በተዋሕዶ ክርስትና እና ቤተ ክርስቲያን ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ከሁሉም አቅጣጫ እየመጣ ነው።

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

አባቶቻችንን በየገዳማቱ ማጥቃትና መግደል የመጨረሻው ዒላማቸው እንደሆነ ብናውቅም፤ መጀመሪያ ግን ክርስቲያናዊ ሕይወትን በመላው የማሕበረሰብ ክፍሎች፣ በየመንገዱ፣ በየመስሪያ ቤቱ፣ በየጎረቤቱ በመቅረብ ብሎም ወደ ቤተክርስቲያን በሱቅ መልክ፣ በጎብኚ መልክ፣ የመስገጃ ቦታ በመሻማት ቀስ በቅስ ጠጋ ጠጋ በማለት ይዋጉታል።

ይህ ክስተት ላለፉት ዓመታት የምናየው ነው።  በተለያዮ አድባራትና ዓብያተ ክርስቲያናት የሕዝበ ክርስቲያኑን መንፈሳዊ እርጋታና ሰላሙን ለማወክ ገበያዎችን ይከፍታሉ፣ የመዝሙር ሲዲዎችን በከፍተኛ ጭኸት የሚያስተዋውቁትን መኪናዎችን አምጥተው ያቆማሉ፤ ባሕላዊ ዘፋኞችን እና ጨፋሪዎችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ግቢ ያስገቧቸዋል። የስከሩ ጨፋሪዎች ሁሉ ሲገቡ የሚታዩባቸው በዓላት አሉ። ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሌላ ቦት ባሕላቸውን ቢያስተዋውቁ ባልከፋ፤ ነገር ግን ያመጧቸው ሆን ተብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው "ሁሉም ባሕል ነው፣ ሁሉም አንድ ዓይነት ነው" የሚለውን አጀንዳ ለማራማድ ይጠቀሙባቸው ዘንድ ነው።

ከራያ ያመጧቸውን የባህል ጨፋሪዎች (ድሮም ወደ አክሱምና ላሊበላ አካባቢ አምጥተው እዚያ እንዲሰፍሩ መደረጋቸው የጣዖቱን ዋቄዮ አምልኮት ያስፋፉ ዘንድ በእባባዊ መልክ በማቀድ ነበር) በየአብያተ ክርስቲያናቱ እንዲገቡ በማድረግ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ለማበላሸትና እምነታችንንም ወደ ባሕላዊ ሥርዓት ለመለወጥ ይቻላቸው ዘንድ በደንብ አቅደውበት ነው።

በነገራችን ላይ፡ እንደ "መስቀል" እና "ጥምቀት" የመሳሰሉትን ክብረ በዓላት የየተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት፤ በምህጻሩ UNESCO በሚባለው ድርጅት እውቅናን እንዲያገኝ መደረጉ መንፈሳዊ የሆነችውን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ወደ ዓለማዊው የባህል፣ ወግና ልምድ ሥርዓት ይለወጥ ዘንድ የተጠነሰሰ ዲያብሎሳዊ ሤራ ነው። ቤተ ክርስቲያንን የባሕል ተቋም ለማድረግ የሚሠራ ሥራ ነው።

ቤተ ክህነትም ሆነች ምዕመናን ክርስቲያናዊ በዓላታቸውን በአውሬው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል ዕውቅና እንዲያገኙ ከመታገል መቆጠብ ይኖርባቸዋል፤ አሊያ ይህ ትልቅ ስህተት ነው የሚሆነው።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment