የዘመኑ አዋቂ ትውልድ እጅግ በሹፈት "ከዚህ በኋላ ንጉስ?" እያለ በንቀት እንደሚያፌዝ ጥርጥር የለውም። ወይ ከመንፈሳዊው ወይ ከምድራዊው ካንዱም ላይሆን ባክኖ ቀረ እንጂ፣ የምድራዊውም ሳይንስ አባቱ Einstein እንኳን "The fourth world war will be fought with stones and sticks" ብሎ ፍንጭ ሰጥቶት ነበር።
ሶስተኛው ላይ የሚፈፀመው እልቂት ከህሊና በላይ በመሆኑና ፍፁም ጠረጋ በአለም በመከናወኑ ምክንያት ከዚያ በኋላ የነበረው ሀያልነት፣ ስርአትና ሁኔታ ሁሉ እንደሚቀያየር መስክሮ ነበር። ከአለም አቀፍ ጦርነቶች ሶስተኛውን ግን ለየት የሚያደርገው የእግዚአብሄር ሰይፍ ፍልሚያውን መቀላቀሉ ነው።
አንዱን ከሌላው ጠቅልሎ፣ የሚያወድም፣ ያልፈጠራትን ምድር ከነፍጡሮቿ የሚያወድም በማይከስም መርዝ፣ ዳግም እንዳይኖሩባት እንኳን በጨረር በሚበክል፣ ከቁጥጥሩ ውጭ የሆነ የጥፋት ትጥቅና ኃይልን በእብሪትና ፉክክር እጅግ እጅግ አብዝቶ የታጠቀው የሰው ልጅ፣ ምድርንና ተፈጥሮን ሊደመስስ በተነሳበት ጊዜ የታጋሹ አምላክም ፅዋ እንደሚሞላ፣ ፍጡራኖቹንና ድሀ ልጆቹን ሊታደግ በቁጣው እንደሚነሳ መገመት ቀላል ነው። በቃሉ የፀናች ተፈጥሮ ሳይቀር በአስፈሪ አውሎ ነፋስ፣ በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በውሀ መጥለቅለቅ ወዘተ በመላው አለም ላይ በትሯን እንደምታፀና መገመት አያዳግትም። የሰለጠኑት ሁሉ ምድር በተነሳችባቸው ጊዜ
ወደ እግዚአብሄር ተስፋ ምድር መግባት ምኞታቸው እንደሚያደርጉ ብዙዎቹም እንደማይሆንላቸው የተነገረውም ይፈፀማል።
በኢትዮጵያ ላይ ለዘመናት ሲነገር የኖረው ትንቢት ራዕየ ሳቤላ
Blogger Comment
Facebook Comment