666ቱ ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ መከራ

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

በአክሱማዊቷ ቅድስት ኢትዮጵያ ምድር ተወልዶ እግዚአብሔርን ከካደ አደገኛ ግለሰብ ውይም ቡድን የከፋ የጽዮናውያን ጠላት ሊኖር አይችልም። ህፍረተ-ቢሶቹና ጸጸት-አልባዎቹ እነ ጌታቸው ረዳና ህወሓት ምሳሌ ናቸው።

እነዚህ 'አንማርም!' ባይ ከሃዲዎች ጽዮናዊውን ሕዝቤን በጥይትና በረሃብ ከጨረሱት በኋላ፣ የቀረውንም ለተጨማሪ ረሃብ፣ በሽታና ደዌ አጋልጠው ካዳከሙት በኋላ አሁን የዋቄዮ-አላህ-ባፎሜት-ሉሲፈር ባሪያዎቹና የመጨረሻው ትውልድ ቅሪቶች መካከል አንዶቹ የሆኑት ህወሓቶች ክርስቲያን እናቶችንና አባቶችን በመደብደብ፣ በማሰርና በመግደል ላይ ናቸው። ይህ እንደሚመጣ እግዚአብሔር ስላሳየን ነው እኮ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ስንጮኽና ስናስጠነቅቅ የነበረው።

ደብረ ሲና ድረስ የሄዱት እንደተለመደው ለሰይጣናዊ ተልዕኮ ነበር። በትግራይ ግዛት ምድሪቷ ከምትችለው በላይ ክርቲያን ወገኖቼን ስለጨረሷቸውና ዓለምም መጮኽ ስለጀመረ(በድሮን ጨፍጫፊዎቹ ኤሚራቶች ሰይጣናዊውን ጂሃዳዊ ግዴታቸውን ተወጥተው ወዲያው ነበር የዓሰብን ወደብ ለቅቀው ወጡ)ስለዚህ አሁን የቀረውን የትግራይ ወጣት ለመጨረስ ከትግራይ ግዛት መውጣትና ማስመታት አቀዱ። አዎ! ህወሓቶችና እነ ጄነራል ጻድቃን ከግራኝ፣ ከእነ አሜሪካና ቱርክ ጋር ተማክረው በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠረው የትግራይ ወጣትን ባዘጋጁልት 'አመቺ' ቦታ ላይ በድሮን ለመጨፍጨፍና ሬሳዎቹንም ስውር ወደሆነ ተራራማ ቦታ ወስደው በስውር ቀብረው በኋላ ለማቃጠል ነበር እስከ ደብረሲና ድረስ ሰተት ብለው የገቡት። የትግራይን ሬሳ ቀብሮ በኋላ ላይ የማቃጠሉ አረሜኒያዊ፣ ሲዖል የሚያስገባ ዲያብሎሳዊ ተግባር በምዕራብ ትግራይም፣ በራያ አካባቢም፣ ኦሮሞ በተባለው ክልልም፣ በሳውዲና የመን ጠረፍም እየተካሄደ መሆኑን እያየነው ነው።

በጽዮናውያን ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነቱ እንደጀመረ ይህን ጥያቄና መልስ አቅርቤ ነበር፤

ለመሆኑ ይህ ጦርነት ማንን ነው “የሚጠቅመው”?

☆ ፩ኛ. የምዕራቡን ኤዶማውያንን እና የምስራቁን እስማኤላውያንን (ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ እስላም፣ ኢ-አማኒ፣ ግብረ-ሰዶም)

ምክኒያቱ፦ ሁለቱም ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን አጥፍተው የራሳቸውን ዲያብሎሳዊ ርዕዮተ ዓለማት ማስፋፋትና በኢትዮጵያ የሚገኘውን የሕይወት ዛፍም ለሳጥናኤል ስም፣ ክብርና ዝና ሲሉ መውረስ ይሻሉና ነው።

