ባለቀለም የመስታወት መስኮት ኢትዮጵያዊውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያሳያል

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ኢትዮጵያ በ'ሰሜን ምስራቅ' አፍሪቃ እንደምተገኘው፣ በ'ሰሜን ምስራቅ' አሜሪካ በምትገኘዋ የሮድ አይላንድ ግዛት የ፻፶/150 አመት እድሜ ያለው ባለቀለም የመስታወት መስኮት ኢትዮጵያዊውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያሳያል። ይህን እስካሁን ተሰውሮና ብዙ አትኩሮት ሳያገኝ ቀርቶ የነበረውን ክስተት ተከትሎ ስለ ዘር በጣም አነቃቂ ጥያቄዎች በመነሳት ላይ ናቸው።

በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጥበብ ታሪክ ምሁር ሃድሊ አርኖልድ በሮድ አይላንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተገኘውና የ፻፶/150 አመት እድሜ ያለው ባለ መስታወት መስኮት ኢየሱስን እንደ ኢትዮጵያዊ ጠቆር ያለ ቆዳ ያለው ሰው እንደሆነ አድርጎ እንደሚያሳይ ተናግረዋል ።

..አ በ 1877 የተተገበረው መስኮት በዓይነቱ የመጀመሪያ ሊሆን ይችላል ብለው ምሑራኑ ያስባሉ። የሥነ ጥበብ ታሪክ ምሁር ቨርጂኒያ ራጊን 'ይህ በአሜሪካ ባሕል ውስጥ እንደ ዋና ምልክት ሆኖ ሊቆም ይገባዋልብለዋል።

ጠቆር ያለዉ ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን ትዕይንቶች ከሴቶች ጋር ሲነጋገር የሚያሳየው ይህ በጽዮን ቀለማት የደመቀው መስታወት ስለ ዘረኝነት፣ ሮድ አይላንድ በባሪያ ንግድ ውስጥ ያላትን ሚና እንዲሁም የሴቶችን ቦታ በተመለከተ በ፲፱/19ኛው ክፍለ ዘመን የኒው ኢንግላንድ/አዲሷ የእንግሊዝ ማህበረሰብ የነበራትን አስትዋጽዖ ይጠቁማል።

ይህ ድንቅ የመስተዋት መስክቶ ስዕል የተሰቀለው በዋረን ከተማ ለረጅም ጊዜ በተዘጋው የቅዱስ ማርቆስ ኤጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን እ..በ 1878 .ም ላይ ነበር።

በዎርሴስተር፣ ማሳቹሴትስ በሚገኘው የቅዱስ መስቀል ኮሌጅ የሰብአዊነት ፕሮፌሰር የሆኑት ቨርጂኒያ ራጊን እና የባለቀለም መስታወት ጥበብ ታሪክ ባለሙያዋ፤ “ይህ መስኮት ልዩ እና ያልተለመደ ነው፣ ይህን ምስል ለዛ ዘመን አይቼው አላውቅም።ብለዋል።

ባለ ፲፪/12 ጫማ ርዝመት እና ባለ ፭/5 ጫማ ስፋት ያለው ይህ መስኮት ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦችን ያሳያል። ሴቶቹም ጥቁር ቆዳ ያላቸውና ከክርስቶስ ጋር እኩል ሆነው ይታያሉ። አንዱ፡ ከሉቃስ ወንጌል፡ ክርስቶስ ከአልዓዛር እህቶች ከማርታ እና ከማርያም ጋር ሲነጋገር ያሳያል። ሌላው ደግሞ፡ ከዮሐንስ ወንጌል፡ ክርስቶስ ጉድጓድ አጠገብ ለሳምራዊቷ ሴት ሲናገር ያሳያል።

በእውነት ድንቅ ነው፤ እንግዲህ ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት ለወቅቱ በጭራሽ በማይታሰብ መልክ በአሜሪካ 'ኢትዮጵያዊኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተስሎ ይታይ ነበር። አባቶቻችን ሲስሏቸው የነበሩትን ዓይነት ስዕሎችን ተከትሎ ነው የተሳለው። የጽዮን ቀለማቱም እንዲሁ።

አዎበዛሬዋ ዓለም ሕዝቦች ከመቼውም ጊዜ በከፋ የዘር ጉዳይ ላይ በጣም ስሜታዊና ጠበኞች እየሆኑ ነው። ባገራችንም በተቀሩት አገራትም የምናየው ነው። ሰሞኑን እንኳን መኖርና አለመኖሯ አጠራጣሪ የሆነችው የጥንታዊቷ ግብጽ ንግሥት ክሊዮፓትራ በኔትፍሊክስ ፊልም ላይ እንደ ጥቁር መሳሏ በግብጽና በመላው የምዕራቡ ዓለም ከፍተኛ ውዝግብ በማስነሳት ላይ ነው። "እንዴት አንዲት ጥቁር ሴት የእኛ ንግሥት ሆና ፊልም ላይ ትታያላች?! ይህ በጭራሽ መሆን የለበትም፤ ክሊዮፓትራ ብሎንድ የጸጉር ቀለም የነበራት ግሪካዊት ነበረች...” እንግዲህ አሜሪካዊቷ ተዋናይ ክልስ ናት፤ እንደሚወራው ክሊዮፓትራም ክልስ ነበረች። ግን ምን ልዩነት አለውክሊዮፓትራን ጨምሮ የያኔዎቹ ግብጻውያን እኮ ወንጀለኞች ነበር፤ ታዲያ ማንም ድራማ ወይንም ቴአትር ቢሠራስ ምን ክፋት አለውታሪክ ተቀማን፤ ነውየማን ታሪክየዛሬዎቹ ግብጻውያን ከኮፕቶች በቀር ሁሉም ወራሪ መሀመዳውያን አረቦች ናቸው። ለመሆኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ብሎንድና ሰማያዊ ዓይኖች ያሏቸው ተዋናውያን አልነበሩም እንዴ ሲወክሉት የነበሩት?! ንግሥታችንን ሳባን/መከዳን ለረጅም ጊዜ ሲወክሏት የነበሩት ነጭ ተዋናውያን አልነበሩምንእንዴት ነው ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ እንኳን ዛሬም በቆዳ ቀለም ላይ ያተኮረ ልዩነትን ፣ ጥላቻን እና ትንኮሳን የምታስተናግደውበእውነት ይህ ስንፍና፣ ኋላ ቀርነትና ውድቀት እጅግ በጣም አሳፋሪ ነው!

ለማንኛውም፤ ይህን ድንቅ የጌታችንን ስዕል አመልክቶ ሌላው የሚገርመው ነገር ደግሞ ይህ የመስተዋት መስኮት ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተገጠመ መሆኑ ነው። ባለፈው ሳምንት ልክ በዚህ በሰኞ ዕለት የሐዋርያው/ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስን ዓመታዊ በዓል በዚህ መልክ አክብረነው ነበር

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment