ለምን የአጼ ዩሐንስ ሐወልት አይሰራም?


መጋቢት ፩ - አፄ ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ነገስት ዘ-ኢትዮጵያ የፅዮን ጠባቂ ፻፴፩/131ኛው የመስዋዕት ቀን።
"እኔ ዮሐንስ እንደሆንኩ ሐሳቤም፡ ነፍሴም፡ ሃይማኖቴም አንዲት ናት!!! የሀገሬን መደፈር የሕዝቤን መዋረድ በሕይወቴ ቁሜ አላይም፤ አልሰማም!!! የሚንቁኝንና አንበገርልህም የሚሉኝን እገጥማለሁ ብዬ ጦሬን ወደ ወንድሞቼ አላዞርም" አንገቱን የሰጠው ንጉሣችን ዩሐንስ ፬ኛ።

ይህ ጉዳይ ቀላል ጉዳይ አይመስለኝም፤ ሀገርንና እያንዳንዱን ግለሰብ የሚመለከት ወቅታዊ ጉዳይ ነውና ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል በግልጽና በንጹሕ ልብ ሊነጋገርበት የሚገባው ጉዳይ ነው። ጠላት ከብዙ አቅጣጫ እየተለሳለሰ መጥቷል።

ከተማ ውስጥ ስዘዋወር አንድም የአፄ ዮሐንስን ወይም የራስ አሉላ አባ ነጋን ፎቶ የለጠፈ ታክሲ አታዩም። (የአፄ ቴዎድሮስ፣ የአፄ ምኒልክ፣ የአፄ ኃይለ ሥላሴ፣ የመንግስቱ ኃይለ ማርያም፣፣ የቼጉቬራ ወዘተ ፎቶዎች በብዛት ተለጥፈው ይታያሉ)። እንዲያውም ጠለቅ ብዬ ስሄድ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ ለ አፄ ዮሐንስ እና ራስ አሉላ መታሰቢያነት ይውል ዘንድ በስማቸው የቆመ ሐውልት፣ የተሰየመ መንግድ፣ አደባባይ፣ ትምህርት ቤት ወይም ሆስፒታል አንድም የለም። ቅዱስ ያሬድ እንኳን ከሙዚቃው ትምህርት ቤትና ዘንድሮ ለይስሙላ ከተመረቀው አደባባይ በቀር መንገድም ሆነ ሰፈር አልተሰየመለትም። የቤተ ክርስቲያን አባት ለሆነው ቅዱስ ያሬድ በስሙ የተሰየመው ቤተ ክርስቲያንም አንድ ብቻ ነው። የሚገርም ነገር አይደለም? ቁልፍ የሆኑ የከተማዋ ቦታዎች ካርል አደባባይ፣ ሃይሌ ጋርሜንት፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ውንጌት፣ ቸርቺል ጎዳና፣ ጆሞ፣ ፉሪ፣ ጉለሌ ወዘተ እየተባሉ በባዕዳውያኑ ስም ይጠራሉ፤ ለኢትዮጵያና ተዋሕዶ እምነቷ የሞቱላት ግን የሚያስታውሳቸው እንኳን የለም። ለእነ ቦብ ማርሊ እና ካርል ህይንስ ቡም ኃውልት ቆሞላቸዋል በመንግስቱ ኃይለ ማርያም በሲባጎ ታንቀው ለተገደሉት አቡነ ቴዎፍሎስ የተሠራው ኃውልት ግን በአደባባይ እንዳይቆም ተደርጓል። በእርኩስ ቱርክ ለተሰዉት ለእነ አፄ ዮሐንስማ የማይታሰብ ነው።

እስኪ ይህ ለምን እንደሆነ እራሳችንን በንጹህ ልብ እንጠይቅ?

1ኛ. ደገኛ የሰሜን ሰው ስለሆኑ?
2ኛ. ምርጥ የተዋሕዶ አርበኞች ስለነበሩ?
3ኛ. ጥልቅ የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን ስለያዙ?
3ኛ. ሰንደቃችንን እና አማርኛን ብሔራዊ ስላደረጉ?
4ኛ. ባዕዳውያኑ የኢትዮጵያ ጠላቶች ስለማይፈልጓቸው?
4ኛ. ቆላማዎቹ ኦሮሞዎች እና ሙስሊሞች ስለሚጠሏቸው?
5ኛ. ብዙ አብሮ ከመኖር የተነሳ ሰው በዋቄዮ-አላህ መተት ስለተያዘ?

በክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ቱርኮች የተጨፈጨፉት አባቶቻችን እንባቸውን እያረገፉ ነው! በቱርክ ሰይፍ የታረዱት አፄ ዮሐንስ መቃብራቸውን እይገለበጡ ነው! እግዚአብሔርም በትውልዱ እያዘነበት ነው።

በዛሬዋም ኢትዮጵያ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት እና አፄ ዮሐንስ ችግር ያለው ከፍተኛ ችግር ያጋጥመዋል!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment