✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
❖ የገሪማ ወንጌሎች በትግራይ ገዳም ውስጥ ለ ፲፻፭፻/1,500 ዓመታት የሰው ልጅ ታሪክ ከተረፉ በኋላ አሁን በጣም ከባድ ሥጋት እየገጠማቸው ነው፡፡
❖ ከግራኝ አሕመድ ኢብን ኢብራሂም አል-ጋዚ ወረራ ጀምሮ ከምንም ነገር በላይ በኢትዮጵያ ያለው ጦርነት በኢትዮጵያ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች ላይ የበለጠ ጥፋት/ውድመት አስከትሏል።
❖ በዓድዋ፤ ትግራይ በጥንታዊው የቅዱስ አቡነ ገሪማ ገዳም የሚኘው መጽሐፍ ቅዱስ ከመጀመሪያው የእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ (KJV – King James Version) በ፰፻/800 ዓመት ቀደምትነት እንዳለው ሳይንሱ ሳይቀር ማረጋገጫ ሰጥቷል።
"ከአምስት መቶ ዓመታት በኋላ፤ ከግራኝ አህመድ ቀዳማዊ ዘመን በኋላ እንዲህ ዓይነት ውድመት በኢትዮጵያ ሲታይ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው" እያሉን ነው ባዕድውያኑ እንኳ። በእውነት ባዕዳውያኑ "ኤትዮጵያውያን ነን፣ ተዋሕዶ ነን" ከሚሉት ይልቅ ስለ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ቅርሶቻችን በይበልጥ ተቆርቋሪዎች ሆነው ይታሉ። ዋይ! በለዓለማችንና ለመላው የሰው ልጅ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ታሪካዊ ቅርሶችና ኃብቶች የሚገኙባትን ትግራይን የኢትዮጵያና ተዋሕዶ እምነቷ ጠላት እንዲጨፈጭፍላቸው ፈቃድ የሰጡት "ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ተዋሕዶ ክርስቲያን ነኝ" ባዮች አሁን የት አሉ? ስንቱስ ነው እንኳን ለአባቶቹ ቅርስ ለሃገሩ የማንነት መገለጫ ለመጋደል፤ ጉዳዩ አሳስቦት "ቅርሶቻችን እየጠፉ ነውና ጦርነቱን አቁሙ!” ለማለት ኢትዮጵያዊ፣ ክርስቲያናዊ ድፍረት ያለው? ፲/10 % የሚሆን አይመስለኝም።
ባለቤቱን ሳይንቁ አጥሩን አይነቀንቁ" እንዲሉ፤ ለሦስት ዓመታት ያ ሁሉ ግፍ በቤተ ክርስቲያንና ልጆቿ ላይ ሲሰራ፣ ቅድስት ሀገር አክሱም ጽዮን ትግራይ ስትጨፈጨፍ ለአንዴም እንኳን ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት የተሳነው ሙት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሙቀቱ በዋቄዮ-አላህ ልጆች ተለክቶ ያው መስቀል አደባባይን ሊወርሱለት ዱብዱብ በማለት ላይ ናቸው። ለመሆኑ ከሁለት ሳምንታት በፊት ዐምሓራው ሲያሰማው የነበረው ጩኸት የት ደረሰ? ሁሉም ጭጭ፤ አይደል! እንዲያውም ግራኝ ይባስ ብሎ ኮሚሽነሩን በመገደል የአማራውን ወንድ ወኔ በድጋሚ ነጠቀው። አዎ! ከእነ ጄነራል አሳምነው ግድያ በኋላ ያየነው ነው። የዲያብሎስ ጭፍራው ግራኝ አብዮት አሕመድና አማካሪዎቹ በስነ-ልቦና ጨዋታው ተክነዋል።
Blogger Comment
Facebook Comment