ጨቅላ ሕፃናትን ማስወረድ ትልቅ ኃጢያት ነው፤ ማስወረድ ሰው መግደል ማለት ነው፤ ሰው መግደል ደግሞ የሚያስገድል ነው።
ፅንስ ማስወረድ በአሜሪካና ሌሎች ምዕራባውያን መንግስታት አበረታችነት የመጣና ከፍተኛ የሞራል ዝቅጠት ያስከተለ ተግባር ነው። የምዕራቡ ዓለም ጽነስ በማስወረድና የሰዶም እና ገሞራ ዓይነት አኗኗር ውስጥ በመግባት የሕዝባቸው ቁጥር እየቀነሰ ስለመጣ አሁን ሰዎች በመንቃት ላይ ናቸው፤ እራሳቸውን ማዳን አለባቸውና።
በተቃራኒው ግን ይህን በሽታቸውን ወደ አፍሪቃውያን አገሮች በማሰራጨት ላይ ናቸው።
"ሜሪ ስቶፕስ" የተባለውና ከፅንስ ማቋረጥ ጋር በተያያዘ ወንጀል የሚፈጽመው ጽንፈኛ ድርጅት በጎረቤት ሀገር ኬንያ ባለፈው ዓመት ላይ ታግዷል። በኢትዮጵያ ግን አሁንም ሕፃናቱን በመግደል ላይ ይገኛል።
የአፍሪቃውያን ሕዝብ ቁጥር መጨመር ምዕራባውያኑን በጣም አሳስቧቸዋል። በሀገራችን የሚታየው የፅንስ ማስወረድ ወረርሽኝ፤ ከታቀደልን የጎሣ እና ኃይማኖት ጦርነቶች ጋር ተደምሮ የሕዝባችንን ቁጥር ይቀንሳል ብለው በጽኑ ያምናሉ። በዚህ መልክ በኢትዮጵያ ብቻ እስከ ሃምሳ ሚሊየን ሰዎች በሚቀጥሉት ዓመታት መገደል አለባቸው። አሁን እየተነገረን ያለው የሕዝባችን ቁጥር በፍጹም መቶ ሚሊየን አልደረሰም። ኢትዮጵያ ቢበዛ ቢበዛ ስልሳ ሚሌየን ነዋሪዎች ነው ያሏት።
Blogger Comment
Facebook Comment