☆ ፪ኛ. ዋቀፌታን/ኦሮሙማን

ምክኒያቱ፦ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን አጥፍተው የራሳቸውን ርዕዮተ ዓለማት ማስፋፋት ይሻሉና ነው። የፕሮቴስታንቲዝም አባት ማርቲን ሉተር ወደ ጀርመንኛ በተረጎመው መጽሐፍ ቅዱስ 'ኢትዮጵያን' 'ኩሽ' ብሎ ነው የጻፋት። ይህ ቀላል ነገር እንዳይመስለን። እ.አ.አ ከ 1837 እስከ 1843 ዓ.ም ባለው ጊዜ ፕሮቴስታንቱ ጀርመናዊ ዮኻን ክራፕፍ ኦሮሚያ የተባለውን ግዛት ለመመሥረት የተነሳሳው ክርስትናን ለማስፋፋት ሳይሆን፡ እንደ አንድ ፕሮቴስታንት የኢትዮጵያ ቀጥተኛ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለመዋጋት ነው። ለዚህም በወራሪነት ባሕርይ ከጀርመኖች ጋር ይስማማሉ በሚል ሃሳብ “ጋላ” ተብለው ሲጠሩ የነበሩትን ጎሳዎች ለማደራጀት በመነሳሳት በ 'ኢትዮጵያ' ፋንታ 'ኩሽ' የሚለው ትርጉም ያለበትን መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ ወደ ምስራቅ አፍሪካ/ኢትዮጵያ ተጓዝ፤ በዚህም የኦሮሙማ እንቅስቃሴን ጀመረው። ተልዕኮው ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ፀረ-ተዋሕዶ እና የክርስቶስ ተቃዋሚ ተልዕኮ መሆኑን ዛሬ እያየነው ነው። ዋናው ዲያብሎሳዊ ዓላማቸው፤ ኢትዮጵያን አፍርሰው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትንም በተለይ ከዐምሓራና ትግራዋይ በመንጠቅ “መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰችው ኩሽ እኛ ነን” የሚለው ነው።

“ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም”[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥፲]

☆ ፫ኛ. የዐምሓራ ብሔርተኝነትን

ምክኒያቱ፦ ከኦሮሙማዎች፣ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ተጋሩዎችንና ትግርኛን አጥፍተው ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን፣ ግዕዝን፣ ሰንደቁን፣ አክሱም ጽዮንን፣ ቅዱስ ያሬድና አቡነ አረጋዊን ከተቻለም መላው ትግራይንና ኤርትራን ወርሰው ለራሳቸው ብቻ ለማድረግ ይሻሉና ነው። በነገራችን ላይ፤ ኦሮሞዎች በኬኛ ቅዠታቸው ሙጭጭ ያሉበትንና “ፊንፊኔ/ ፊልፊሌ” የሚለውን ስያሜ ለአዲስ አበባ ፍልወሃ ክፍለ ከተማ እቴጌ ጣይቱ እንደሰጡት፤ “አማራ” የተባለውን የአማራ ከንቱ ብሔርተኞች ክልልን መጠሪያ ስም የሰጡት ደግሞ'ትግሬው' ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ነበሩ። የሕይወት ምፀት!

☆ ፬ኛ. የተጋሩ ብሔርተኝነትን

ምክኒያቱ፦ ኢ-አማንያኑ ሻዕቢያ እና ህዋሓት ቡድኖች ከኦሮሙማዎች፣ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን፣ ቅዱስ ያሬድን፣ አቡነ አረጋዊን፣ አባ ዓቢየ እግዚእን፣ ነገሥታቱን ኢዛናን፣ ዮሐንስን፣ ሰንደቁን፣ ግዕዝን፣ አክሱምን አጥፍተው በሃምሳ ዓመታት ውስጥ በተገኘ ጣዖታዊ ማንነት “ኢ-አማኒ የትግራይ ሶሻሊምዝ-ብልጽግና” ርዕዮተ ዓለምን በመከተልና የሉሲፈር ኮከብ ያረፈበትን የቻይና ሰንደቅም በማውለብለብ ከኤርትራ ጋር ለብቻቸው መኖር ይሻሉና ነው። በትግራይ የተካሄደው ጦርነት የግራኝ አብዮት አሕመድ እና የስብሃት ነጋ ጦርነት ነበር። መንግስቱን ለኦሮሙማዎች እንዳስረከቡት፣ ቤተ ክህነትንም ለእነ ኤሬቻ በላይ በማስረክብ ላይ ያሉ ይመስላሉ። በትግራይ ላይ የተከፈተውን ጦርነት የደገፉበት አንዱ ምክኒያትም ይህ ሊሆን ይችላል፤ ዋናው ፍላጎታቸው ግን የትግርኛ ተናጋሪ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን ልብ በመስበርና ተስፋ በማስቆረጥ፡ ተዋሕዶ ክርስትናን እና ኢትዮጵያን እንዲተው ማድረግ ነው። በነገራችን ላይ፤ ዛሬ የትግራይ ከንቱ “ትግራይ! ትግራይ!” ብሔርተኞች ለሚጮሁለት ክፍለሀገር “ትግራይ” የሚለውን መጠሪያ የሰጡት ድንቁ 'አማርኛ ተናጋሪ ጽዮናዊ' ኢትዮጵያዊ ንጉሥ አፄ ዓምደ ጽዮን ናቸው። የሕይወት ምፀት!

ሉሲፈራውያኑ እና  ወኪላቸው አብዮት አሕመድ ዓሊ ትግራይን ከኢትዮጵያ ገንጥለው የስጋ ማንነትና ምንነት ባላቸው ጠላቶቿ የምትመራዋን የዛሬዋን ኢትዮጵያን አፈራርሰው ከሞያሌ እስከ መተከልና ጎንደር ያለውን ግዛት ለኦሮሞዎች ለማስረከብ ተግተው በመሥራት ላይ ናቸው። ዐምሓራው የስጋ ማንነትና ምንነት ካላቸው ኦሮሞዎቹ ጎን ተሰልፎ የመንፈስ ማንነትና ምንነት ባላቸው ተጋሩ ወንድሞቹ ላይ በመቶ ዓመት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ጦርነት በማወጁ አብቅቶለታል! አክሱም ጽዮንን ክዷልና የሆነ ተዓምር ካልመጣ በቀር ምንም ተስፋ የለውም፤ በቅርቡ ሃገር አልባ ነው የሚሆነው። እነ ግራኝ እየሠሩ ያሉት ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያዊነታቸው፣ ከአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቃቸው እና ከተዋሕዶ ክርስትናቸው እንዲላቀቁ ብሎም አዕምሯቸውን ተቆጣጥረው፣ መንፈሳቸውን አድክመውና ሞራላቸውን ሰብረው ልክ እንደ “ኤርትራውያን” ለአውሮፓውያን አረጋውያን የኩላሊትና መቅኒ መለዋወጫ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። ከኦሮሞዎቹ ከእነ አብዮት አሕመድ ጋር ተናበው በመስራት ላይ ያሉት ህወሓቶች የዚህ ዲያብሎሳዊ ሤራ አካል ቢሆኑ አይገርመንም። ዋ! ዋ! ዋ!

በዓለማችን ያሉ ብዙ ሕዝቦች በተቻለ መጠን በሃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በባህልና በመልክ የሚመስሏቸውንና የሚቀርቧቸውን ሕዝቦች እየፈለጉ ማስጠጋትና መውደድ በጀመሩበት በዚህ ዘመን ትንሿ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔሮች ግን ጥላቻን አንግሦ አንዱ ከሌላው የሚለይበትንና የሚረቅበትን፣ አንዱ ሌላውን የሚጠላበትንና የሚያርቅበትን ሰበባ ሰበብ እየፈላለገ እርስበርስ መባላቱንና ውድቀቱን መርጧል። ሞቃዲሾን አልፎ ኪጋሊንና ካምፓላን፣ ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ኤደንና ሙስካትን “ የኛ ነበሩ! የኛ ይሆናሉ!” በሚል ወኔ ታላቅነትንና አርቆ አሳቢነትን እንደ ቀደሙት አያቶቹ ይዞ “ኢትዮጵያ ርስቴ” በማለት ፈንታ እራሱን አጥብቦና በጣም አውርዶ በወልቃይትና ራያ ሚጢጢ“እርስቶች” ላንቅው እስኪበጠስ ይነታረካል። በከሃዲዎቹ የሉሲፈራውያኑ ባሪያ ልሂቃኖቹ አዕምሮው እስኪጠብብ ድረስ መታጠቡ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ የለም።

የሕዝቡን ስነ-ልቦና በልተውታል፤ ስለዚህ “አዲስ አበባ ኬኝ” ይሉና መስቀል አደባባይን እና ጃን ሜዳን በመቆፈር የተዋሕዷውያኑን ሃሳብ በነዚህ ትንንሽ ቦታዎች ላይ ብቻ እንዲቀር ያስሩታል፣ ወደ ወልቃይት፣ ራያና ሑመራ ልጆቹን እየላከ ተጋሩ ወገኖቹን እንዲገድል፣ የራሱንም ደም እንዲያፈስ፣ የአክቲቪስቱ ሃሳብም በእነዚህ ትንንሽ ቦታዎች ብቻ ተወስኖና ታስሮ እንዲቀር፣ የቀረውም እንዲኮላሽና ሰፊዋን ኢትዮጵያን ከጠላቶቿ ነፃ ለማውጣት አቅም እንዳይኖረው፤ ብዙም እንዳይጠይቅ፣ በጥቃቅን ነገሮች ላይ ብቻ ጊዜና ጉልበቱን እያባከነ ለባርነት እንዲዘጋጅ አድርገውታል። ትልቅ ቅሌት! 

አንድን ሀገር/ሕዝብ ለመቆጣጠር ሉሲፊራውያኑ የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች፦

– ተስፋ ማስቆረጥ/ሞራል መስበር

– አለመረጋጋትን መፍጠር

– ዓመፅ መቀስቀስ

– መደበኛነትን/መረጋጋትን ማምጣት








Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment