የኢትዮጵያ ትንሣዔ | ኢራናውያን በከፍተኛ ቁጥር እስልምናን ለቀው እየወጡ ነው

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ኢራናውያን በከፍተኛ ቁጥር እስልምናን ለቀው እየወጡ ነው፡ በኢራን ውስጥ ከ፷/60 በመቶ በላይ መስጊዶች ተዘግተዋል፤ ከሰባ አምስት ሺህ/75,000 ዎቹ ሃምሳ ሺህ/50,000 ዎቹ መስጊዶች አሁን በኢራን ተዘግተዋል።

☪ የኢራን መስጊዶች ባዶ ናቸው!

ጥንታዊው የአክሱማውያን ክርስቲያን ኢትዮጵያ መንግሥት ግስጋሴ ለጊዜው እንዲቋረጥ ወሳኝ ሚና የተጫወተችው ፋርስ በእስልምና መቅሰፍት ተቀጥታለችና ብዙ ሚና አትጫወተም። ተወደደም ተጠላም ኢራን ከእስልምና ነፃ ወጥታ የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ አጋር ትሆናለች።

በቅርብ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በመካከለኛው ምስራቅ እና ኢራን በግማሽ የሚጠጋ ህዝብ ከእስልምና ጋር ያለውን ግንኙነት እየፈታ ነው።

ዛሬ፣ ብዙ ኢራናውያን/ፋርሳውያን ፥ እስካሁን ጌታችን በራዕይ እየታያቸው ያሉት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢራናውያን እስልምናን ትተው የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ለመሆን እየበቁ ነው። በዚህም ምክንያት በኢራን ከሚገኙት 4 መስጊዶች 3ቱ ተዘግተዋል። ከ 80% በላይ የሚሆኑት ኢራናውያን ወጣቶች የሙስሊም እለታዊ ሶላቶችን እንደማይሰግዱ አሳውቀዋል። 
ከሁለት ወራት በፊት የኢራኑ ከፍተኛ የሃይማኖት አባት መሐመድ አቦልጋሰም ዱላቢ ኢራን ውስጥ ያለው እስልምና ደካማ ነው ሲሉ 50,000 መስጂዶች ተዘግተዋል።

በኩም ሴሚናሪ የሺኢዝምን ህግጋት እና መርሆች የሚያስተምሩ አያቶላ ሰይድ ሙሐመድ-ጃቫድ አላቪ ቦሩጀርዲ ከዲባን ኢራን [ኢራን ሞኒተር] ድረ-ገጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሲናገሩ በኩም ውስጥ ክርስትናን ለተቀበሉ ሙስሊሞች ቤት-ተኮር ቤተክርስትያኖች እንዳሉ ጨምረው ገልጸዋል።

"እኛን ትተው ክርስቲያን ለሆኑት ወጣቶች ሀላፊነት ይሰማኛል፤ እሱ የሺዓ ልጅ ነው እና ወደ መንጋው ልመልሰው ይገባል፣ ልተወው አልችልም።" አያቶላ አላቪ-ቦሩጀርዲ ተናግረዋል.
ወደ ሌላ ሃይማኖት መለወጥ በእስልምና የተከለከለ ነው እና የኢራን መንግስት የእስልምና አምልኮን እንጅ ሃይማኖትን አይፈቅድም ወይም እውቅና አይሰጥም።
በመንፈሳዊ አነጋገር፣ ዋናው ምክንያት፣ ፋርስ በእስልምና የተወረረችበት ምክንያት አሁን የመን ተብሎ የሚጠራው ግዛት ነው። እስልምና አክሱማዊት ኢትዮጵያ ጠላቶቿን ለማዳከምና ለማጥፋት ያስችላት ዘንድ የፈጠረችው አምልኮ እና እንደ ወረርሽኝ የምትጠቀምበት መቅሰፍት ነው። የሚል እምነት አለኝ። በዚህ ረገድ የጥንቷ ፋርስ እና መጽሐፈ አስቴር ጠቃሚ ትምህርት ያስተምሩናል።

በ፮/6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በክርስቲያን አክሱማዊት ኢትዮጵያ እና በፋርስ መካከል ብዙ ጦርነቶች ነበሩ። እነዚህ ጦርነቶች በሳሳኒያ የፋርስ ኢምፓየር እና በአክሱም ኢምፓየር መካከል በደቡብ ዓረቢያ (የአሁኗ የመን) እየተመናመነ ያለውን የሂሚያራይት መንግሥት ለመቆጣጠር በ፮/6ኛው ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ የተካሄዱት የተራዘመ ተከታታይ የታጠቁ ጦርነቶች ነበሩ። እ.ኤ.አ. በ 570 በሐድራማውት ጦርነት ወሳኝ ድል ከተቀዳጀ በኋላ የሳሳኒያ ጦር ዘምቶ ሰነዓን ከበበ በኋላ አክሱማውያን ከዓረብ ባሕረ ገብ መሬት በብዛት ተባረሩ። ፋርሳውያን የአዲሱ የሳሳኒያ የየመን ግዛት ገዥ አድርገው የቀድሞውን የሂሚያራይት ንጉስ ሰይፍ ኢብን ዲይ ያዛንን ሾሙት። ነገር ግን ያዛን በነገሠ አራት አመት በኢትዮጵያውያን አገልጋዮቹ ተገድሏል፣ ከዚያም አክሱማውያን እንደገና ስልጣናቸውን በክልሉ አቋቋሙ። የያዛን ሞት ተከትሎ የሳሳኒያ ጦር ለሁለተኛ ጊዜ ወረራ በማድረግ በ575–578 የመንን በድጋሚ ድል በማድረግ የአክሱማውያን አገዛዝ በዓረብ ምድር ማብቃቱን አሳይቷል።

በዓረቢያ እና ፋርስ ተስፋፍቶ የምናየው የእስልምና ወረርሽኝ፤ ዓረቦቹና ፋርሶቹ ብሎም ቱርኮቹ በክርስቲያን አክሱም ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸሙት ግፍና መከራ ያስከተለው መቅሰፍት ነው። 100%። በሃገራችንም ዋቄዮ-አላህ ባሪያዎችም ላይ ተመሳሳይ መቅሰፍት ተከስቶ እየታየ ነው። ሁሉም በጋራ ሲወገዱ እናት ኢትዮጵያ ነፃ ትሆናለች። በቅርቡ!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment