ተዋሕዶነት ትዕግስት ነው ፤ ፈራጁ እግዚአብሔር ነው።

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ግራ ጉንጭህን ሲመታህ ቀኙን ስጠው የተባለው በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ለሚኖሩ የእርስበርስ ጠላቶች እንጅ ለክርስቶስ ተቃዋሚዎች ወይም ለእግዚአብሔር ጠላቶች አይደለም። እንግዲህ ቀሳውስቱ ሲታረዱ፣ ዓብያተክርስቲያናቱ ሲጋዩ “ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ መቃጠል በመቃጠል፥ ቍስል በቍስል፥ ግርፋት በግርፋት ይከፈል” በማለት እስካሁን ድረስ ኢማሞቻቸውን አልገደልንም፣ መስጊዶቻቸውንም አላቃጠልንም፤ ልብ በል ወገን፤ በአንድ ዓመት ብቻ ሃያ አብያተክርስቲያናት ሲቃጠሉ ሕዝበ ክርስቲያኑ አንድም መስጊድ አላቃጠለም። ነገር ግን እስከ መቼ ይመስላቸዋል የተዋሕዶ ልጆች ዝምታና ትእግስትተዋሕዶ ክርስቲያኑን ከሌሎች ክርስቲያኖች ክሚለዩት ዋና ማንነቶች መካከል፤ ተዋሕዷውያን አይሁዶችም ክርስቲያኖችም መሆናቸው ነው።
አምላካችን በ [መክብብ ፫:]እንዲህ ብሎናል፦
ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤ ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሣቅም ጊዜ አለው፤ ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመተው ጊዜ አለው፤ ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።”
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment