይህንን ነው። ሌላው አራራት ተራራ ተያያዥነት ያለው ተራራማ ነው።መርከቧ ያረፈችበትና ኖኅ ወይን የተከለበት ተራራ ነው።ኖኅ አካባቢውን ሳይለቅ ከጥፋት ውኃው በኋላ 350 ዓመት ኖረ። የትም አልሄድም ኖኅ ካምን ይዞ ወደ አፍሪካ ምድር ሄደ የሚለው ልቦለድ ድርስት ነው።
ሌላው የኖኅ መቃብር ከአራራት ተራራ አይርቅም። እርሱም በአሁኗ ጎንደር ከተማ ሲሞት በመቃብሩ ላይ ምንጭ ፈልቆ በርካታ ሰዎችን ይፈውስ ነበር። ሆኖም ፈጣሪ ለኖኅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በቤተመንግሥት አሳቦ የኖኅ መቃብር ሐውልት እንዲታነጽ ፈቀደ።
የኖኅ ሚስት እሜቴ አይከል የተቀበረችው ጭልጋ ላይ ነው። በዚህም የጭልጋ ዋና ከተማ በስሟ አይከል ተባለች። ጭልጋ የአራራት ተራራ አዋሳኝ መሆኑ ይታወቃል። ሉባር የሚባል ከተራሮች መሃል የሚገኘው ጣና እንጅ ከአርመኒያው ቦታ የለም። የነጮች የፈጠራ ውሸት ነው። ያልተፈጠረን ታሪክ ሲነግሩን የቆዩት የአራራትን ተራራ ታሪክ ለመሻማት መሆኑ ግልጽ ይሁን።
መጽሐፈ ኩፋሌ 9 ላይ እንደተብራራው ኖኅ ለልጆቹ ርስት ሲያከፋፍል ለሴም ጣናንና አባይን ተንተርሶ እስከ ግብፅ ዕጣ እንደወጣለት ይታወቃል። ግብፅ ለመነሻው ቦታ ሰሜን ናት። ግብፅ ለእስያ ምድር ሰሜን አትሆንም። አራራት ተራራ ለማየት በባህርዳር ከተማ ፊትለፊት 3 ዝቅተኛ ተራራዎች በጣና ሐይቅ ዳርቻ ማየት ይቻላል። ወይንም በዘጌ በኩል ሦስቱ ተራሮች ከስር በኩል አንድ ሆነው ከላይ በኩል ተለያይተው ይታያሉ። መርከቧ ያረፈችበት ቦታ ደልዳላ ሲሆን የመርከቧን ስፋትም መገመት ይቻላል።
ወይንም አራራት ተራራ የይጋንዳ ተክለሃይማኖት ቤተ ከርስቲያን ያለበት ነው። መርከቧ ያረፈችው ከቤተ ክርስቲያኑ ጥግ ነው። መርከቧ ያረፈችበት ሉባር ተራራና ሌሎችም ቦታዎች እስከ አሁን ድረስ በአትክልት የታጀቡ ናቸው። የዘጌ ኗሪዎችም አትክልት በማትከል ብቻ የሚተዳደሩ ናቸው።
Blogger Comment
Facebook Comment