✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ህወሓቶች ሉሲፈራዊ ሰንደቃቸው ለማስተዋወቅ የሄዱበትን ርቀት እንመልከት፤ እንዲያውም ህወሓቶች የሚኖሩት ይህን አስቀያሚ ሰንደቅዓላማ ለማስተዋወቅና ሉሲፈርን ለማንገስ ብቻ ነው ብል አላጋነንኩም። በፖለቲካዊ፣ ርዕዮተ ዓለማዊና ወታደራዊው 'ዘመቻቸው/ ትግላቸው' በኩል ያቀዱትን ሕዝበ ክርስቲያኑን የማስጨፍጨፍና የማስራብ ግባቸውን መትተዋል (በስጋዊ ሕይወት)። አሁን ደግሞ በተረፉት የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ሰርገው በመግባት ጥንታዊውን ባህል እና ሃይማኖትን ለመበከል ብሎም የሕዝቤን ነፍስ ለመንጠቅ ተግተው በመሥራት ላይ ናቸው። ለዚህም ሉሲፈራዊን የህወሓት ሰንደቅን በአልባሳቱ፣ በጃንጥላዎቹና መስቀሎቹ፣ በቤተ ክርስቲያን እና ገዳማት እንዲሁም ንዋያተ ቅድሳት በኩል እያሰተዋወቁ ነው። በጦርነቱ ወቅት እንኳን ዋናው ተግባራቸው ይህን የሉሲፈር ሰንደቅ በየቦታው ማውለብለብ ነበር። አክሱም ጽዮን እንኳን አልተረፈቻቸውም።
❖ በደንብ እናስተውል፤ ለዘመናት፡ በትግራይ የሚገኙት ገዳማትና ዓብያተክርስቲያናት፤ አክሱም ጽዮን፣ ደብረ አባይ፣ ደብረ ዳሞ ወዘተ ሁሉም በጽዮን ማርያም መቀነት አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ያሸበረቁ ገዳማት ናቸው። ታዲያ ይህን መለኮታዊ ፀጋ ከትግራይ ሕዝብ ለመንጠቅና ተዋሕዶ ክርስቲያን ሕዝቤንም ከአምላኩና ከጽዮን እናቱ ጋር ለማጣላት ብሎም ሉሲፈርን ለማንገስ፤'ሰለጠንን' ባዮቹ “ኢ-አማንያኑ” የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ህወሓቶች፣ ሻዕቢያ፣ አሕዛብ የዋቄዮ-አላህ ልጆች፣ ከሃዲ መናፍቃን ሁሉ የዘር ማጥፋት ጦርነቱን በሕብረት ተናብበው በመክፈት እነዚህን አብያተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን በተቀናጀ መልክ ነበር ወዲያው ያጠቋቸው። ብዙም ሳይቆዩ የሉሲፈርን ሰንደቅ ሰቀሉ፣ ክቡሩን የጽዮንን/የንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስን ሰንደቅ በሉሲፈር ሰንደቅ ተኩት።
ለመሆኑ ጨርቁ የት ነው የሚመረተው? ከየት እያመጡት ነው? ምናለ ለተራበው ወገኔ እንጀራ ቢጋግሩለት?
ከተራበው ሕዝቤ በሰረቁት ስንዴ የፋፉትና ከዓረብ በመጣ ውስኪ በመሳከር ላይ ያሉት ወንጀለኞቹ እነ ጌታቸው ረዳ ከልባቸው ተጸጽተው ለንሰሐ ወደ ገዳም በመግባት ፈንታ በለመዱት ዲያብሎሳዊ መንገድ ሉሲፈርን ለማንገስ ሲሉ “መንበረ ሰላም” የተሰኘውን ቡድን ካባ መልበስ መርጠዋል። ይህ ደግሞ እጅግ በጣም ከባድ ኃጢዓትና ከሁሉም የከፋ ወንጀል ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment