ሮማኒያ | ሰባ አምስት ሺህ/ 75,000 ምዕመናን ወላዲተ አምላክን በኒኩላ ገዳም አከበሯት


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

በኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሮማኒያ፡ ሰባ አምስት ሺህ/ 75,000 ምዕመናን ወላዲተ አምላክን በኒኩላ ገዳም አከበሯት 

በሮማኒያ፡ ሰባ አምስት ሺህ/ 75,000 የሮማኒያ ኦርቶዶክስ ምዕመናን ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክን የእረፍት በዓል ለማክበር ወደ ክሉጅ ወረዳ ኒኩላ ገዳም ተጉዘዋል።

ብዙ አማኞች ከበዓሉ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ በገዳሙ የሚገኘውን ተዓምረኛ/አስደናቂ የእምቤታችንን ስዕል/አይኮን ለማክበር እና ከቤት ውጭ ባለው መሠዊያ ላይ በሚከበሩ አገልግሎቶችና መርሃ ግብሮች ላይ ለመሳተፍ መጥተው ነበር ሲል ባዚሊካ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

እ.አ.አ በ1699 በዚህ ታሪካዊ ገዳም የሚገኘው የወላዲተ አምላክ ስዕል ለሦስት/3 ሳምንታት ያህል ሲያለቅስ እንደነበር ያስታውሳል። ዝግጅቶቹ የጀመሩት ከአንድ ቀን በፊት ነበር። ሰልፉ የተካሄደው በክሉጅ ከተማ በክቡር የከተማው ጳጳስ ሜትሮፖሊታን አንድሬ እና በምዕራብ እና በደቡብ አውሮፓ ታላቁ የከተማው ጳጳስ/ሜትሮፖሊታን ዮሴፍ ነበር።

ከኮሚኒስት ዘመነ መንግስት የፖለቲካ እስረኞች የጅምላ መቃብር ባለበት መቃብር ፊት በመንገዱ ላይ ሰልፉ ቆሞ የሃይማኖት መሪዎች እና ምዕመናን ለድናቸው ፀልየዋል። ለበዓሉ የምሽት ጸሎት ከተደረገ በኋላ ምዕመናኑና ካሃኗቱ በገዳሙ የተዓምር ሠሪውን የወላዲተ ዓምላክ ሥዕልን ተሸክመው ባካባቢው ሰልፍ አካሂደዋል።

ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጠዋት ሰላሳ ሺህ/ 30,000 የሚጠጉ ምዕመናን በቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።

በድርሳናቸው ወቅት የከተማው ጳጳስ አንድሬ ታማኞች ለሌሎች የሚያሳዩትን የግድየለሽነት ኃጢአትን እንዲያሸንፉ እንዲህ በማለት አበረታቷቸዋል፡-

"ወላዲተ አምላክ/የእግዚአብሔር እናት፡ ልጇ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የነገረንን እንድናደርግ እና ልንረሳው ስለማይገባን ክርስቲያናዊ የምሕረት ሥራዎች ታስተምረናለች። ክርስቲያናዊ ምሕረት ንድፈ ሃሳብ አይደለም፣ ነገር ግን በትናንሽ እና በትልቁ በተግባር የሚታይ ሥራ እንጂ። ራሳችንን የምንጠይቀው ጥያቄ፡ የክርስቲያን የምሕረት ሥራዎችን ተግባራዊ ማድረግ ለምን ተሳነን? ለምንድነው ሰዎች እርስ በርሳቸው ደንታ ቢሶች፣ ከቤተክርስቲያን፣ ከእግዚአብሔር እና ከቅዱሳን የራቁት? ምክንያቱ አንድ ይሆናል፡ ይህም 'ግዴለሽነታችን' ነው።

በዚህ ዓመት ወደ ኒኩላ ገዳም የመጣችሁ ሁሉ ደስተኛ መሆን ትችላላችሁ። አንዳችሁ ለሌላው ግድየለሽ መሆናችሁን ብቻ ማቆም አለባችሁ፣ ምክንያቱም ከሌላው የትኛው ክርስቶስ እንደሆነ አታውቁምና።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment