የአምኃ ኢየሱስ ገብረ ዮሐንስ ቁጥር ፰ መልእክት

ለሃይማኖታዊ ጥያቄአችሁ መልስ የተሰጠበትና ለሌሎችም ሰዎች ወቅታዊ መልእክት ያስተላለፍኩበት ከመደበኛ መልእክቴ ውጭ ተጨማሪ ትምህርታዊ የሆነ የጽሑፍ መልእክት ነው። ግንቦት ፳፯ ፪ሺ፲፫ ዓ ም __በል እንግዲህ ""እውቀትን የምትፈልግ ሁሉ አንብብ። አፍህ የሰፋው ደግሞ ለፍልፍ""። ""Land of the Blacks..............."" ካነበባችሁ ከፊታችሁ ታገኙኛላችሁ። ከፊታችሁ የሚለው (ሰምና ወርቅ) ነው። ____ፍሬ ነገር ወደ ሆነው ወደ ዋናው መልእክቴ ከመግባቴ በፊት ግን ከመላው ኢትዮጵያ ገዳማትና ገዳማዊያን አባቶች ስለ ንጉሥ ቴዎድሮስ መምጣት ሐሰት እንደሆነና እንዲህ የሚባል ንጉሥም እንደሌለ መናገራቸዉንና በገዳማቸው ማኅተም አስደግፈው ለመላው ክርስቲያን ሕዝብ ሁሉ ጻፉ የተባለውንና እንደጻፉ የሚገልጸውን በውስጥ መስመሬ የላካችሁልኝን ሰይጣናዊ ደብዳቤ ሁሉንም አይቸዋለሁ። እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ? አምኃ ኢየሱስ ከሰይጣኒዝም ወያኔ ዘመን ጀምሮ በገዳም ውስጥ መኖር አቆመ። ለምን ይመስላችኋል? መልሴ፦ ገዳም፤ ገዳም ሳይሆን ጉዳም ስለሆነብኝ ነው። የሚገባችሁ ከሆነ ይግባችሁ። ሁሌ ሰንበት ማለት ቅዳሜና ዕሁድ ነው ስላችሁ አልኖርም። ሌላም ነገር ልጨምራችሁና ብታምኑም ባታምኑም እኔ ቤተ-መቅደስ መግባት ብቻ ሳይሆን ለግሌ መቁረብም በራሴ ፈቃድ ያቆምኩ ገና ወያኔዎች እንደገቡ በለጋ እድሜየ ነው ብላችሁ ምን ትላላችሁ? እንግዲህ እኔና ቤተ-መቅደስ፣ እንዲሁም ቁርባን የምንገናኘው በንጉሡና በጳጳሱ ጊዜ ነው ማለት ነው። ከዛ ወዲህማ የማይታሰብ ነው። ለምን? እንዳትሉኝ። ራሴ አውቃለሁ። የወሬ ሱስ ስላለባችሁ ከፈለጋችሁ ልንገራችሁ? ኧረ እሺ! ""በልጅነት እድሜየ ምክንያት ንጽሕናን ጠብቄ፣ ከሴት ርቄ መኖር ስላቃተኝና እልም ያልኩ የለየልኝ ልክስክስ ዘማዊ ሆኜ ስለተገኘሁ ተባርሬ ነው"" በቃ ይኸ ነው። ደስ አላችሁ? በሉ ሳትስቁብኝ፣ ሳትረግሙኝ፣ ሳትጠሉኝ፣ ሳትጠቋቆሙብኝ ስለ ደካማነቴ በደንብ ጸልዩልኝ። የደከመውን ማበረታታት፣ የወደቀውንም ማንሳት እንጅ ከዛው ላይ መቀጥቀጥ ምን ይጠቅማል? እባብ ነው እንዴ? እናም ገዳማዊያንን ልተዋቸውና ይህንን ደብዳቤ ከገዳም በማኅተም አስደግፈው አወጡት፣ አመጡት፣ በተኑት የተባሉት ሰዎች እኮ በቅዱሳንና በመጽሐፍ የተነገረውን፣ የተጻፈውን፣ የተቀመጠውን፣ የታወቀውን፣ የታመነውን በመካድ ክህደታቸው ሥላሴን ከካደው ከሳጥናኤል ዲያብሎስ ክህደት የበለጠ ነው። እንዲሁም ክርስቶስን ከካዱትና ከሰቀሉት አማጽያን ካህናተ አይሁድ በብዙ እጥፍ የበለጠና የከፋ ነው። ደግሞም ሕዝበ አይሁድስ ቢክዱትም ለሙሴ ሕግ በመቅናትና ክርስቶስ የሚወለድበት ጊዜው ገና ነው በማለትና እንዲሁም የሚወለደው ከእኛ ወገን ብቻ ነው እንጅ የሌላ ነገደ ትውልድ የሆነ አይቀላቀልበትም በማለትና እንዲሁም ባለማወቅም ጭምር፣ እንዲሁም ቀድሞ በነብያት አባቶቻቸው የተነገረባቸው ትንቢት ይፈጸምባቸው ዘንድ ግድ ስለነበር ነው። እነዚህ የዛሬዎቹ የቁም ሰይጣኒስቶች ግን ለክህደታቸው በደል ምክንያት የራሳቸው የልባቸው ክፉ ኃጢአት ነው እንጅ ሌላ ምክንያት የላቸውም። ""የያዛችሁት የትችትና የነቀፋ ዓላማችሁና ግባችሁ ደግሞ በአምኃ ኢየሱስ ላይ ሆነ በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ማኅበር ላይ ያላችሁን ሰይጣኒዝም የሆነ የልብ ጥላቻችሁን ለመግለጽ ብላችሁ ነገር ፍለጋ ከሆነ ደግሞ የንጉሥ ቴዎድሮስንና የአቡነ ፀሐይን ማንነት ከእኛ ጥላቻችሁ ጋር ማስገባትና እናንተ ክዳችሁ ሌላውን ማስካድ ምን ይባላል?"" ያለመማርና ያለማወቅ ድንቁርና! ድድብና! ዕውርነት! ዝንጉነት! ስሑትነት ይባላል። ገባችሁ? ምን ይገባችኋል! ገደል ገባችሁ እንጅ። ጊዜውና ማስሚዲያው ተመቸን ብላችሁ ታጎሩበታላችሁ። መንጋ ዛራም!!! አንባብያን ሆይ! እኔ አሁን እየተናገርኩ ያለሁት ስለ ንጉሡና ስለ ጳጳሱ ማንነት እንጅ ስለእኔ ማንነትና ስለ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ማኅበር ማንነት አለመሆኑን ይታወቅልኝ። ለእነሱ ሰይጣኒስቶች የአፋቸው መክፈቻ የሚሆን ምንም አይነት መንገድ አልሰጣቸውም። እናም ጤነኛ የሆናችሁ ክርስቲያኖች ሆይ፦ በሐሰተኞች ሳይሆን በእውነተኞች ገዳማዊያን አባቶቻችን ስም ሐሰትንና ክህደትን የሚነግዱ እነዚህ ሰይጣኒስቶች ንጉሥ ቴዎድሮስን እነሱ ክደውና ገፍተው አያስቀሩትም። እኛም አምነንና ስበን አናመጣውም፤ እግዚአብሔር እንጅ። እነዚህ ምናምንቴዎች ኃጢአትንና በደልን ጠጥተዉ ጠጥተዉ በመስከር ቢለፈልፉ ልፍለፋቸውን ለምን ትሰማላችሁ? ሰካራምን ሰካራም ብላችሁ እንደምታልፉት ሁሉ እነዚህንም ሰይጣኒስቶች ሰይጣን! ብላችሁና ገጻችሁን አማትባችሁ ማለፍ ብቻ ነው። ሌላ ነገር መናገር አያስፈልግም። በዚህ ዙሪያ ደግሞ ዋናው ለፍላፊ ዲያቆን ተብየው ሰይጣኒዝም ዓባይነህ ካሴ ነው። በሆነ ዜና ማሰራጫ ሰምቸዋለሁ አይቸዋለሁ። እሱ ማለት እኮ ቃሉና ተግባሩ ይቅርና የፊቱ ገጽ ሙሉ በሙሉ ልክ መለስ ዜናዊንና አለቃውን ዲያብሎስን ነው የሚመስለው። እስቲ አይገባህም እንጅ የሚገባህ ከሆነ አንድ በጣም ቀላል የሆነ የአማርኛ ህብረ-ቃል ሰምና ወርቅ ልስጥህና ከራስህ ጋር አውራ። እውነተኞችን ተዋቸው። ለሰምና ወርቁ ቃሌ ግን ዋናው ምክንያቴ እሱ ቢሆንም ለእናንተም ይጠቅማልና ተማማሩበት። ___አሳምረኝ ብለህ ጌታን ስትለምነው ___መልሱንም ሳይነግርህ አበላሸህ ምነው? ___ጌታ ካሳመረህ ብዙ አበላሸህ። እናማ ባታውቋቸዉ ነው እንጅ እነዚህ እኮ እከክ ናቸው። ከእከክም የሰውነት እከክ ሳይሆኑ ሰይጣኒስት የመንፈስ እከክ ናቸዉ። ስለዚህ የሰይጣኒስቶችን እከክ ወደራሳችሁ ላለማጋባት ሰይጣናዊ ቃላቸዉን አለመስማት ነው። ከዚህ ውጭ ማናችሁም ብትሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ስለ ንጉሡ ምንም ነገር ብትሰሙ ደግማችሁ ደጋግማችሁ ስለ ንጉሥ ቴዎድሮስ ማንነትና አመጣጥ ንገረን አስረዳን እንድትሉኝና እንድትጨቀጭቁኝ አልፈልግምና ተጠንቀቁ። አስቀድሜ እኮ በቂ ነገር ነግሬአችኋለሁ። ቀሪውንና ዋናውን ደግሞ ሌላ ጊዜ ብየ ባለፈው ነገርኳችሁ። ታዲያ የማንንም ሰይጣኒዝም ርኩስ ቃል በሰማችሁ ቁጥር እኔን በመጠየቅ ለምን ታደክሙኛላችሁ? የማትረቡ ተጠራጣሪና ተስፋ-ቢስ ከሆናችሁ ደግሞ እነሱን ማመን፣ መቀበልና መከተል፤ እኔን ደግሞ ሳይጨልምባችሁ ቶሎ ብላችሁ በጊዜ ለቀቅ አድርጋችሁ መራቅ ብቻ ነው። በሉ ወደ ዋናው መልእክቴ ልምራና ላስገባችሁ። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። ""ወንጀለኛን"" ""በሐሰት ድጋፍ ማዳን አይቻልም""። ____ይድረስ ""ለደም ሰው"" ጠበቃወች ሆናችሁ በ Mereja TV ለምትጮሁት ሰዎች በሙሉ። ዘመድ-ኩን 'ን' እንኳ አልፈርድበትም፣ ከዚህ ግባም አልለውም። እንዲያውም መካሪ ባለመኖሩ አዝንለታለሁ እንጅ። በተለይ ግን በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን፣ በጽዮን ማርያም ጽዮናዊያን ለተባላችሁት ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያን ወንድሞቼ ለሀብታሙ አያሌውና ለኤርምያስ ለገሰ፦ በቅዱሳን ሐዋርያት አምላክ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለሁለተኛና ለመጨረሻ ጊዜ የሆነውን መልእክቴን የጻፍኩላችሁ ኢትዮጵያዊው ጽዮናዊ ክርስቲያን ወንድማችሁ አምኃ ኢየሱስ ገብረ ዮሐንስ ነኝ። ከዚህ በማስለጠቅ ከላይ ይድረስ ብየ በጀመርኩልህ መሰረት ነገሬን የምለጥቀው ባለፈው በአምስተኛው የጽሑፍ መልእክቴ ላይ ስለ አባ ማትያስ ማንነት በሚመለከት ጉዳይ አንተ ስትናገር ስለሰማሁህ እኔም ንግግርህ ትክክል እንዳልሆነና ስለ አባ ማትያስ የምትናገረውን ነገር ማስተካከል እንዳለብህ ጠቁሜህ ነበር። ሆኖም ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ስንባል ውድቅ የሆነ የአስተሳሰብ ችግር ተጠናውቶን ስለሚኖር አንተም ያ ችግር ተጠናውቶህ ነው መሰለኝ ያችን ጥቆማየን ከንቱ በሆነ ባልሸነፍም ባይነት በሚመስል መልኩ በሌላ ቀን ""ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቀዳሚ ግብሩ ወንጀለኛ እንደነበርና ኋላ ግን ከተመለሰ በኋላ የቀደመ ወንጀሉ እንዳልተቆጠረበትና እንደቀረለት ባጭር ቃል ለመናገር ስትሞክርና በዚህም አያይዘህ አንተ ብፁዕ ወቅዱስ.......የምትላቸው አባ ማትያስም የቀደመ ወንጀል ቢኖራቸውም እንኳ ከተመለሱ በኋላ ግን እንደማይቆጠርባቸውና የፊተኛውን ወንጀልም ማሰብና መመልከት እንደሌለብን ከቅዱስ ጳውሎስ ማንነት ጋር አነጻጽረህ ለመናገር ስትዳፈር ስሰማህ እጅግ በጣም አዘንኩብህ፣ አዘንኩልህ። ስለሁለት ነገር። ሀ/ በ ፪ሺ ፰ ዓ ም ጎንደር ላይና ባሕር-ዳር ላይ ""ሀብታሙ አያሌው ይፈታ፣ ሀብታሙ አያሌው Free......"" እያልን በእውነት በመጮሃችን በእነ አባ ማትያስ የውጭ ዝምተኛነትና የውስጥ አባሪ ተባባሪነት ጭምር በሰይጣኒዝም ወያኔና ብአዴን መንግሥትና ታጣቂ ጦር ስንትና ስንት ወንድሞቻችን እንደ ዱር ታዳኝ አውሬና እንስሳ ሆነው በጥይት እየረገፉ መቅረታቸዉን ረስተኸው ይሆን? ወይንስ ንቀኸው ይሆን? ወይንም ክደኸው እንደሆን ለአሁኑ ባላውቅም ዛሬ ግን አንተ ስለ አባ ማትያስ ማንነት በመልካም ነገር የምትናገረውን ነገር እንድሰማህ በሰዎች ጠቋሚነት ሳይህና ስሰማህ ባንተ ላይ ከማዘን አልፌ ተርፌ በዓይነ ሕሊናየ የሚመጣብኝና የሚታየኝ ገና ለገና በተዋህዶ ሃይማኖትህና በክርስትናህ ስም ብለህ አንተም የአባ ማትያስ ጠበቃ በመሆንህ ያለ ቀደምት ክፉ ሥራህ ልክ እንደ ደም አፍሳሽ ወንበዴዎች መስለህ መታየትህ በጣም ያሳዝናል። በል ግፋበት በርታ። የባለ ደም ምስክር በመሆንህ ግን የንጹሐን ደም ይፋረድሃል። ስላንተ ጩኸው የሞቱት ሁሉ ገነት ውስጥ ናቸዉ። አንተ የምትዋቀስለት አባ ማትያስ ግን ሲኦል ነው። ጻድቅ አማላጅ ሆነህ ከጌታችን ፍርድ ስታድነው እናይሃለን። ለ/ ከየትኞቹ የብሉይና ሐዲስ ኪዳን ሊቃውንት መምህራን እንደተማርከውና እንዳወቅኸው ባላውቅልህም የቅዱስ ጳውሎስን የቀደመ ስሕተትና የኋላ መመለስ ከባለ ደሙ ከአባ ማትያስ የወንጀል ጥፋት ጋር ለማመሳሰል ደፍረህ ስትናገር ስሰማህ በጣም ነው ያዘንኩብህና ያፈርኩብህ። ደጋግመህ ተምሬአለሁ ስትል ሰምቸሃለሁና። የወንጌሉን ትምህርት ግን አውቃለሁ ብለህ የምትናገረው ለኛ ነውን? ወይስ ለማይሞች ምእመናን ነው? በጣም ትገርመኛለህ። እናማ ቅዱስ ጳውሎስ ከመመለሱ በፊት የስሕተቱ ጥፋት ምን እንደነበረ ማንም ማይም የሚያነበው ነጠላ ንባቡና ጥሬ ቃሉ አዎ ከዛው ከመጽሐፉ ላይ አለ የታወቀ ነው። ስህተቱም በምን ምክንያት እንደነበረ አዎ ታውቀዋለህ። ከዛው በነጠላው ቃል ያለ ነውና። እናማ የአባ ማትያስን የቀደመ ጥፋት ከቅዱስ ጳውሎስ የቀደመ ስሕተት ጋር አዛምደህ ለመናገር እንዴት ደፈርክ? ከነማንና የትስ ምን ተብለህ ብትማር ነው? አባ ማትያስ አልተመለሰም እንጅ ቢመለስ እንኳ ከቅዱስ ጳውሎስ መመለስ ጋር አዛምደህ ለመናገር እንዴት ደፈርክ? ወንድሜ ሀብታሙ ሆይ፦ ቅዱስ ጳውሎስ ከመመለሱ በፊት ወንጀለኛ የነበረ ቢሆንም ቅሉ ከተመለሰ በኋላ ግን እስከ ዕለተ ሞቱ (እረፍቱ) ድረስ ከማስተማሩ በተረፈ ለሦስት ምስጢር በመከራ ላይ እንደኖረ ተምረሃልን? ታውቃለህን? ይህንን አሁን ልዘረዝርልህ ጊዜ የለኝም። ቢኖረኝም አልፈቅድም። ከዛው ቲኦሎጂ ኮሌጅ ተብየው ደንቁሮ ያደንቁራችሁ። ከለየላቸዉ መናፍቃን ጋር ልዋጋ? ወይስ በትንሽና በቀላል ስሕተትህ ምክንያት ካንተ ከሰማዕቱና ከየዋሁ ክርስቲያን ወንድሜ ጋር ልዋጋ? ስለ ሀገርና ስለ ሕዝብ.......ብለህ የጠጣሃውንና ያሳለፍከውን የመከራ ጽዋ እኮ እኛ መቸም ቢሆን ልንክደው ይቅርና አንረሳውም። ይሁንና በአባ ማትያስ ጉዳይ ግን በማታውቀው ጉዳይ ገብተህ ልባችንን አደማሃው። እውነቱን ልንገርህና አባ ማትያስን ከደገፍከው ካንተ ይልቅ ማኅበረ-ቅዱሳን የሚባለውን የጽዋ ማኅበር ማንነቱን ይፈተሽ ያለውና አንተ የነቀፍከውና የተቸኸው ሲሳይ አጌና በእኛ ዘንድ ትልቅ ክብር አለው። ምስጢሩም ሁሉ ወደፊት ይወጣልና። እናማ አባ ማትያስ ነው ከተመለሰ በኋላ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በሦስት ምስጢር መከራ ሲቀበል የኖረ???? የትናንቱና የእስከዛሬው ሀገራዊይና ሕዝባዊ ሰማዕት የነበርከው አሁን ግን ያንን ሁሉ ክብርህን በአባ ማትያስ ምክንያት እየጣልከው ያለኸው ወንድሜ ሀብታሙ ሆይ፦ እስቲ ቅዱስ ጳውሎስ ከተመለሰ በኋላ እስከ ዕለተ ሞተ-ሥጋው ድረስ ስለ ሦስት ነገሮች ብሎ ከፈጣሪ ሲቀበላቸው ከኖረው መከራዎቹ አንተም ሆንክ ሌላው አንባቢ ሁሉ ከምታውቁት ነጠላ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ከሆነውና ከማታውቁት ከትርጉም ትምህርቱ ውስጥ ጥቂት ልጋብዝህና ከእንግዲህ ወዲያ በዚህ ዙሪያ ዳግም ስላንተ ምንም ላልናገር በዚኸው ልሰናበትህ። ሀብታሙ አያሌው ከአባ ማትያስ ወንጀልና መመለስ ጋር ያነጻጸረው ብርሃናተ-ዓለም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በፈጣሪ ምርጫና ፈቃድ ወደ ራሱ ከጠራውና ከመለሰው በኋላ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ከተቀበላቸው መከራዎች በጣም በጣም በጥቂቱ እነሆላችሁ። ___በጠላቶቹ በአንድ ቀን ብቻ ፪ መቶ ጊዜ ተገርፏል። ሦስት ቀን ሳያቋርጡና ሳያርፉ እንደ ዳጉሳ ውቂት መላልሰው በዱላ ደብድበውታል። መላልሰው በድንጋይ ወግረውታል። ከወገሩትም በኋላ ትንፋሽ አጥቶ እንዲሞት ብለው ግዙፍ ደንጊያ ጭነውበታል። ቀኑ ገና ስለነበር አልሞተም እንጅ። ደግሞም የተጠራው ለአስቸኳይ ሞት ሳይሆን ለብዙ ጊዜ መከራ እንዲቀበል ነውና። ብዙ ጊዜ በተለያየ የመከራ አይነት የደከመ፣ ብዙ ጊዜ የተገረፈ፣ ብዙ ጊዜ የታሰረ፣ ብዙ ጊዜ ለሞት የሚያበቃ መከራ የተቀበለ፣ በባሕር ሲሄድ መርከቡ ሦስት ጊዜ የተሰበረበትና በዚህም ምክንያት ሦስት ቀንና ሌሊት በጥልቅ ባሕር ሲዋኝ ውሎ ሲዋኝ አድሯል። በመንገድም ሲሄድ ሁልጊዜ መከራ ይቀበል ነበር። ሽፍቶች በፈሳሽ ውኃ እየገረፉና እያፈኑ መከራ አጽንተውበታል። ዘመዶቹ እስራኤል መከራ አጽንተውበታል። አሕዛብ መከራ አጽንተውበታል። በከተማ መከራ ተቀብሏል። በበረሃ መከራ ተቀብሏል። በባሕር ላይ በመርከብ ሲሄድ የባሕር ወንበዴዎች በሚባሉት መከራ ተቀብሏል። ሐሳዊያን መከራ አጽንተውበታል። ብዙ ጊዜ በመጾም፣ ብዙ ጊዜ በብርድ፣ ብዙ ጊዜ በራቁትነት፣ ብዙ ጊዜ በሥራ፣ ብዙ ጊዜ በትጋት (በመንፈሳዊ ተግባር)፣ ብዙ ጊዜ በረሃብ፣ ብዙ ጊዜ በጽም፣ ብዙ ጊዜ በመቆም (በጸሎት፣ በማስተማር፣ በክስ ችሎት ላይ......) ማለት ነው። ብዙ ጊዜ በመስገድ፣ ብዙ ጊዜ በሌሊት ለጸሎት እንቅልፍ በማጣትና በመድከም እንዲሁም ጠላቶቹን በመፍራት። በከባድ የጎን ውጋትና በከባድ የራስ ፍልጠት (ምታት) ሕመም። ከዚህም ሌላ ያገኘው መከራ ቁጥር ስፍር የሌለው ብዙ ነው። ታዲያ ከስህተት ጥፋቱ ከተመለሰ በኋላ ስለ ሦስት ምስጢር ተብሎ ይህንና የቀረውን መከራ ሁሉ የተቀበለው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነው? ወይንስ ምንም ጥቅም የሌለው ድስት የሚያህል ቆብ ጭኖ በፎቅ ውስጥ በዙፋን ላይ ተቀምጦ ክትፎውን ሲበላና ውስኪውን ሲጨልጥ የነበረው ጎሰኛውና ሙሰኛው የሆነውና ከዚህም በላይ የደም ወንጀለኛው የሆነው፥ የአዞ እንባ አፍሳሹና አታላዩ እስስት የሆነው አባ ማትያስ ነው? የምናውቅ እናውቀዋለን። ወንድሜ ሀብታሙ! በል ደህና ሁንልን። ____ሁለተኛው አሳዛኝ ሰማዕት ወንድሜ ደግሞ ኤርምያስ ለገሰ ነው። እሱን እንኳ በሃይማኖት ጉዳይ የተነሣ ስለ አባ ማትያስ ጉዳይ ምንም ቢናገር ብዙ አልፈርድበትም። ከባዶ ተነሥቶ አውቃለሁ አውቃለሁ እወቁኝ እወቁኝ አይልምና። አለማወቁን አውቆ አውቃለሁ የማይል ነውና። ሆኖም ግን አንዲት ቃል ስለተናገረ ለዛች ቃሉ አጭር መልስ ሰጥቼ በዚኸው ልሰናበተው። ወንድሜ ኤርምያስ ለገሰ ሆይ፦ አንተ ደግሞ ስለ እነ አባ ማትያስ ውይይትህ ላይ ""ሃይማኖት በመንግሥት፣ መንግሥት በሃይማኖት ላይ ጣልቃ አይገባም። ነገ ከነገ ወዲያ ሕግ ቢኖረንም የምመኘው እሱን ነው።"" ስትል ሰማሁህ። ይህ ያንተ እውቀት፣ ሐሳብ፣ ፍላጎት፣ ምኞትና ሕልም ነው። የእኛ ትክክለኛው የትምህርት እውቀትና እውነታ ደግሞ ""መንግሥትም ክህነትም ሁለቱ ሥልጣን ባንድነት የእግዚአብሔር የባሕርዩ ናቸው።"" ስለዚህ መንግሥትና ክህነት ሰይፍና እጅ ማለት ናቸው። መንግሥትና ክህነት ሀገርና ሕዝብ ማለት ናቸው። መንግሥትና ክህነት ሥጋና ነፍስ ማለት ናቸው። የዘመኑ ፖለቲከኛ ተብየዎች ሁሉ ያለምንም ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ትምህርታቸው እየተነሱ ሃይማኖትና መንግሥት አንድ አይደሉም። አንዱ ባንዱ ጣልቃ አይገባም እያሉ እንደሚዘባርቁትና ተበላሽተው እንዳበላሹት አይደለም። ስለዚህ የመንግሥትና የሃይማኖት አንድ መሆን እንደማይቀርና እንደሚሆን እድለኛ ከሆንክ በቅርብ ጊዜ ታየዋለህና እንደ ክርስቲያንነትህ በእምነትና በተስፋ ጠብቅ እልሃለሁ። ከዚህ ውጭ ግን ስለ ሃይማኖት ቃልና ተግባር እናውቃለን እያሉ በባዶ እንደሚቀባጥሩት ዘመን አመጣሽ የወንጌል ደላላ ሰባኪዎች እንደሆኑት ብዙ ለመናገር እንዳትደፍር። በጥቅሉ ሰይፍ ያለ እጅ፤ እጅ ያለ ሰይፍ ሊያጠቃ እንደማይችል ሁሉ (መቸም ደደብ ምንጊዜም ደደብ ነውና አሁን ከዚህ ላይ ደደቡ አንባቢ ሁሉ ደንጊያስ? ዱላስ? ቦክስስ? ጥይትስ?.......) እንደሚል አትጠራጠሩ። መናገር እንጅ ማሰብ አያውቅምና። ቤተ- መንግሥትም ያለ ቤተ-ክህነት፤ ቤተ-ክህነትም ያለ ቤተ-መንግሥት ምንም ነገር ማድረግ ስለማይችሉ ሁለቱም እንደ እጅና ሰይፍ አንድ ሆነው የሀገርንና የሕዝብን ጠላት ሁሉ በትግልና በፍርድ እየቆራረጡ ያጠፋሉ ማለት ነው። ይህንን ስናገር ያ "አሮጌ ጅብ" (ብርሃኑ ነጋ) ስለ ሃይማኖትና ፖለቲካ የተናገረው የድንቁርና ቃል ትዝ አለኝ። ሌላ ጊዜ እመጣበታለሁ። ስለማታውቁ እንጅ ብታውቁማ ኖሮ መንግሥትና ክህነት (ሃይማኖት) ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሰይፍና እጅ ናቸው። እግዚአብሔር በጻድቁ በአባታችን በኖኅ እና በልጁ በካም አማካኝነት ከ ፭ ሺ ዓመታት በፊት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ጉንደ-ሀገር (ጎንደር) ዛሬ ትልቁ የፋሲል ግምብ ካለበት ቦታ ላይ ሀገርን፣ ሃይማኖትን፣ መንግሥትን፣ ክህነትን፣ የቃል ኪዳን ሰንደቅ-ዓላማን ሳይለያይ አንድ አድርጎ ነው የሰጠንና እኛም ተቀብለን ጠብቀንና አስጠብቀን እንድንኖር ነው ያዘዘን። ከዚህ ውጭ ፲፱፻፷፮ ዓ ም ያመጣቸዉ የደናቁርት ፖለቲከኞች ጥርቅም የሆኑት የአስኳላ ትምህርት ቤት መምህራንና ተማሪዎች እነዚህን የፈጣሪ ስጦታወቻችንን አንዱን ከአንዱ እንከፋፍላለን እንለያያለን ብለው በሰይጣናዊ የክህደት ዓመፅ ተነሡ። ሆኖም ግን በተቃራኒው እነሱ በሃሳብ ተከፋፍለውና ተለያይተው ብዙ አይነት የፖለቲካ ድርጅት ሲያቋቁሙ ከተቃራኒያቸው መንግሥት ጋር በፈጠሩት አለመግባባት በሞት መቅሰፍት ረግፈዉና በእግሬ አውጭኝ ስደት ይኸው እስከ ዛሬ ድረስ ሀገራቸዉንና ወገናቸዉን ትተዉ እንደተሰደዱና እንደ በጠበጡ በሥጋና በነፍስ ሳያምርባቸዉ እድሜአቸዉ አለቀ። መንጋ ከሐዲ!! (እነ ብርሃኑ ነጋና አንድ አርጋቸዉ ጽጌ..........) ያሳዝናል!!! እንዲያው ይህን ሁሉ መናገሬ ብትሰሙም ባትሰሙም ልንገራችሁ ብየ ነው እንጅ የደም ሰው ማትያስ ወያኔ ጠበቃ መሆናችሁን ከተረዳሁ ወዲህ ፈልጌ ልሰማችሁ ይቅርና ሰዎች እስቲ ዛሬ ስማቸው ብለው ቢጠቁሙኝም እንኳ አልሰማችሁም ትቻችኋለሁ። ምክንያቱም "በማያዉቁት ነገር ከመግባት፣ ከውሸትና ከማስመሰል በላይ የሆነ ጥላቻና ጠላት የለኝምና"። ስለዚህ እየሰማኋችሁ ከእናንተ ጋር ከምጣላ አለመስማቴ ሰላሜ ነው። እናማ በጣም የማከብርህ ወንድሜ ኤርምያስ ሆይ! አሁንም በድጋሚ ይህ ሲሆን ለማየት ያብቃህ እልሃለሁ። በተረፈ ግን አንተንም ሀብታሙንም፣ ሁላችሁንም ለሀገርና ለሕዝብ በከፈላችሁትና አሁንም እየከፈላችሁ ላላችሁበት ሰማዕትነታችሁ በጣም እንወዳችኋለን፣ እናከብራችኋለን። ሰማዕታትን ከኋለኛው ስሕተታቸዉ እንዲመለሱ እንመክራለን እንጅ መቸም ቢሆን ልንጠላቸዉ ቀርቶ አንረሳቸዉም። ብቻ ግን ከሀገርና ከሕዝብ ጠላት ጋር ሳታውቁ አትወግኑ ነው የምንላችሁ። በሉ ሁላችሁም ደህና ሁኑ። ___ ከዚህ በማስለጠቅ ደግሞ ወደ እናንተ ጥያቄና መልስ ነው የምመራችሁ። በውስጥ መስመሬ በጣም ብዙ ሰዎች ሃይማኖታዊ፣ ሀገራዊ፣ ሕዝባዊ፣ አማራዊ፣ ግላዊ የሆነ ጥያቄ ደጋግማችሁ ጠይቃችሁኛል። የሁላችሁንም በደንብ አይቸዋለሁ አየዋለሁም። አላየውም አያየውም ብላችሁ አትጠራጠሩ ብየ ባለፈው መልእክቴ ነገርኳችሁ እኮ። ቶሎ ብየ መልስ የማልሰጣችሁ ፌስቡኬን ቶሎ ቶሎ ስለማልከፍት ነው። በተጨማሪም ዋናው ነገር በእናንተ (በሕዝቡ) እና በሀገራችን ጉዳይ ከባድ የሆነ ሀሳብ፣ ኀዘን፣ ጭንቀት፣ ብስጭት፣ ንዴት፣ ቁጭት ስላለብኝ ለመጻፍ ስለማልፈልግ ነውና ይቅርታ። ደግሞም ከልባችሁ እዘኑልኝ። የኔ ኑሮ እኮ አሁን ኑሮ አይምሰላችሁ። በኢትዮጵያ ጉዳይ ጨርቄን ጥየ እንዳልሄድ እየፈራሁ ነው። ሁሌም ሁሉ የደስታ ነገር ቀርቶብኝ መኖር፤ መሞት፤ መቀበር የምመኘውና የምፈልገው የት እንደሆነ ታውቃላችሁ?? ድንግልን ነው የምላችሁ! ስለ እናት ኢትዮጵያ ማንነት ብሎ በሕልሙ ኖሮ በሕልሙ ከሞተው ከአባቴ ጎን ""መቅደላ""!!!! ____ለአሁኑ ግን በውስጥ መስመሬ ከተጠየቅኋቸውና ሁሉም ክርስቲያን የሆነ አንባቢ ሁሉ ያውቀው ዘንድ አስፈላጊ ከሆኑት ጥያቄዎች መካከል የአንዱንና አንዱን ብቻ መርጨ አቀረብኩላችሁ። የጠየቀኝ ሁለት ጥያቄ ነው። አንደኛው በአምስተኛው የጽሑፍ መልእክቴ ላይ Mesfin Birhanu (መስፍን ብርሃኑ) የተባልክ ክርስቲያን ወንድሜ ""በርስዎ የመጀመሪያዎቹ መልእክት መሠረት ሥጋ ወደሙ የተቀበልን አሁን ላይ ብንቀበል ችግር አለው ወይ?"" ብለህ ጠይቀኸኛል። ይሁንና ለአንዱ ሰው ጥያቄ መልስ ከሰጠሁትና ያ ጥያቄ ሌሎቻችሁ ከምትጠይቁኝ ጥያቄ ጋር አንድ አይነትና ተመሳሳይ ከሆነ የሰጠሁት መልስም ለእናንተ ጥያቄ መልስ እንደሚሆን ለምን አይገባችሁም? ተመልሳችሁ ለየግላችሁ የዛን አይነት ጥያቄ ለምን ትጠይቁኛላችሁ? ጊዜየንስ ለምን ትገሉብኛላችሁ? ጉልበቴንስ (ዓይኔን፣ ጣቶቼን፣ አዕምሮየን፣ መንፈሴን) ለምን ታደክሙኛላችሁ? እባካችሁን አስተዉሉ። መልእክቴን ከስር ከስሩ ብትከታተሉ ኖሮ አትጠይቁኝም ነበር። ችግራችሁ ስለማትከታተሉ ነው መልስ የሰጠሁበትን ጥያቄ እንደ አዲስ መልሳችሁ የምትጠይቁኝ። ስለዚህ የዚህን ጥያቄህን መልሱን ""ለሰባተኛ ጊዜ ትምህርታዊ የሆነ የጽሑፍ መልእክት ነው"" ከሚለው ላይ ታገኘዋለህና ያንን ተመልከት። ሁለተኛውና አሁን ለሁሉም ትምህርት የምሰጥበት ጥያቄህ ደግሞ እንዲህ ይላል። ___""በዓለ ሃምሳ ላይ የአምልኮት ስግደት እንሰግዳለን?"" የሚል ነው። ይህንን ጥያቄ በተለያዩ ድህረ-ገጾች ሌሎች ጠያቂዎች ለሁሉም ሰው ሲጠይቁ አይቸዋለሁ። መልስ ያግኙ አያግኙ ባላውቅም። አሁን ደግሞ ተመልሶ ወደኔ መጣ። አጠያየቅህ ግልጽ ያልሆነና የማይገባ ቢሆንም ቅሉ እኔ ግን ጥያቄህን አስተካክየ ጠቅለል አድርጌ ባጭሩ ነው የምመልስልህ። የአምልኮት ስግደትማ በታቦታት ላይ አድሮ ለሚመለከው ለፈጣሪ ምንጊዜም ቢሆን ይሰገዳል። ጥያቄህ መሆን የነበረበት እንዲህ አልነበረም። መሆን የነበረበት በበዓለ ሃምሳ የንስሐ ስግደት፣ የፈቃድ ስግደት፣ የትሩፋት ስግደት ይሰገዳል ወይስ አይሰገድም? ነበር። ለነገሩ አጠያየቅህ ያላዋቂ ስለሆነ አልፈረድኩብህም አልፈርድብህም። እንዲያው ለወደፊቱ ሁላችሁም ብትሆኑ ስትጠይቁ ጥያቄአችሁ ለተጠያቂዎቹ ግልጽ ሆኖ እንዲገባቸውና መልስ እንዲሰጧችሁ እንድትማሩና እንድታውቁ ብየ ነው። ካለዚያ ግን ሊቃውንት ጥያቄአችሁን ወልጋዳ ወልገድጋዳ ብለው ነው ዝም የሚሏችሁ። ስለዚህ ከአዋቂዎች ፊት ""ስታስቡ፣ ስትናገሩ፣ ስትጠይቁ፣ ማስተዋልና ረጋ ረጋ ማለት ያስፈልጋል""። ይህ ካልሆነ ግን ሊቃውንቶች በመንፈስ ብስጩና ቁጡ ስለሆኑ ተጠንቀቁ። መቸም አዕምሮአችሁ ጠባብ፣ አፋችሁ ሰፊ ስለሆነ ""ሊቃውንት ሊበሳጩና ሊቆጡ ተገቢ ነውን? ትዕግስተኞች አይደሉምን? እነሱ ከተበሳጩና ከተቆጡማ ምኑን አዋቂ ሆኑ? በእነሱ አይነት ከሆነማ እኛስ ብንቆጣና ብንበሳጭ ይፈረድብናልን? እኛ ከእነሱ ትዕግስትን እንጅ የምንጠብቀው ብስጭትንና ቁጡነትን ነው እንዴ?......."" እንደምትሉኝ አውቃለሁ። መልሱን ባጭሩ፦ እናንተም አዋቂ ሊቃውንት ሁኑና ያኔ አግኙት"" ሌላ ማውራት አልፈልግም። ጥያቄው ግን ለሁላችሁም የሚጠቅም ስለሆነ መልሱም ለሁላችሁ ነውና በሉ በደንብ እያስተዋላችሁ ስሙ። ___መልስ፦ በመሠረቱ ስግደት በሦስት ይከፈላል። እነዚህም፦ የአምልኮት፣ የጸጋ፣ የአክብሮት ተብለው ነው። ትርጉማቸውም፦ የአምልኮት ስግደት ለሥላሴ (ለእግዚአብሔር) ለፈጣሪነቱ፣ ለአምላክነቱ፣ ለንጉሥነቱ፣ ለጌትነቱ፣ ለመምህርነቱ፣ ለመድኃኒትነቱ፣ ለአባትነቱ፣ ለቀዳማዊነቱ፣ ለዘላለማዊነቱ፣ የባሕርዩ ነው ብለን በማመን የምንሰግድለት ስግደት ነው። ___የጸጋ ስግደት ደግሞ፦ የመዳን ምልክታችን፣ ነጻነታችን፣ ምስክራችን፣ መድኃኒታችን፣ እናታችን፣ እመቤታችን፣ ንግሥታችን፣ ቃል-ኪዳናችን፣ አማላጃችን፣ ተማላጃችን፣ ተስፋችን፣ ብርሃናችን........ከሆነችው ከቅድስት ድንግል ማርያም ጀምሮ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ለሆኑት የጸጋ አማልክት ተብለው ከፈጣሪ በተሰጣቸዉ ቃል-ኪዳን መሠረት የጸጋ ክብራቸውንና አማላጅነታቸዉን አውቀን፣ አምነንና ተቀብለን የጸጋ ስግደት የምንሰግድላቸዉ ሰማያዊያን ቅዱሳን መላእክትና ቅዱሳን ነብያት፣ ሐዋርያት፣ ሰማዕታት፣ ጻድቃን ናቸዉ። ___የአክብሮት ስግደት ደግሞ፦ ለምድራዊያን ነገሥታትና ጳጳሳት የሚቀርብላቸዉ ነው። ይኸውም ፈጣሪ በቅብዐ-መንግሥትና በቅብዐ-ክህነት ቀብቶ በሀገርና በሕዝብ ላይ ስለሾማቸው ያንን ተንተርሰን የምናቀርብላቸዉ አክብሮታዊ ስግደት ነው። ከዚህ ላይ ግን ልብ የምትሉልኝ ምስጢር፦ የጸጋ ስግደቱን ለነገሥታትና ለጳጳሳትም ጭምር እንደሆነ አድርገው የሚናገሩ መምህራንና ሊቃውንት ቢያጋጥሟችሁና ብትሰሙ በእኔና በእነሱ ትምህርት ላይ ምንም አይነት የተቃርኖ ልዩነት እንደሌለው አውቃችሁ መቀበል ነው። ምክንያቱም ትክክል ናቸውና ነኝና። የአክብሮቱን ስግደት ደግሞ በእድሜ፣ በእውቀት፣ በታላላቅ የታሪክ ሥራ፣ በመልካም ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ሥራ ላይ ታዋቂ ለሆኑት ታላላቅ ሰዎች የሚቀርብ እንደሆነ አድርገዉ ያስተምራሉ ይናገራሉ። ልክ ናቸዉ። ስህተት የለውም። እኔም እንደነሱ ነኝ። እነሱም እንደኔ ናቸዉ። በመንፈስ ቅዱስ መልእክተኞችና በአዋቂ ሊቃውንቶች መካከል ቅንጣት ልዩነት የለም። የሚበጠብጠን ማንም የወንጌል ደላላ የሆነው ደንቆሮ ነው እንጅ። አልተማረማ! የጸጋ ስጦታ የለውማ!! እናም እኔ የአክብሮት ስግደቱን ለነገሥታትና ለጳጳሳት የሰጠሁበት እውነታ እንዳለ ሆኖ ምክንያቱንም ከታች ታገኙታላችሁ። ___የስግደቱ የአሰጋገድ አይነት፦ ለአምላክና ለቅዱሳን አማልክት የምንሰግደው ስግደት አንድ አይነት ሥርዓት ያለው ነው። ይኸውም፦ ከአካላችን ሦስት ጊዜ እየተጎነበስንና እየተመለስን ጉለበታችን መሬት ነክቶ፣ እጆቻችን መሬት ነክተው፣ ግምባራችን መሬት ነክቶ የምንሰግደው ነው። ከዚህ ላይ ግን ልብ በሉና አስተውሉኝ። ይኸውም፦ የደናቁርት ጥርቅም የሆኑት ዘመን አመጣሽ የወንጌል ደላላ ሰባኪ ተብየዎች ሁሉ የአምላክንና የአማልክትን የአሰጋገድ አይነት ልዩነት እንዳለው አድርገዉ ነው የሚለፈልፉትና ስተው የሚያስቱበትና ተጠንቀቁ። ይኸውም፦ ለአምላክ እና ለቅዱሳን አማልክት ስንሰግድ እኔ አሁን ከላይ እንደነገርኳችሁ በግምባራችንና በአፋችን መሬት ስመን መመለስ ሲሆን ደናቁርት ደላሎች ግን የብልግና ድፍረታቸዉ ድፍረት ከእመቤታችን ጀምሮ ላሉት ለቅዱሳን አማልክት የሚሰገደው የስግደት አይነት ግን የአምልኮት ሳይሆን የጸጋ ስለሆነ ልክ እንደ ነገሥታት የአክብሮት የሰላምታ አሰጋገድ አይነት ከትክሻችንና ከወገባችን ጎንበስ እያልን ቀና በማለት ነው ሰላም ለኪ ሰላም ለከ የምንል እንጅ በግምባራችን፣ በእጆቻችን፣ በጉልበታችን፣ በከንፈራችን መሬትን መንካት የለብንም ክልክል ነው ይላሉ። አዎ! እነሱ በድንቁርናቸዉ የከለከሉት ነው። በጥቅሉ ይህ ስብከታቸዉ ግን ከድንቁርናቸውም በላይ ሰይጣናዊና ኑፋቂያዊ መሆኑን አውቃችሁ አትቀበሏቸዉ። ወደዛ በሏቸዉ። እንዲያውም ይህንን አይነት ቃል በመድረክ ላይ ቆመዉ ለሕዝቡ ሲናገሩ ከሰማችኋቸዉ ሳትፈሩና ሳታፍሩ በጩኸት ማስቆምና ከዚህም በላይ ጎትታችሁ በማውረድ ከቅጽረ ቤተስኪያን አስወጥታችሁ ማባረር ነው። ልዩነቱ ለፈጣሪ የምንሰግደው ስግደት ለባሕርዩ የሚገባው መሆኑን አውቀንና አምነን መስገድ ሲሆን ከእመቤታችን ጀምሮ ላሉት ለሁሉም ቅዱሳን አማልክት የምንሰግደው የጸጋ ስግደት ደግሞ ከፈጣሪ የተሰጣቸዉን የጸጋ አማልክትነታቸውን አውቀንና አምነን ለጸጋቸው የምንሰግደው ስግደት ነው እንጅ የአሰጋገዱ ሥርዓት ልዩነት የለውም አንድ ነው። እንዲያው እናንተ እንደምትሉት አይደለም እንጅ ቢሆንም እንኳ ክርስቲያኖች ሙሉ አካላቸውን መሬት አድርሰው ለጸጋቸው ክብር ቢሰግዱ ይጠቀማሉ እንጅ ምን ይጎዳቸዋል? ወይንስ ለቅዱሳን አማልክት ወድቀው በመስገዳቸዉ ፈጣሪ ለሱ የሚገባውን የስግደት አይነት ለበታቾቹ ለቅዱሳን በመስገዳቸው ይቀናል ይቆጣል ልትላቸው ነውን? ለታቦት ሰገዱ እንጅ ለጣዖት የሚሰግዱ መሰለህ እንዴ? ታቦቱስ (ጽላቱ) የማን ማደሪያና መመለኪያ ሆነና? ምናምንቴ ደንቆሮ ደላላ!!!! ____የአክብሮት ስግደት ደግሞ፦ ለነገሥታትና ለጳጳሳት ሆኖ ፈጣሪ ለአስተዳደርና ለቡራኬ ከሕዝብ መርጦ፣ አክብሮና ለይቶ ስለሾማቸው እኛም ይህንን የፈጣሪ ምርጫና አክብሮት አውቀንና አምነን በመቀበል እነሱን በማክበር የክብራቸዉ መገለጫና መታወቂያ የሚሆናቸውን እንደ ቅዱሳን የአማልክትነት ሳይሆን የአክብሮት ስግደት ከትክሻችንና ከወገባችን ጎንበስ ዝቅ በማለት መስገድ ይኖርብናል ማለት ነው። ከዚህ ላይ ግን አስተዉሉኝ ልብ በሉኝ። ይኸውም፦ ለንጉሡና ለጳጳሱ ከፈለጋችሁና ከወደዳችሁ እንደ ቅዱሳን አማልክት ስግደት መሬት ድረስ መጎንበስና መንካት፣ እግራቸዉን መሳም መብታችሁ ነው። ምንም አይነት ስሕተት፣ ጥፋትና ኃጢአት የለበትም። እንዲያውም በረከት ታገኙበታላችሁ። ከላይ ሊቃውንት ለንጉሡና ለጳጳሱ የጸጋ ስግደት ይሰገድላቸዋል ይላሉ። ይህም ቃላቸዉ ምንም ችግር የለበትም ያልኳችሁን አስታውሱ። በእርግጥም ለንጉሥና ለጳጳስ ይቅርና ለአንድ የሥጋ ወላጅ አባትስ ቢሆን እንደ ወላጅ አባትነቱ፣ እንደ አሳዳጊነቱ ልጆቹ ዝቅ ብለው ጉልበቱን ይስሙት የል? በተለይ በተለይ ደግሞ ይህ አይነት ጥሩ ልማድ ያለው በበጌምድር ክፍለ-ሀገር ትውልዶች የተለመደ ነው። እናም ለታላላቆች ነገሥታትና ጳጳሳት ይቅርና ማለቴ ነው። ችግሩ ግን የዛሬ ዘመን ንጉሥም ጳጳስም ዓለማዊ ወንበዴዎች እየሆኑ ክብራቸዉን በመጣል አስቸገሩን እንጅ ክብራቸዉማ በፈጣሪ ዘንድ ትልቅ ነበር። በንጉሥነታቸዉና በጳጳስነታቸዉ ዘመን ለሀገርና ለሕዝብ ሃይማኖታዊ መልካም ሥራ ቢሠሩ ደግሞ እግዚአብሔር ከሥጋ ሞታቸዉ በኋላ የጸጋ አማልክትነትን ሊያጎናጽፋቸውና ጽላትም እንዲቀረጽላቸዉ፣ የፍጹም አማልክትነት አምልኮትና ስግደት እንዲቀርብላቸዉም ያደርጋል። ለምሳሌም:- እንደነ አብርሐ ወአጽብሐ፣ ንጉሥ ይምርሐነ ክርስቶስ፣ ላል ይበላ፣ ነአኩቶ ለአብ እንዲሁም በፋሽሽት ጣሊያን ለሀገራቸው፣ ለሕዝባቸው፣ ለሃይማኖታቸው፣ ለሰንደቅ ዓላማቸው፣ ለማንነታቸው፣ ለነጻነታቸው ወዘተ ወዘተ ብለው ለተሰየፉት ለአቡነ ሚካኤልና ለአቡነ ጴጥሮስ የጸጋና የአክብሮት ስግደት እንዲቀርብላቸው ብቻ ሳይሆን ጽላትም እንዲቀረጽላቸው እንደታዘዘውና እንደሚታዘዘው ማለት ነው። ___የስግደቱ ትርጉምና መሬት ነክቶ መመለሱ፦ ሀ/ ከመሬት ፈጠርከኝ ከመሬት አነሣሃኝ። ለ/ ከመሬት እንደ ፈጠርከኝና እንደ አነሣሃኝ ሁሉ መልሰህ ወደ መሬት ታስገባኛለህ። ሐ/ በኃጢአት ብወድቅ በንስሐ ታነሳኛለህ። መ/ መሬታዊም ሰማያዊም ነኝ (መሬታዊ በአሁኑ፣ ሰማያዊ በኋላኛው) የሚሆነውን መናገሬ ነው። ሠ/ በሥጋ ወደ መሬት (መቃብር) ብገባም ኋላ ደግሞ እንደገና በትንሣኤ ጊዜ መልሰህ ሥጋየንና ነፍሴን አንድ አድርገህ አዋህደህ በክብር ለክብር ታነሣኛለህ ማለት ነው ባጭሩ። ጻድቃንን ማለቴ ነው። ኃጥአን ደግሞ ያው ከጭራ ቀጥነዉ፣ ከቁራ ጠቁረዉ፣ ከሽንት ቤት ኩስ ሸተዉና ከርፍተዉ፣ ፍጹም የግብር አባታቸውንና ጌታቸውን ዲያብሎስን መስለዉ በመከራ ለመከራ በከባድ የለቅሶ ዋይታና ጩኸት ርስታቸውን ገሃነም እሳትን ለዘላለም ለመውረስ ይነሳሉ ማለት ነው። አደራህን ሰውረኝ። ___ወደ በዓለ ሃምሳው የአምልኮት ስግደት ጥያቄ ስመጣ፦ ባጭሩና በጥቅሉ የምነግራችሁ በበዓለ ሃምሳ ሰሞን የአምልኮት ስግደት ከሰኞ እስከ ዕሁድ ድረስ ለታቦታት በቁጥር እንደተለመደው ከሦስት ጊዜ በላይ ስግደት በፍጹም አይፈቀድም ክልክል ነው። እንደ ሰንበት ሦስት ጊዜ ጎንበስ ቀና በማለት መሬትን እየሳሙ በመስገድ ከመነሳት ውጭ ሌላ ትርፍ ስግደት አይቻልም ማለት ነው። ___የሰአት ቆይታም ሆነ የቅባት ምግብ መጾም ፈጽሞ የተከለከለና የማይፈቀድ ነው። እኛስ ይህን ይህን አይደል ከዓመት እስከ ዓመት የምንፈልገው!! ሕግ አገደን እንጅ። ከንቱዎች ነን። ___ንስሐ በራሱ በገቢው የቃል ተናዛዥነትና በካህኑ ቃል የኃጢአት ስርየት ከመቀበልና ከመስጠት ውጭ የስግደትና የጾም ቅጣት መስጠት ፈጽሞ ክልክልና የማይፈቀድ ነው። ሆኖም ግን ኃጢአትን ለካህን መናዘዝና በካህኑ ቃል ስርየት ማግኘትና ምጽዋት ለነዳያን መስጠት ግን የግድ ግድ ነው። የሚሰጠው ከሌለውና ካላጣ በቀር። ""ሕይወቱ ለነዳይ ስኢለ ምጽዋት"" እንዳሉ ነብያትና ሐዋርያት። ቀጥተኛና ነጠላ ትርጉሙ ""የነዳይ ሕይወት (ኑሮው) ዘመኑን ሁሉ ምጽዋትን መለመን ነው ማለት ነው። ስለዚህ ካላችሁ ስጡ አትሳሱ አትንፈጉ። ከሌላችሁ ደግሞ ካለበት ያድርስህ በሉት። ሌላ ትርፍ ቃል አያስፈልግም። ___በበዓለ ሃምሳ ጾምና ስግደት የማይፈቀድበት ምክንያት ምስጢሩ ግሩም ነው። ይኸውም፦ የበዓለ ሃምሳ ቀኖች የገነትና የመንግሥተ-ሰማያት ምሳሌ ነው። ኃጥአንን ወደዛ ልተዋቸውና ጻድቃን በሥጋ ከሞቱ በኋላ በነፍሳቸው በገነት ውስጥ ሲኖሩ አሁን ጥጋብ እንጅ ጾም (ረሃብ) የለባቸውምና። እረፍት እንጅ (ስግደት) ድካም የለባቸውምና። እርካታ እንጅ ጥማት የለባቸውምና። ተድላ ደስታ እንጅ ኀዘን፣ ትካዜና ለቅሶ የለባቸውምና። ኋላ በትንሣኤ ጊዜ ደግሞ ለጻድቃን ከፊተኛው የገነት ኑሮ ይልቅ የበለጠ ስለሆነ በዓለ ሃምሳ የአሁኗ ገነት የኋላዋ መንግሥተ-ሰማያት ምሳሌ ስለሆነች በበዓለ ሃምሳ በንስሐ ቅጣት መጾም፣ መራብና መጠማት፤ መስገድና መድከም፣ ማዘንና ማልቀስ የለም። ይህን ስላችሁ ደግሞ እንደነ ሆድ አምላኩ በበዓልና በተለያየ የዝክር አይነት እያመካኛችሁ፣ በምግብና በመጠጥ እየጠገባችሁና እየሰከራችሁ በሥጋ ደስታ ደንሱ፣ ዘሙቱ፣ ያለ ሥርዓት ቆዩ ኑሩ ማለት አይደለም። መቸም ጤና የላችሁምና እናንተን ከመጠበቅ ይልቅ የእረኝነት በጎቼንና ፍየሎቼን በሰላምና በጤና መጠበቅ ይሻለኝ ነበር። በድምፅ ብቻ ተመለሱ ሲሏቸው ይመለሳሉና። እናም በገነትና በመንግሥተ-ሰማያት ኃጢአት የሚባል ነገር እንደሌለና እንደማይኖር ሁሉ በበዓለ ሃምሳም ኃጢአት ሠሪና ኃጢአት መኖር የለበትም ብላችሁ ራሳችሁን አሳምናችሁና ገዝታችሁ ለመኖር ሞክሩ እላችኋለሁ። በጥቅሉ በበዓለ ሃምሳ ቀናት ከስግደትና ከጾም ድካም ማረፋችን ምሳሌውና ትርጉሙ ከበዓለ ሃምሳ ቀናት እረፍተ ሥጋ በፊት በጾመ አርባ ሁዳዴ ቀናት በጾምና በስግደት ስንደክም እንደቆየን ሁሉ ከትንሣኤ በኋላ በበዓለ ሃምሳ ማረፋችን ""ጻድቃን በሕይወተ ሥጋ በምድር ላይ ሳሉ በጾምና በስግደት ሲራቡና ሲደክሙ ከኖሩ በኋላ በሥጋ ሞት ከምድር ዓለም ካለፉ በኋላ በነፍሳቸው አሁን በገነት፤ ኋላ ደግሞ በዳግም ትንሣኤ ጊዜ በሥጋ በነፍስ ተዋህዶ በመንግሥተ ሰማያት ከድካመ ሥጋ የማረፋቸው ምሳሌ ነው""። በተረፈ ግን ከእኔ መልስ በተጨማሪና የበለጠ ለማወቅና ለማግኘት ደግሞ ወደ ምናምንቴዎች የስም መምህራንና አዋቂዎች ናቸው ወደሚባሉት የወንጌል ደላላዎች ሳይሆን ነብዩ ሲራክ ""ልጄ ሆይ ልትማርና ብልህ አዋቂ ልትሆን ብትወድ ወደ ብዙ መምህራን ሂድ። ነገር ግን ሁሉም አዋቂዎች አይደሉምና ከእነርሱም ይበልጥ የተማረውንና ሊቅ አዋቂ የሆነውን መምህር ብታይና ብታውቅ ወደ እርሱ ሂድ፣ ተከተለውም። እግሮችህም በደጃፉ ይመላለሱ"" ባለው መሠረት መጠቀም ይኖርባችኋል። አንባብያን ሆይ፦ እስካሁን ያልነገርኳችሁና አሁን የምነግራችሁ ነገር የመጽሐፎቹን ምዕራፍና ቁጥር የማልጽፍላችሁ የኔ መጻፊያ ከአሥር (፲) ቁጥር በላይ ስለሌለውና ስለማይጽፍልኝ ነውና ይቅርታ አድርጉልኝ። ዓመተ ምህረቶችንም ቢሆን የማጽፍላችሁ ወደ ሌላ ሰው የጽሕፈት መሣሪያ በመላክና ትብብር በመጠየቅ ነው። ይህም ቢሆን ደግሞ ይሰለቸኛል። የሰው ነገር አያኮራምና። በተለመደው በባዕዳ ቁጥር እንዳልጽፍላችሁ ደግሞ ክልክል ነው አይቻልም። እኔም አላደርገውም። ለአሁኑ አበቃሁ። የሌሎቻችሁ የግል ጥያቄና መልስ ግን በውስጥ መስመሬ የሚመለስ ስለሆነ በዛው መስመሬ በትዕግስት ጠብቁኝ አታስቸኩሉኝ። ባታውቁኝ ነው እንጅ ብታውቁኝማ ኖሮ ስለ እናንተ ከእናንተ በላይ እኔ አስባለሁ ብል እውነታውን የሚያውቁት መድኃኒዓለምና ድንግል ማርያም፣ ቅዱሳን ብቻ ናቸው። አጼ ቴዎድሮስ ምን ነበር ያሉ? ""የልቤን ውስጥ እሳት ብታዩልኝና ብታውቁልኝ ኖሮ ለሀገሬና ለሕዝቤ ጥሩ ዓላማና ፍቅር ነበር ያለኝ"" አሉ። እውነታቸውን ነው። ለእሳቸው እኔ ራሴ በራሴ ዋና ምስክር ነኝ። እሳቸውንም በመንፈስ አሳምሬ አውቃቸዋለሁ። ሞት ቀደመብኝ እንጅ። በሉ ደህና ሁኑልኝ። ወደ እናንተ ስመለስ፦ እኔ መልስ የምሰጣችሁም መልስ ያስፈልገዋል ብየ ለአመንኩበት ጥያቄ ብቻ ነው እንጅ እንዲያው እናንተን ለማስደሰት ብየ ለመጣው ጥያቄ ሁሉ መልስ አልሰጣችሁም። የብዙዎቻችሁ ጥያቄም መልስ የማያስፈልገው ትርኪ-ምርኪ ነው። በተረፈ ግን በአማራ ክልል የምትማሩ የአማራ ተዎላጆች የሆናችሁ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርቱን ትተን ወደየ ትውልድ ሀገራችንና ቤተ-ሰቦቻችን እንሂድን ወይስ እንማር ላላችሁኝ ጥያቄ፦ ለምንድን ነው የምትሄዱ? ቀይ-ባሕር ለመግባት ነው? አርፋችሁ ተማሩ ተቀመጡ አይዟችሁ። አታቋርጡ አትሂዱ። የመጣው ነገር ለሁሉም በሁሉም የማይቀር ነውና ብዙ አትሰቡ አትጨነቁ። በኦሮሚያና በትግሬ ክልል ለተመደባችሁትና ለምትመደቡት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግን መልእክቴን ሁሉ በ ፪ሺ ፲፩ ዓ ም በግንቦት ወር አንዴ አስረግጨ ተናግሬ ዘግቻለሁ። ዳግም ሌላ የምነግራችሁ ነገር የለኝም። ለራሳችሁ ራሳችሁ ታውቁ። አንድና ሁለት ዓመት አቋርጠህ በጤና፣ በሰላም፣ በእድሜ ለመቀመጥ ጠልተህ ሞትን መርጠህ ስትሄድና ስትገባ እኔ መጥቼ እጅህን እየያዝኩና እየጎተትኩ እንዳወጣህና እንድመልስህ ነው የምትፈልገው??? ____ሌላው ጥያቄ ደግሞ፦ አዲስ አበባን ለቀን እንውጣ ወይ? ያላችሁኝ ግን በጣም ታበሽቃላችሁ። ለማንና ለምን ብላችሁ ነው የምትለቁ? ለኦሮሞ ወረራ? ለዐረብ ወረራ? የትም ለማይቀረው የጠረጋ ሞት? ኦሮሞም ሆነ ዐረብም እኮ ለወረራ ቢመጣና ቢገባም ራሱ መውጣትና ማምለጥ እንደማይችል ምን ብየ ልንገራችሁ? አዲስ አበባ እኮ መሠረቷም መጨረሻዋም የአማራ ናት። የርስት አገራችሁን ለማን ጥላችሁ ነው የምትወጡ? የሀገሬ የበጌ ምድር ጀግና ገበሬ ብሶቱንና የወንድነት አልጠቃም ባይነቱን በቀረርቶ ሲገልጽ የሚያሰማውን ስነ-ቃል በልጅነቴ እረኛ ሳለሁ የምሰማውንና ዛሬም ድረስ በልቤ ያለውን እስቲ ልንገራችሁ!! ___አባቴ አባቱን ልጁን እኔ ሳውቀው፣ ___እንዲያው ባረባ ሰው ሀገሩን ለቀቀው። ወይኔ አምኃ ኢየሱስ!! ስለዚህ ይህ ምስጢራዊ የጀግንነት መታወቂያ የሆነው ስነ-ቃል ከገባችሁ ሀገራችሁን፣ ርስታችሁን፣ ባድማችሁን ለማንና ለምን ብላችሁ ነው ለቃችሁ የምትሄዱ? የእነሱ እጅ ጠብ-መንጃ ሲይዝ የእናንተስ እጅ በሶ ነው እንዴ የሚጨብጠው? አዲስ አበባም ሆነች ኢትዮጵያ ዛሬ ለጊዜው በኦሮሞና በትግሬ ትውልዶች እየታመሱ ቢሆንም ነገ ግን በአማራ መንግሥትና በአማራ ጦር ሠራዊት እጅ እንደሚገቡ ምንም አትጠራጠሩ፣ አይዟችሁ፣ ተረጋጉና ከንስሐ ኑዛዜ ጋር ተቆራኝታችሁ በያላችሁበት ሥራችሁን ሥሩ። ኦሮሞና ትግሬ መጨረሻቸዉ ሰዶም ገሞራ ነው አልኳችሁ እኮ። ዛሬ እንዲህ እንደ ቁንጫ የሚያዘልላቸዉና እንደ ቆርቆሮ የሚያስጮሃቸው ለመጥፋት ነውና አይዟችሁ። እኛም የኢትዮጵያ ጦር፣ የአማራ ጦር፣ የክርስቲያን ጦር የሆንነው ኢትዮጵያንና አዲስ አበባን ለመረከብ በእግዚአብሔር ፈቃድ እየመጣን ስለሆን ተረጋጉ አትጨነቁ። ከዐረብ ወረራ በኋላ ሁሉም ነገር የኛ ነውና ደስ ይበላችሁ። የኔን ዘመን ትውልዶች ማን እንደረገመን ባላውቅና ባያድለን ነው እንጅ አዲስ አበባን ለቀን መውጣት፣ መሄድና መተው ይቅርና የኢትዮጵያ ሀገራችን ግዛት እስከ የት እንደነበርና ኢትዮጵያ ማለትስ ምን ማለት እንደነበር አልተማራችሁምን? አላነበባችሁምን? እኔ ማይሙ ምናምንቴ የሆንኩት ላስተምራችሁን? ልንገራችሁን? እሺ ምን ቸገረኝ!! እስቲ እንዲያው አጋጣሚውንም ተጠቅመው እንደኔ የትምህርትና የእውቀት ደደቦች ሆነው የሚሰድቡኝም ትንሽ ታሪክ ይማሩና ለማወቅ ይሞክሩ። ""Land of the Blacks"" meant all Ethiopia, all Ethiopia meant all Africa, and all Blacks were Africans or Ethiopians, etc. Translation (ትርጉም) ""የጥቁሮች ሀገር መላው ኢትዮጵያ ማለት ነበር፤ መላው ኢትዮጵያ ማለት መላው አፍሪካ ማለት ነበር፤ እና መላው ጥቁሮች ሁሉ አፍሪካዊያኖች ወይም ኢትዮጵያዊያኖች ነዋሪዎች ነበሩ"" ወዘተ ይል ነበር። በተረፈ ለታሪኩ ትምህርት ሳይሆን ለእንግሊዝኛው ቋንቋና ትርጉም ብቻ ስህተት ካለብኝ የቋንቋውና የትርጉሙ ባለቤት የሆናችሁ ምሁራን አስተካክሉልኝ፣ አስተካክሉኝ እታረማለሁ። ስህተት ያለብኝ ግን አይመስለኝም። እናም ገና ድሮ ድሮ በሕጻንነቴ ነውና 3ኛ ክፍል ሳለሁ ከቋንቋ ጋር የተማርኳትና የያዝኳት። መቸም እንዲህ አይነት ልጅ እንዲህ ሆኖ ቀረ በማለት በጣም እንደምታዝኑና በአንጻሩ ደግሞ በ3ኛ ክፍሏ በሳቅ ስትፈርሱ ይታየኛል። በዚኸው አጋጣሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ነጠላ ቃልና ጥሬ ቃል አንባቢዎችና ተናጋሪዎች የሆናችሁ ዘመን አመጣሽ ደናቁርት ደላላ ሰባኪዎችም ሆናችሁ ምእመናን ሁሉ በማንበብ፥ በመጻፍና በመናገር ብቻ ስሜታዊ በሆነ በድንቁርና ድፍረት እየተነሳችሁ እንተረጉማለን፣ እናስተምራለን ከማለታችሁ በፊት እግረ- መንገዳችሁን ከዚህ ከእኔ የንባብና የጽሑፍ፣ የንግግርና የትርጉም መልእክት ብትማሩ ይበጃችኋል። ምክንያቱም በጥልቅ ትምህርትና በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተሞልተውና ተመርተው ነብያት፣ ሐዋርያትና ሊቃውንት የተረጎሙትንና የሚተረጉሙትን የመጽሐፍ ቅዱስን የንባብ ምስጢር ለመተርጎም ይቅርና ማንኛውንም ቋንቋ ማንበብና መናገር ከመተርጎም ጋር አይገናኝምና። የቃላትን ንባብና ንግግር ከኔ ጀምሮ ማንም ማይም ሊያነበውና ሊናገረው ይችላል። ትክክለኛ ምስጢሩን ለመተርጎም ግን አይችልም። ትርጉም በመንፈሳዊውም ሆነ በዓለማዊው ትምህርት ራሱን የቻለ የመተርጉማን ምሁራን እውቀት ነውና እላችኋለሁ። ከዚህ ውጭ እንደ ፕሮቴስታንት አንባቢና እንደ ዲያስፖራ ተናጋሪ በአምኃ ኢየሱስ ጀሮ ላይ እንድትለፈልፍ አልፈቅድልህም። ከዛው እርስ በርስህ ተለፋለፍ እንጅ ወደኔ አትምጣብኝ። ሌላው ተጨማሪ መልእክቴ ከዚህ በፊት በአራተኛው የመደበኛ ጽሑፍ መልእክቴ ላይ ተናግሬዋለሁ። አሁንም ለመጨረሻ ጊዜ ልድገመው። ይኸውም አማርኛ ቋንቋ መጻፍና መናገር የማትችሉ ካልሆናችሁ በቀር መጻፍና መናገር የምትችሉ ግን ማንኛውንም ኮሜንታዊ መልእክታችሁን ሁሉ በአማርኛ ቋንቋ ጻፉ፣ ተናገሩ። ምክንያቱም እኔ አማርኛ ቋንቋ መጻፍ፣ መስማት፣ መናገር የምችል የቋንቋው ባለቤት የሆንኩና ከዚህ በፊት ክብርና ምስጋና ለአርበኞች አባቶቻችን ይሁንና በማንም በማን የባዕዳን ወራሪ ኃይል ቅኝ ያልተገዛሁና አሁንም ወደፊትም የማልገዛ፣ የአማርኛ ቋንቋየ በባዕዳን ወራሪ ኃይል ያልተበረዘብኝና ያልጠፋብኝ፣ በሙሉ ማንነቴ ኩሩ ኢትዮጵያዊ፣ ኩሩ በጌምድሬ፣ ኩሩ አማራ፣ ኩሩ ክርስቲያን ነኝ። ስለዚህ በባዕዳን ወራሪ ቋንቋ በእንግሊዝኛ አትጻፉልኝ አታናግሩኝ ነው የምላችሁ። በሱ የምትጽፉልኝ ምስጢራዊ ቋንቋ መሆኑ ነው? ወይስ የእውቀታችሁ ጣራ መሆኑ ነው? የባንዳ ጥርቅም የሆነው ከሐዲው ትግሬና ኦሮሞ የሚረብሸኝ ይበቃኛል። ወይንም ደግሞ የጽሕፈት መሣሪያችሁ ከእንግሊዝኛ ውጭ አማርኛ የማይጽፍና የማያነብ ከሆነ አስቀድማችሁ መጠቆም ነው። ስለጻፋችሁልኝ መልካም ኮሜንታችሁ ግን በጣም በጣም አመስግኛለሁ። እስቲ ምሳሌ የምትሆናችሁን ዕንቁ ስለሆነች ልጅ ልንገራችሁና በማንነታችሁ ተገኙ። አሜሪካ አትላንታ ከተማ ነዋሪ የሆነች Azeb Begosew እሷ በዚህ ስለጻፈችው ነው (አዜብ በጎ-ሰው) ዘስመ ጥምቀቷ ዕሴተ-ጻድቅ። ትርጉም፦ ""የጻድቃን ደስታ"" ማለት ነውና ያዥው አትርሽው። እናም ይች ሕጻን ልጅ በውስጥ መስመሬ በድምፅ ተቀርጻ በአማርኛ ቋንቋ ያስተላለፈችልኝን መልእክት ስሰማ እውነት እላችኋለሁ አለቀስኩ። እንዴት? ብትሉኝ፦ የንግግሯ ቅላጼ ከዛው አሜሪካ እንዳደገችና እንደኖረች በደንብ ያስታውቅባታል። ይህም ሆኖ ግን የአማርኛዋ የጥራት ንግግሯና እንዲሁም የባዕዳንና እንደ ከንቱዎቹ ሰዎች የድንቁርና ጉራ መታወቂያቸዉ የሆነውን እንግሊዝኛ ቋንቋን ወደዛ አሽቀንጥራ ጥላ የማንነቷ መገለጫና መታወቂያ በሆነው በአማርኛ ቋንቋ በዛ የሕጻን ጣፋጭ አንደበቷ አቀላጥፋ ስታናግረኝና ከዚህም በላይ ደግሞ የምትናገረውን ፍሬ ነገር ስሰማት ደስታየን ልነግራችሁ አልችልም። ለዚህ ሁሉ ብቃቷ ግን ትልቁ ድርሻ የወላጅ እናቷ ነው። ስለሆነም ወላጅ እናቷ ሆይ! አንቺ የነብዩ ሙሴ ወላጅ እናት ነሽና የሙሴ እናት አምላክ ይባርክሽ እላለሁ። መልካም ስምና መልካም ተግባር አንድ ሲሆን በጣም ደስ ይላል። እውነትም የበጎ-ሰው ልጅ። አንድ ትልቅ ነገር ልንገራችሁማ። መጭው ንጉሥና ጳጳስ እንደ ሐዋርያት የመላው ዓለም ቋንቋ ባለቤት ናቸው። ያነባሉ፣ ይጽፋሉ፣ ይናገራሉ፣ ይተረጉማሉ። ከሥጋ ትምህርታዊ እውቀታቸው በላይ መቶ እጥፍ እውቀት ከመንፈስ ቅዱስ በጸጋ እንደ ሸማ ይጎናጸፋሉ። ታዲያ ግን ይህ ሁሉ ሆኖላቸው ሳለ ወደ ማንኛውም ውጭ ሀገር ለሥራ (ለሀገራዊና ለሕዝባዊ ጉዳይ ለስብሰባ) ሲሄዱ ሁሉንም ቋንቋ እናውቃለን፣ ምን ጎሎን? ብለው በባዕዳን ቋንቋ አይናገሩም። በአስተርጓሚ በአማርኛ ቋንቋቸው ነው የሚናገሩ። ብዙ ጊዜ በዓለም ቋንቋ የሚናገረው ጳጳሱ ፀሐይ ነው። እሱም ቢሆን መላው ዓለምን ለማስተማርና ለማሳመን፣ ለማጥመቅና ለማቁረብ፣ ለመባረክም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለሚዞር ነው። ስለዚህም ነው ያኔ ኢትዮጵያ ሁለት ፓትርያሪክ ስለሚያስፈልጋት የግድ ሁለት ይሆናሉ ያልኳችሁ። ፓትርያሪክ ፀሐይ ልክ እንደ ፀሓይዋ ፳፬ ሰአት ምንም እረፍተ-ሥጋ የለውም። በምድር ሲኖር በሥራ የተወጠረ ነው። ለማየትና ለመደሰት ያብቃችሁ። እኔስ ከጠረጋ ሞት ለመትረፍና ለመኖር ጓጓሁ። __በሉ እንግዲህ እየተሰናበትኳችሁ ነው፦ በውስጥ መስመሬ የምጽፍላችሁ ግን በትዕግስት ጠብቁኝ እጽፍላችኋለሁ። በሉ ሁላችሁም ደህና ሁኑልኝ። ___የግርጌ ማስታወሻ፦ መንጋ የቆላ ፍየል የሆነው ክርስቲያን ተብየው ጠላቴ የሆነው ወንዱም ሴቱም ሁሉ በእኔ መሠወርና አለመገለጥ ምክንያት ለምን ራሱን አይገልጥም? እስከ መቼ ተሸፍኖና ተሰውሮ? ይኸ ሰው ግን ማን ነው? እያሉ በተጠቂነታቸው በንዴት እያበዱ ነው። እናም ጠላቴ ሆይ! የምትሰሙኝ ከሆነ እኔ ራሴን ለማንም ለማን በየጎዳናውና በየቦታው የምገልጥና የምዞር ምንም እንኳ የዛሬ ስደተኛ፥ ብቸኛና ድሀ ብሆንም ቅሉ ነገር ግን ትናንትም ዛሬም ከቤተ-መንግሥት ውስጥ በክብርና በእልልታ፣ በምስጋናና በዘፈን፣ በትልቅ ድግስና ደስታ የተወለደና የሚወለድ፤ እንዲሁም እስኪሞሸር ድረስ ከዛው ሳይወጣ በክብር የሚያድግና የሚኖር የንጉሥና የንግሥት የጨዋ ልጅ ነኝ እንጅ ከማንም ከማን ያለፍላጎት በየትም ተወልዳችሁ በየትም ስትዞሩ የምትኖሩ እንደ እናንተ ለሽያጭ የተዘጋጀና የሚቀርብ የባሪያ ልጅ ባሪያ መሰልኳችሁ እንዴ?? ወይንስ እንደ እናንተ በማንም በማን የትም ተገዝቶ የትም ለሽያጭ የሚቀርብ ሰው የሆነ እቃ መሰልኳችሁ እንዴ?? ደጋግሜ ነገርኳችሁ እኮ። አይገባችሁም እንዴ?? _______የባላባት ልጅ ተዋርዶ _______እንጨት ሰበራ ቆላ ወርዶ _______ሲያነደው ያድራል ሌሊቱን __________ቀን የሰበረውን። አምኃ ኢየሱስ እኮ ቤቱን ትቶ የወጣው ሀገርንና ሃይማኖትን ሊያቀና እንጅ እንደ እናንተ ዓለምን ሊቀላውጥ አይደለም። እያንዳንድህ ኩራት ማለት ለእኔ ሁለመናየ መሆኑን እወቅ። ለዚህም ነው እኮ ልሸነፍላቸው ያልቻልኩት። መንጋ ቀለዋጭ!!! አሁን ይህን ሁሉ ታነብና በድንቁርና ልማድህ ወንጌል በሰዎች ፊት ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ ይላል። እሱ ግን ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል.......እንደምትለኝ አውቃለሁ። የደንቆሮ መንጋ!! ንባቡን እንጅ ምስጢሩን የት አውቀኸው? ወንጌሉ እኮ ""ወኢታትሕት ርእሰከ ለብእሲ አብድ፤ አላ አትሕት ለጻድቅ ብእሲ"" ትር፦ ባጭሩ ""ስታስተምረው፣ ስትነግረው፣ ስትመክረው፣ ስትገሥጸው፣ ስትዘልፈው ለሚሰማህ፣ ለሚቀበልህና ለሚድነው ለጻድቅ ሰው እንጅ ብትነግረው ብትነግረው ለማይገባው፤ ለማይማርና መልካምን ነገር ለማይናገርና ለማይሠራ ኃጢአተኛ ሰው ራስህን በሱ ፊት አታሳንስ፣ ዝቅ አታድርግ። መልካምን ነገር ማወቅና መፈጸም አይወድምና........."" ነው ያለኝ እንጅ እንዳንተ ድንቁርና አይደለም። ይህን ትምህርት ለወደፊቱ እስኪበቃህ እግትሃለሁና ጠብቅ። በል እንግዲህ ጠላቴ ሁሉ እያንዳንድህ ተቃጠልና እረር። ይህ ሁሉ የመብረቅ ድብደባ ከሚደርስባችሁ ቱቦ አፋችሁን ብታጠቡት ወይም ብትዘጉት አይሻላችሁምን?? መቼ ነው ግን ከልባችሁና ከአፋችሁ ጠማማነት ርቃችሁ በመጥፎ ማንነታችሁ ከመዋረድ ይልቅ በመልካም ማንነት መከበርን የምትጀምሩ?? በመከራ ስትያዙ?? ያሳዝናል!!!! ተጻፈ፦ ከአምኃ ኢየሱስ ገብረ ዮሐንስ ከምድረ እስራኤል ናዝሬት ግንቦት ፳፯ ፪ሺ፲፫ ዓ ም
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment