✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ጥንታውያኑ የክርስቲያን ሃገራት አርሜኒያ እና ኢትዮጵያ በቅድስት አርሴማ ተሳስረዋል፤ መጭው መስከረም ፳፱/29 ቀን ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት ያረፈችበት ዕለት ነው።
ከሚበደሉት፣ ከሚሰቃዩትና ለሰማዕትነት ከሚበቁት ክርስቲያን ወገኖቻችን ጋር አንድነትንና ፍቅርን የማሳየቱን ባሕል እናዳበር፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በዚህ በኩል በጣም ደካሞች ነን! እስኪ "አርሜኒያ" ብላችሁ ጉግል ላይ ይተይቡ፤ በብዛት የሚወጡት ለአዘርበጃን እና ቱርክ ድጋፋቸውን የሚያሳዩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን፣ ፓኪስታናውያን፣ ዓረቦች ወዘተ መጣጠፎችና ነበር።ተንቀሳቃሽሽ ምስል ወድምጽ ናቸው። ጠላት ምንም ሳይኖርና እውነትን ሳይዝ 24/7 ለዲያብሎስ ቅስቀሳ ሲያደርግና ለአጋሩ ድጋፍ ሲሰጥ ይታያል።
አውሬዋ የግራኝ ሞግዚት ቱርክ በአርሜኒያውያን ክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ ከመቶ ዓመታት በፊት የጀመረችው ዘር ማጥፋት (ጀነሳይድ)1 ለመቀጠል ተነስታለች። አርሜኒያ ስትነካ ኢትዮጵያም ትነካለች፣ በጥንታዊው የአርሜኒያ ክርስቲያን ሕዝብ የሚሰነዘረው ጥቃት በጥንታውያኑ ኢትዮጵያውያን ላይም እየተሰነዘረ ነው። በመላው ዓለም በክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ በተለይ በሙስሊሙ ዓለም ለዘመናት እየተካሄደ ያለውን ጭፍጨፋ ከሃያ ሰላሳ ዓመታት በፊት አስቀድመን ብናወግዝና አንጋፋ የድጋፍና ተቃውሞ ሰልፎችን በየከተማው ብናካሂድ ኖሮ እርግጠኛ ነኝ አሁን ሕዝብ ክርስቲያኑ የተኛበት አልጋ ላይ ባላንቀላፋ ነበር፤ ወገኖቻችንም ዛሬ ለምናየው ግፍና ሰቆቃ ባልበቁ ነበር።
እምነትን በሥራ መዳንን በሕይወት መግለጥ ያስፈልጋል።
Blogger Comment
Facebook Comment