የበቁት ገዳማውያን አበው ስለ ኢትዮጵያ ትንሣኤ ምን ትንቢት ተነበዩ?




በ፲፪፲፪ ዓ.ም ጀርመን የሚገኘው ብራና መጽሐፍ ነፍሳቸውን ይማረው እና አለቃ ታምሩ በኢትዮጵያ ከሠሩት ታላቅ ሥራ አንዱ፣ትንቢት - ዘኢትዮጵያ በ፲፪፲፪ በግዕዝ የተፃፈውን ወደ አማርኛ በ ፲፱፬፱ ዓ.ም ተርጉመው አሳትመውታል ::

፩ኛ) ጣሊያን የተባለ ወራሪ ተነስቶ ኢትዮጵያና ህዝቧን ሊወጋ ይነሳል፣በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጊዮርጊስ በፈረስ ሆኖ አድዋ ላይ ይዋጋል። እውን ሆኗል

፪ኛ) በቋራ አንበሳ ተነሳ ይልና የአፄ ቴድሮስን መምጣት ቀድሞ በትንቢቱተናግሯል ::

፫ኛ) ዘመነ ጎንደር እያለቀ ንግሥናው ወደ ሸዋሊ መጣ ሲል ፋሲል ግቢ የሸረሪት ድርያ ደራበታል፣ የቁራ ማደሪያም ይሆናል። እውን ሆኗል ::

፬ኛ) ስለ ንጉሥ አጼ ኃይሌ ሥላሴ ደግሞ ፈረሳቸው ሳይቀር ይከዳቸዋል ይላል ::

፭ኛ) ልጅ ኢያሱን ያወሳል:-ኢያሱን ላለመካድ መኳንንቶች ተማምለው ነበር በኋላ ግን ኢያሱን ክደው የጣይቱን ወንድም ብጡለን ራስ ጉግሳን ገድለው በዛየተነሳ መኳንንቱና እና ተፈሪ መኮንን ጥቁር ውሻ ይወልዳሉ ይላል ::

የመግስቱ ኃይለ ማርያምን መምጣት ቀደም ብሎ ተነግሮአል:- ተኩላ ይመጣል ንጉሡን ይገድላል ሃይማኖት የለውም ጉግማንጉግ ሆኖ በክፉ ይበረታል።

በዚያን ዘመን ወላድ እናት ደረቷን ትመታለች ይላል፣ በቀይ ሽብርና በብሔራዊ ውትድርና፣ "ተኩላ ይመጣል ጠቦቶችን ይበላል" የተባለውትቢንትተፈፀመ::

፮ኛ) ትንቢት ፳፯ ዓመት ስለገዙት ወያኔዎች ጉንዳን ከሰሜን ይመጣል የኢትዮጵያን መዓዛ ይመጣል፣ ይህ ጉንዳን እንደጢስ ተኖ እንደ አመድም ብን ብሎ ይጠፋል ብዙዎቹም ጉንዳኖች ያግዛሉ ያጋግዛሉ ነገር ግን ሀብታቸውን እንኳን የትም ይዘው ለመሄድ እድሉን አያገኙም :: 

ወየው የሚሉበት ጊዜ ይመጣል። ከዚያ በኋላ ተመልሰው ለመምጣት ብዙ ይጥራሉ መከራም ያደርሳሉ ግን አይመለሱም። ከሰሜን መረብ ከተሻገሩ በኋላ ዝም በሏቸው አባይን ተከዜን ከተሻገሩ በኋላ እርስ በእርሳቸው ይተላለቃሉ።

ኤርትራውያንም ኢትዮጵያ ውስጥ እህል ውሃ አላቸው :: በዚያን ዘመን ደግ የሠሩ ሠዎች ምነው ብለው እስኪፀፀቱ ድረስ ፍዳቸውን ይቀበላሉ ::

ትንቢት ከጉንዳኖች (ወያኔዎች) ውድቀት በኋላ እሳት ይመጣል፣ በዚያን ጊዜ የአህዛብ ንጉሥ ይነግሣል ለቤተክርስቲያን እና ለክርስቲያኖችም መልካም ያልሆነጌዜ ይሆናል !! ብዙዎች ድንገት እንደ ወጡ ይቀራሉ፣ፍትህን አያገኙም።

በዚያን ዘመን አብዛኛዎች በዳርሀገር ያሉክርስቲያኖች መከራ ያገኛቸዋል ደም ይፈሳል ሠማዕትነትን ይቀበላሉ ትልቅ ክብር ያገኛሉ። ከሠማዕትነት ይቆጠርላቸዋል ብዙዎች ወጣቶችም ይህንን ክብርይ ቋደሳሉ !!

እንደ ቅዱስ መርቆሪዎስ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሠማዕትነት ይቆጠርላቸዋል ::

የኑሮ ውድነት ርሃብ ቸነፈር የከፋ ይሆናል :: የኤድስ በሽታምየ ሚመሰገንበት ጊዜ ይመጣል :: ምክንያቱም የኤድስ በሽታ ለንስሃ ጊዜ ይሰጣል ከዚያ በኋላ የሚመጣው መቅሰፍት ድንገተኛ ነው። ለንሰሃ ጊዜ የማይሰጥ አጣድፎ የሚገል  በሽታ ሳይሆን አይቀርም ::

የሚቆመው የአህዛብ መግስት ለዓለም መግስታት ያስቸገረ ይሆናል :: ሰላም ሳይኖር ስለ ሰላም የሚያወራ ፍርድ የሚያጓድል ደሃ የሚበድል ፍቅር ሳይኖር ስለ ፍቅር የሚሰብክ አንደበተ ለስላሳ የውጭ አልጋየ ቤት ቀጋ የሆነ ይሆናል። ነገር ግን ስለተመረጡት ቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ዕድሜው አጭር ይሆናል ::

ትንቢት ስለ ንጉሥ ቴዎድሮስ:-

ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ በኢትዮጵያ ምድር ደገኛ ንጉሥ ይነግሣል። ኢትዮጵያን በዘንግና  በነጭ መነሳንስ አርባዘመን(ዓመት) የሚገዛ ንጉሥ (ቴዎድሮስ ይሉታል ) ይነግሣል። የሚነሳው ም ከምስራቅ ነው። በእርሱ ዘመን ስደት ወደ ኢትዮጵያ ይሆናል።

በዚያን ዘመን የአንድ ላም ወተት የአንድ በሬ ጉልበት በቂ ነው፤ አህያና ጅብ በአንድ ላይ ይውላሉ በአንድ ላይ ያድራሉ።

አንድ እንጀራ ለአገር ሰው ያጠግባል፤ በእርሱ ዘመን እንኳን የሰው የእንጨት ጠማማ አይኖርም።

በዚያን ዘመን የኢትዮጵያ ግዛት ይሰፋል ኤርትራም ወደ እናት ሀገሯ ትመለሳለች ፍቅር እና አንድነት ይሆናል። ኢትዮጵያ እጅግ ታላቅ ሀገርት ሆናለች። በእርሱ ዘመን የሚነሱት ፖትሪያክ እጅግ የበቁ እና ገቢረ ተአምር የሚያደርጉ ይሆናሉ። በዚህ ሰው ንግሥና ዘመን በኢትዮጵያ ፍፁም ሠላም ይሆናል በሀገሪቱም በረከት ይሆናል ከሌላው ሀገር ተለይታም የጥጋብ እና የበረከት ሀገርት ሆናለች።

የበርካታ ሀገር ስደተኞችንም የምታስተናግድ የስደተኞች መጠለያ እና ማረፊያ ትሆናለች።
ለዘመናት ደም ሲቃቡ የነበሩት ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያዊንም አንድ ይሆናሉ። ሁለቱም ወንድማማች ህዝብ ወንድማማችነታቸውን አድሰው በሰላም በፍቅር ይኖራሉ። 

በዚያን ዘመን የሚሾሙት ፖትሪያክ ህዝቡን ከአምላኩ ከእግዚአብሔር የሚያስታርቁ ሀገርን የሚጠብቁ ተአምር የማድረግ ፀጋ የተሰጣቸው ትልቅ አባት ናቸው።

አቤቱ የድንግል ማርያም ልጅ ሆይ ይህን ዘመን አሳየን ::

አሜን(፫)

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment