አስደሣች ወይስ አሣዛኝ...?


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

በእኛ ላይም የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ላከ፤ የቅድስት ቢተ ክርስቲያንህንም ደጆች በምሕረትና በሃይማኖት እንዲከፈቱ አድርግልን። እስከ መጨረሻዪቱ ሕቅታም ድረስ ልዩ ሦስትነትህን ማመንን ፈጽምልን።

የቤተክርስቲያን ሸምጋይ እና አስታራቂ ሆኖ የመጣው ልወደድ-ባይ የአውሬው መንግስት ኮሮናን ተገን አድርጎ ሕዝበ ክርስቲያኑን ከቤተ ክርስቲያን ለማራቅ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ እንደሆነ እያየነው ነው። የክርስቶስ ተቃዋሚው የቤተ ክርስቲያንን ቦታ ለመውረስ ተወዳጅነት እያጡ የመጡትን የመስኮተ ትዕይንት (ቴሌቪዥን) እና ኢንተርኔት ጣቢያዎች (ኢቢሲ፣ ፋና) የቅዳሴ ሥነ ስርዓትን በቀጥታ እንዲያስተላልፉ አድርጓል። የቤተ ክርስቲያንን እና ሜዲያዎቿን ኃላፊነት በመንጠቅ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፎች ይመታል ማለት ነው።

ሲጀመር ዲያብሎስ አስታራቂ ሆኖ እንዲገባብን መደረግ አልነበረበትም። በኢትዮጵያ ርትዕት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየሠሩት ያሉት ወንጀል ለይቅርታ፣ ለዕርቅና ለንስሐ የሚያበቃ አይደለምና።

 በኮሮና ድራማ ተጠምደን ጸጥ ብለናል፤ አይደል! አዎ!የበሬውን አንጀት ለሞኙ ኢትዮጵያዊ ሰጥቶ አፉን ይዘጋና ሰንጋውን ለራሱ በማግበስበስ ላይ ነው።ትንሽ ከፊት ሲሆን ሀገር ያሳንሳል!

"....ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው...የሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸው...ከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ... ብለህ ተርትባቸው" ብሎን የለ ተሳላቂው አብዮት። በመስቀል አደባባይ ደመራ ዕለት በሬው የተላከውም በቤተ ክርስቲያን እና ክቡር መስቀሉ ላይ ለመሳለቅ ታስቦ ነበር። አንርሳው!

ወገኖቼ መታለሉ ይብቃ! ይብቃ! ይብቃ! ንቁ!እንንቃ! ነፍሱ እንዳይታወክበት የሚሻ የተዋሕዶ ልጅ ወደ እውነት ይመለስ።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment