የሰውን ሕይወት የሚያበላሹትና አገር የሚያጠፉት ክፉ መካሪዎች ናቸው!


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ሰይጣን አዳም አባታችንንና ሔዋን እናታችንን በገነት በነበሩበት ጊዜ በሥጋ ከይሲ (በእባብ አካል) ተሰውሮ ተሸሽጎ ክፉ ምክርን መክሮ አምላክ አታድርጉ ያላቸውን እንዲያደርጉ በማድረግ እግዚአብሔርን እንዲበድሉ ኃጢአት እንዲሠሩ ትዕዛዙን እንዲያፈርሱ አድርጓቸው እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምርናል።

ቅዱስ ዮሐንስ ሲያገለግል ዓላማው ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘት እንጂ ሰዎችን በእርሱ ዙሪያ መሰብሰብና መክበር አልነበረም፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ እንደሚነግረን «ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳ፣ በዮርዳኖስ ዙሪያ ባለው ነገር ሁሉ ሰዎች ወደ እርሱ ይጎርፉ ነበር፡፡» /ማቴ.፫÷፭-፡፮/ እርሱ ግን «እኔ በውኃ ለንስሐ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡» እያለ ሰዎቹ እርሱን እንዲከተሉ ሳይሆን የጌታችንን መምጣት ተስፋ እንዲያደርጉ የሚያደርግ ትምህርት ያስተምራቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

የመጀመሪያዎቹ ጌታችንን የተከተሉት ደቀመዛሙርት የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ነበሩ፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘመን መታጀብ /በሕዝብ መከበብ/ ለሚያስደስተን የእግዚአብሔርን ሳይሆን የእኛን ተከታዮች እንደ ፈሪሳውያን ለምንፈልግ አገልጋዮች ትልቅ ተግሳጽ ነው፡፡

እግዚአብሔር ከመልካም ምክር እንዲያገናኘን ክፉውን እና መልካሙን ምክር እንድለይ ማስተዋሉን እንዲሰጠን ቅዱስ ፍቃዱ ይሁን!

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment