ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የሰው ልጅ ከዶሮ ባነሰ ደረጃ የሚከበርበት ዘመን ላይ እነገኛለን። የተሰወሩትን ሴት ተማሪዎች ለመፈለግ ከመሄድ ይልቅ አንድ በሽተኛ ዶሮ ለመግዛት ቀኑን ሙሉ ሲንገዋለል የሚውል ትውልድ የፈራበት ዘመን ነው።
ምስኪኖቹን ወገኖቻችንን ማን ያስብላቸዋል? ጠበቃቸውስ ማን ነው? ጉዳዩንስ ማን ይከታተለዋል? ለመሆኑ "ነፃ" የሚባሉት የኮሮና ቁጥር ደርዳሪ መገናኛ ብዙኅን የት ደረሱ? ቤተ ክህነት የት አለች? ማሕበረ ቅዱሳንስ ምነው ፀጥ አለ? ምነው የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ሴት ህፃናት ዕጣ ፈንታ ሊያሳስባቸው አልቻለም? የድሃ ገበሬ ልጆች ስለሆኑ? ተጠቂዎቹ የተለመዱት ክርስቲያኖች በመሆናቸው?የደምቢዶሎ ተማሪዎች ጉዳይ ቀስ በቀስ ተረስቷል፤ የናዝሬቱ ሕፃናትማ በሁለት ቀናት ብቻ ነው የተረሳው። ምን ዓይነት ዝቅጠት ቢሆን ነው?! "ለመሐመዳውያኑ እና ለኦሮሞ ጉዳይ" ጠበቃ ለመቆም ከመሐመዳውያኑና ከኦሮሞዎቹ በፊት ቀድመው የሚጮሁትና ገንዘብ የሚያሰባስቡት "ሁሉን አቃፊ" መሀል-ሰፋሪዎች የት ደረሱ? ይህን ሁሉ ወንጀል "ትግራዋይ" የምትሏቸው የጥላቻ ዒላማዎቻችሁ ስላልሠሩት? ወይንስ ችግሩ የቤቶቻችሁን በር ገና ስላላንኳኳ? ወኔያማው ተቆርቆሪነታችሁ ለኢትዮጵያ፣ ለተዋሕዶ ሃይማኖቷ ባጠቃላይ በኢትዮጵያዊነት ላይ ለተነሱት የሀገር ጠላቶች ብቻ እንደሆነ ለማየት አትችሉምን? ምርጫዎቻችሁ ሁሉ ከስሜታዊነት በመነሳት እንጅ አርቆ በማሰብ አይደለም፤ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ ቢወገድ ወይም የሚያወጣውን ካዝናውን በኢትዮጵያ ስም በሚሰበሰበው ገንዘብ ከሞላ በኋላ ቤተ መንግስትን ለአል-ሸባብና ለኦነግ አስረክቦ ቢኮበልል ሙስሊሙን ሙስጠፌን ለመተካት ፣ የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ደግሞ ኦሮሞው አቡነ ናትናኤል እንዲሆኑ ለማድረግ በማዘጋጀት ላይ ናችሁ፤ አይደል?! አልማር-ባይ፣ አሳፋሪ፣ ከንቱና ግብዝ ትውልድ!
ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ሕፃናትን የሚገድል አረመኔ የአሕዛብ መንግስት በኮሮና እና በቢጫ ወባ ብታልቅለት ደስተኛ ነው። ህጻናትን ለአምላኩ ለዲያብሎስ መስዋዕት ባደረገ ማግስት በጋኔን የተበከለውን ደሙን "ሊሰጥ" ወደ ሆስፒታል አመራ፤ አላጋጭ የቃየል ዘር! ለመሆኑ አንድ ሙስሊም ሲገደል አይታችሁ ወይም ሰምታችሁ ታውቃላችሁን? አንድም!በጭራሽ!80% ክርስቲያን በሆነባት በዛሬዋ ኢትዮጵያ እንደምናየው በተፋጠነ መልክ አንድ ባንድ እየተገፋ፣ እየተፈናቀለ፣ እየተመረዘና እየተገደለ ያለው ሕዝበ ክርስቲያኑ ብቻ እንደሆነ ልብ እንበል።
Blogger Comment
Facebook Comment