ኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካ እንድትከተል ያደረገችው አሜሪካ እራሷ በፖለቲካ ዘውገኝነት እየተፈረካከሰች ነው።

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

የፖለቲካ ዘውገኝነት የአሜሪካን ውድቀት እያስከተለ ነው። ኢትዮጵያ መውጫና መግቢያ በር እንዳይኖራት ያደረገችውና 361 የባሕር በሮች ያሏት አሜሪካ ከ19 ዓመታት በፊት ስትደግፋቸው የነበሩት መሓመዳውያን ባደረሱባት የሽብር ጥቃት ልክ እንደ ኢትዮጵያ አንድም የባሕር በር እንደሌላት ሀገር ሆና ነበር። ዛሬ ደግሞ ኦሮሞ ሽብር ፈጣሪዎችንና ግብጽን እሹሩሩ በማለት ላይ የምትገኘዋና "አንድ ሕዝብ፣ ሁለት ፓርቲዎች" እያለች የምትመጻደቀው አሜሪካ መቶ ጎሳዎችና መቶ የፖለቲካ ፓርቲዎች ካሏት ኢትዮጵያ በከፋ የፖለቲካ ዘውገኝነት ቀውስ ውስጥ ገብታ ትታያለች።

ርዕሰ ብሔር ትረምፕ ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል በሚል ክስ በዲሞክራት ፓርቲ አባላት የሚመራው የተወካዮች ምክር ቤት / ኮንግረስ    ትራምፕ ከሥልጣን እንዲወርዱ ትዕዛዝ ሰጠ። ርዕሰ ብሔር ትራምፕ በአሜሪካ ኮንግረስ የተከሰሱ ሶስተኛው የአሜሪካ ርዕሰ ብሔር ሆነዋል ማለት ነው።

አሁን ርዕሰ ብሔር ዶናልድ ትራምፕ ሴኔት ፊት ቀርበው የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ይገደዳሉ ማለት ነው።
በጣም የሚገርም ነው፤ በርዕሰ ብሔር ትራምፕ የምትመራዋ አሜሪካ ርዕሰ ብሔሮች ከሊንተን፣ ቡሽና ኦባማ ካመጡባት በሽታ በማገገም ላይ ነበረች፤ ነገር ግን በሁለት ፓርቲ ብቻ የምትመራዋ አሜሪካ በምርጫ በተሸነፈው በዲሞክራቲክ ፓርቲው በኩል በጣም አሳፋሪ የሆነ የጥላቻ ዘመቻ በርዕሰ ብሔሩ ላይ ላለፉት ሁለት ዓመታት ካካሄደ በኋላ ሥልጣኑን ያለምርጫ በአቋራጭ በእጁ ለማስገባት ይሞክራል። ይህ አካሄዳቸው አሜሪካ የውድቀቷ ገደል አፋፍ ላይ እንድትገኝ እያደረጋት ነው።

የሚገርመው ደግሞ እነርሱ ወደ እኛ መጥተው የሀገራችን ፈላጭ ቆራጮች ሲሆኑና፡ የእኛዎቹም እየሞተች ያለችውን ሃያል ሀገር ለእርዳታና ድጋፍ ደጅ ሲጠኑ ማየቱ ነው። ሲ.አይ. ኤ / ኤፍ.ቢ.አይ እና ሌሎቹ የድብቁ ሉሲፈራዊ መንግስት ተቋማት ፈራርሰው የሚወድቁበት ጊዜ ተቃርቦ እያለ እኛ ታዲያ በእግዚአብሔር ፈንታ እነርሱን መለማመጥና መፍራት ይገባናልን?

እስኪ ይህን ቅሌት በጥሞና እናነፃፅረው፤ ለሀገራቸው ብዙ በጎ የሆኑ ሥራዎችን በሁለት ዓመታት ብቻ የሠሩትን ሀገር ወዳዱን ርዕሰ ብሔር ትራምፕን ያለምንም ማስረጃ ከሥልጣናቸው እንዲወገዱ ለማድረግ እየተሞከረ ነው፤ በሀገራችን ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ጊዜ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ችግርና ሰቆቃ ያመጣው፣ ከሃዲው፣ ሌባው፣ ቀጣፊው፣ ገዳዩ፣ ሥልጣኑን ያላግባብ በመጠቀም ላይ ያለው ወሮበላው ግራኝ ዐቢይ አሕመድ አሊ በቂ ማስረጃዎች እያሉን ከሥልጣን እንዲወገድ በማድረግ ፈንታ ሽልማቶች ይሰጠዋል። የተገለባበጠች ዓለም!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment